Go to full page →

ንግድ MYPAmh 145

ጌታ በአገልግሎቱ ውስጥ በተለያየ የሥራ መስመር ብቃት ያላቸው አዋቂ ሰዎች እንዲኖሩት ይፈልጋል፡፡ ግልጽ የሆኑና የእውነትን መርሆዎች በንግዳቸው ውስጥ ሸምነው ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ሰዎችን ይፈልጋል፡፡ ችሎታዎቻቸው ጥልቅ በሆነ ጥናትና ሥልጠና ወደ ፍጽምና መድረስ አለባቸው፡፡ በማንኛውም የሥራ ዘርፍ ያሉ ሰዎች ጠቢባንና ብቁ ለመሆን የተሰጡአቸውን አጋጣሚዎች ማሻሻል ከፈለጉ ማድረግ ያለባቸው ችሎታቸውን በዚህ ዓለም የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት የሚጠቀሙ መሆን አለባቸው፡፡ ከዳንኤል የምንማረው ነገር ቢኖር በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ሁሉ እጅግ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር ቢደረግበትም እንኳን አንዲት ስህተት እንዳልተገኘበት ነው፡፡ እርሱ ለእያንዳንዱ የንግድ ሰው ሊከተለው የሚገባ ምሳሌ ነው፡፡ የእርሱ ታሪክ የአእምሮን፣ የአጥንትን፣ የጡንቻን፣ የልብንና የሕይወትን ብርታት ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚቀድስ ሰው ምን ማድረግ እንደሚችል ያሳያል፡፡ Christ’s Object Lessons, p. 350-351. MYPAmh 145.6