Go to full page →

ከስህተቶች ጋር ያለን ግንኙነት MYPAmh 148

ፍጽምናን ለማግኘት ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ ነገር ግን ስህተት ስለፈጸማችሁ ከእግዚአብሔር አገልግሎት እንደተገለላችሁ አድርጋችሁ አታስቡ፡፡ ጌታ አፈጣጠራችንን ያውቃል፤ አፈር መሆናችንንም ያስታውሳል፡፡ እግዚአብሔር የሰጣችሁን መክሊቶች በታማኝነት ስትጠቀሙ በራሳችሁ እንዳትረኩ የሚያደርግ እውቀትን ታገኛላችሁ፡፡ በመጥፎ ምሳሌነታችሁ ሌሎችን እንዳትጎዱ ጎጂ ባሕርያትን የማስወገድ አስፈላጊነትን ታያላችሁ፡፡ MYPAmh 148.3

ለእናንተ ክቡር የሆነውን እውነት ለሌሎች በመስጠት ተግታችሁ ሥሩ፡፡ ከዚያም ሊሞሉ የሚገቡ ክፍተቶች በሚኖሩበት ጊዜ «ወደ ላይ ከፍ በሉ» የሚሉ ቃላትን ትሰማላችሁ፡፡ ምናልባት ምላሽ ለመስጠት አትፈጥኑም ይሆናል፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ትኩስና እውነተኛ ቅናት በማምጣት በእምነት ወደ ፊት ተጓዙ፡፡ MYPAmh 148.4

ነፍሳትን የመማረክን ምስጢር መማር የምንችለው ከታላቁ መምህር ነው፡፡ ጤዛና ሰላማዊ ዝናብ እየጠወለጉ ባሉ ተክሎች ላይ በቀስታ እንደሚወርድ ሁሉ እንደዚሁ ቃላቶቻችን ልናድናቸው በምንፈልጋቸው ነፍሳት ላይ በቀስታና በፍቅር መውረድ አለባቸው፡፡ አጋጣሚዎች እስኪመጡልን ድረስ መጠበቅ የለብንም፤ እግዚአብሔር በትክክለኛው ጊዜ ተገቢ የሆነውን ቃል እንድንናገር እንዲረዳን ልባችንን በጸሎት ወደ ላይ በማንሳት አጋጣሚዎችን መፈለግ አለብን፡፡ አጋጣሚው ሲመጠላችሁ ላለመጠቀማችሁ ምንም ምክንያት ሊሰጥ አይገባም፡፡ ያገኛችሁትን አጋጣሚ በአግባቡ መጠቀም ማለት ነፍስን ከሞት ማዳን ማለት ነው፡፡ The Youth,s Instructor, Februay 6,1902. MYPAmh 148.5