Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለተጋድሎው ብርታት

    ለሕፃናት ባልታደለ ዘመን ውስጥ እየኖርን ነን፡፡ ወደ ጥፋት የሚያመራ ከባድ ሞገድ እየመጠ ስለሆነ ይህንን ሞገድ ለመቋቋምና በእርሱ ከመወሰድ ለመዳን ከሕፃንነት ልምምድ የበለጠ ልምምድና ጥንካሬ ያስፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ ወጣቶች የሰይጣን ምርኮኞች ይመስላሉ፤ እርሱና መላእክቱ እርግጠኛ ወደሆነ ጥፋት እየመሩአቸው ነው፡፡ ሰይጣንና ሰራዊቶቹ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየተዋጉ ናቸው፡፡ ልባቸውን ለእርሱ ለመስጠትና ትዕዛዙን ለመታዘዝ ፍላጎት ያላቸውን ሁሉ ተስፋ እንዲቆርጡና በጦርነቱ እጅ እንዲሰጡ ለማድረግ ሰይጣን ግራ ሊያጋባቸውና በፈተናዎቹ ሊያሸንፋቸው ይሞክራል…፡፡MYPAmh 218.1

    ልባዊ በሆነ ጸሎትና ሕያው እምነት ታላላቅ ድሎች ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ ወላጆች በለያቸው ያለውን ኃላፊነት ባለመገንዘብ የልጆቻቸውን መንፈሳዊ ትምህርት ችላ ብለዋል፡፡ በማለዳ የክርስቲያን የመጀመሪያ ሀሳቡ በእግዚአብሔር ላይ መሆን አለበት፡፡ ዓለማዊ ሥራና የራስ ፍላጎት ሁለተኛ መሆን አለባቸው፡፡ ለሥራ ከቤት ከመውጣታቸው በፊት የቤተሰብ አባላት በሙሉ ተጠርተው አባት ወይም አባት በሌላ ጊዜ እናት በቀኑ ውስጥ እግዚአብሔር እንዲጠብቃቸው የጋለ ልመና መደረግ አለበት…፡፡MYPAmh 218.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents