Go to full page →

ወደ ፊት መመልከት MYPAmh 293

የቤተሰባቸውን ቁጥር ከመጨመራቸው በፊት ልጆችን ወደዚህ ዓለም በማምጣታቸው እግዚአብሔር የሚከብርበት ወይም የማይከብርበት መሆኑን ማገናዘብ አለባቸው። ከመጀመሪያው ጀምረው በእያንዳንዱ የጋብቻ አመታቸው እግዚአብሔርን ለማስከበር መሻት አለባቸው። ለልጆቻቸው ሊደረግላቸው የሚገባውን ነገር በጥንቃቄ ግምት ውስጥ ያስገቡ። ለሌሎች ሸክም የሚሆኑ ልጆችን በዚህ ዓለም ላይ የማምጣት መብት የላቸውም። ቤተሰባቸውን መደገፍ የሚችልና ለሌሎች ሸክም ከመሆን የሚከለክል ስራ አላቸውን? ካልሆነ ተገቢ ጥንቃቄ፣ ምግብ ፣ልብስና ሌሎችንም ነገሮች በማጣት የሚሰቃዩ ልጆችን በዚህ ዓለም ላይ በማምጣት ወንጀል እየሰሩ ናቸው። MYPAmh 293.2