Go to full page →

በመርህ መመራት MYPAmh 256

ብዙዎች መርህን ተከትለው ነገሮችን መፈፀም የማይፈልጉበት ምክንያት ድርጊታቸው ጓደኝነትን የሚያበላሽ ትችት ወይም አደገኛ የሆነ ሀሜትን ሊያስነሳባቸው እንደሚችል በመፍራት ነው። ክርስቶስን ከሙሉ ልባቸው ከሚከተሉ ጋር ለመቆም አይደፍሩም። ከዓለማዊ ባሕሎች ጋር ለመስማማትና የዓለማውያንን ተቀባይነት ለማግኘት ይሻሉ። ክርስቶስ ራሱን ለኛ የሰጠው “እኛን ከበደላችን ሁሉ ሊዋጀንና ለራሱ አንጽቶን መልካም ስራን ለመስራት የሚቀና የተለየ ህዝብ ሊያደርገን ነው።” Review and Herald, Nov. 29, 1887. (402) MYPAmh 256.2