Go to full page →

ከሁሉ የበለጠ ሥራ MYPAmh 148

ከሥራ ሁሉ የሚበልጥ ሥራ፣ የነፍስን ኃይላት መሳብና ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ ያለበት ሥራ ክርስቶስ የሞተላቸውን ነፍሳት የማዳን ሥራ ነው፡፡ ይህንን ሥራ የሕይወታችሁ ዋናና አስፈላጊ ሥራ አድርጉት፡፡ የሕይወታችሁ የተለየ ሥራ አድርጉት፡፡ በዚህ ታላቅና ክቡር ሥራ ከክርስቶስ ጋር ተባበሩ፡፡ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ሚስዮናውያን ሁኑ፡፡ ለሌሎች መዳን በመሥራት በአዳኛችሁ ላይ ያላችሁን እምነት አሳዩ፤ የእግዚአብሔርንም ሥራ ሥሩ፡፡ ወጣቶችና አዛውንት ሙሉ በሙሉ ተለውጠው በአጠገባቸው ያለውን ሥራ ቢሰሩና ከክርስቶስ ጋር አብራው ሠራተኞች በመሆን አጋጣሚው እያለላቸው ቢሰሩ ኖሮ እንዴት መልካም ነበር! The Youth’s Instructor may 4, 1893. MYPAmh 148.6