Go to full page →

ተቀባይነት ያለው አገልግሎት MYPAmh 148

እግዚአብሔር ገደብ በሌለው ፍቅሩ ከቃሉ ብርሃን ሰጥቶን እንዲህ ይላል፡- «በነጻ ተቀበላችሁ፣ በነጻ ስጡ፡፡» እግዚአብሔር የሰጣችሁ ብርሃን በጨለማ ላሉት ይብራ፡፡ ይህን ስታደርጉ ሳለ የሰማይ መላእክት ነፍሳትን ለክርስቶስ እንድትማርኩ ሊረዱአችሁ ከጎናችሁ ይሆናሉ፡፡ MYPAmh 148.1

ውድ ወጣት ወዳጆቼ ሆይ፣ ጌታን ለማገልገል የተቀባ አገልጋይ መሆን የግድ አስፈላጊ አይደለም፡፡ለክርስቶስ መስራት የምንችልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ፡፡ የሰው እጆች በለያችሁ ተጭነው አልተቀባችሁም ይሆናል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ለሥራው ገጣሚ ሊያደርጋችሁ ይችላል፡፡ በእናንተ አማካይነት ነፍሳትን ለማዳን መስራት ይችላል፡፡ በክርስቶስ ትምህርት ቤት በመማራችሁ በልባችሁ ትሁታንና የዋህ ከሆናችሁ ለእርሱ እንድትናገሩ ቃላትን ይሰጣችኋል፡፡ MYPAmh 148.2