Go to full page →

ጤናና ንጽህና MYPAmh 227

ልብሳችን ንጹህ መሆን አለበት፡፡ የልብስ ንጽህና ማጣት ጤናማ ያልሆነና አካልንና ነፍስን የሚያረክስ ነው፡፡ «እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናችሁ…ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያረክስ እግዚአብሔር እርሱን ያጠፋዋል፡፡” 1ኛ ቆሮ. 3፡16-17፡፡ MYPAmh 227.5

በማንኛውም ረገድ ቢሆን ልብሳችን ለጤና ተስማሚ መሆን አለበት፡፡ «ከሁሉም ነገር በማስቀደም ባለጤና እንድንሆን» እግዚአብሔር ይሻል፡፡ 3ዮሐ.2፡፡ በአካልና በነፍሳችን ጤነኞች እንድንሆን ይፈልግብናል፡፡ ለአካልና ለነፍስ ጤንነት ከእርሱ ጋር አብረን ሰራተኞች መሆን አለብን፡፡ አካላችን በጤናማ አለባበስ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኛል፡፡ MYPAmh 227.6