Go to full page →

በአገልግሎት ታማኝነት MYPAmh 149

በምድራዊ ጉዳዮች በትንሹ ያልታመኑ ትልቅ ጠቀሜታ ባላቸው ኃላፊነቶችም የማይታመኑ ይሆናሉ፡፡ እግዚአብሔርን ይዘርፋሉ፣ የመለኮታዊ ህግ ጥያቄንም ሳያሟሉ ይቀራሉ፡፡ መክሊቶቻቸው የእግዚአብሔር መሆናቸውንና ለአገልግሎቱ መዋል እንዳለባቸው መገንዘብ አለባቸው፡፡ የሥራው ብልጽግና በእነርሱ የተለየ ጥረት የሚደገፍ መሆኑን እያወቁ እንዲሰሩ ከታዘዙት ሥራ ውጭ ለቀጣሪዎቻቸው ምንም ነገር የማያደርጉ እንደ ታማኝ አገልጋዮች አይቆጠሩም፡፡ መሰራት ያለባቸው ግን በሥራ ዝርዝር ውስጥ ያልተቀመጡና በቀጣሪው እይታ ውስጥ በቀጥታ የሚገቡ ብዙ ሥራዎች አሉ፡፡ MYPAmh 149.1

በኢየሱስ የተሰጡን የፍቅር መርሆዎች በስሙ እንደሚያምኑ በሚናገሩ ሰዎች ቢገለጽ ኖሮ፣ ልፋትን የሚጠይቅ ትጋትና ራስ ወዳድነት የሌለበት ጥረት ቢገለጽ ኖሮ ሊደርሱ የሚችሉ መንጠባጠቦችና ክስረቶች ይከለከሉ ነበር፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ ያሉ ብዙዎች እንደ «ታይታ አገልጋዮች» የተመዘገቡ ናቸው፡፡ MYPAmh 149.2