Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የልበ-ወለድ ውጤት

    ብዙ ወጣቶች “ትምህርቴን ለማጥናት ጊዜ የለኝም” ይላሉ። ነገር ግን ምን እያደረጉ ናቸው? አንዳንዶች እያንዳንዷን ደቂቃ ጥቂት ተጨማሪ ሳንቲሞችን ለማግኘት እያጨናነቁ ናቸው። ይህ በስራ የተጨናነቀ ሰዓት መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ እና የእርሱን ትምህርቶች ቢለማመዱበት ኖሮ ያለመጠን በመስራት ካተረፉት የበለጠ ትርፍ ያስገኝላቸው ነበር። በማያስፈልጉ ጌጣጌጦች የሚባክነውን ገንዘብ ያተርፍላቸው ነበር! እንደዚሁም የአእምሮን ብርታት በመጠበቅ እግዚአብሔርን የመምሰልን ምስጢር እንዲያስተውሉ ይረዳቸው ነበር። “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው::”MYPAmh 188.1

    ነገር ግን እነዚህ ክርስቲያን ነን የሚሉ ወጣቶች የራሳቸውን ዝንባሌ በመከተል የልባቸውን ስጋዊ ፍላጎት ያሟላሉ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውድ እውነቶች ጋር እንዲተዋወቁ በእግዚአብሔር የተሰጣቸው የምህረት ጊዜ ልበ-ወለድና አፈ-ታሪኮችን ለማንበብ ተሰጥቷል። ይህ ልምድ አንዴ ከተመሠረተ ለማሸነፍ ከባድ ነው። ነገር ግን ለሰማያዊው ዓለም እጩ በሆኑ ሰዎች ሊደረግ ይችላል። መደረግም አለበት።MYPAmh 188.2

    ታሪክን በማንበብ እንዲወሰድ የተፈቀደ አእምሮ ተበላሽቷል። አስተሳሰብ የታመመ ይሆናል፣ ግምታዊነት አእምሮን ይቆጣጠራል። ከዚህም የተነሳ ግልፅ ያልሆነ መረበሽና ያለ ማቋረጥ የአእምሮ ሚዛንን ለሚያዛባ ያልተሟላ የአእምሮ ምግብ እንግዳ የሆነ ፍላጎት ይፈጥራል። ዛሬ ልበ-ወለድ ጽሁፎችን በማንበብ አእምሮአቸው ሚዛን ያጣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአእምሮ በሽተኞች መጠለያ አሉ። ውጤቱ በአየር ላይ ቤተ መንግስት መገንባትና የፍቅር በሽተኝነት ስሜት ነው። Signs of the Times, February 10, 1881.MYPAmh 188.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents