Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለፍላጎትዋ ለተገዛች ሴት ልጅ የተሰጠ ምክር

    በሰማይ ንጉስና ቁጥር ስፍር በሌላቸው ንፁህ የሰማይ መላእክት ፊት የተገለጠ ያለፈው ዓመት አስፈሪ መዝገብ አለሽ፡፡ ሐሳቦችሽና ድርጊቶችሽ •እንደዚሁም ያልተቀደሱ ፍላጎቶችሽ ከሟቾች ተደብቀው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን እጅግ ተራ የሆኑ የሕይወትሽ ድርጊቶች ለእግዚአብሔር እይታ ክፍት ናቸው፡፡ በሰማይ የጎደፈ መዝገብ አለሽ:: የፈፀምሻቸው ኃጢአቶች በሙሉ እዚያ ተመዝግበዋል፡፡MYPAmh 55.1

    የእግዚአብሔር ፊት የተፈታልሽ አይደለሽም፤ ሆኖም ስሜት የሌለሽ ትመስያለሽ፡፡ ተስፋ በሌለው ሁኔታ መጥፋትሽን አልተገነዘብሽም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የፀፀት ስሜት አለሽ ፤ ነገር ግን ኩሩና በራስ መተማመን የተሞላ መንፈስሽ ወዲያውኑ ከፀፀትሽ በላይ ይነሳና የህሊና ድምጽን ( ወቀሳን) ታፍኝያለሽ፡፡MYPAmh 55.2

    ደስተኛ አይደለሽም፡፤ ነገር ግን ያለ አንዳች ገደብ የራስሽን መንገድ እንድትከተዪ ብትተዪ ደስተኛ እንደምትሆኚ ትገምችያለሽ፡፡ ምስኪን ልጅ! አንቺ ሄዋን በኤድን ገነት ይዛ የነበረውን ቦታ ነው ይዘሽ ያለሽው፡፡ እግዚአብሔር እንዳይሞቱ በማለት እንዳይነኩ የከለከለውን ፍሬ ብትበላ እጅግ ከፍ ከፍ እንደምትል ገመተች፡፡ ፍሬውን በላች፤ የኤድንን ክብር በሙሉ አጣች፡፡MYPAmh 55.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents