Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለምልመላ ጥሪ

    ክርስቶስ ፈቃደኞችን ከ•ርሱ ዓላማ ሥር እንዲመዘገቡና የመስቀልን ዓላማ እንዲሸከሙ እየጠራቸው ነው:: ቤተክርስቲያን በድፍረት የተሞላ ምስክርነትን የሚሸከሙ፣ ባላቸው የጋለ ቅንዓት የዛለውን የእግዚአብሔር ህዝብ ኃይል የሚቀሰቅሱና የቤተክርስቲያንን ኃይል በዓለም ላይ የሚጨምሩ ወጣት ወንዶችን በማጣት እየደከመች ነው:: የአለማዊነትን ማዕበል የሚከላከሉና በፍትወትና በእርኩሰት ላይ የመጀመሪያ እርምጃ በመውሰድ የተቃውሞ ድምፅ የሚያነሱ ወጣት ወንዶች ይፈለጋሉ::MYPAmh 23.6

    ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያገለግሉና ራሳቸውን ለሥራው የሚሰጡ ወጣቶች በመጀመሪያ የነፍስን ቤተመቅደስ ከእርኩሰት ሁሉ ማጽዳትና ክርስቶስን በልባቸው ማንገስ አለባቸው:: ከዚያ በኋላ በክርስቲያናዊ ጥረታቸው ኃይል እንዲጨምሩ ይደረጉና ሰዎች ከክርስቶስ ጋር እንዲታረቁ ለማድረግ የጋለ ቅንዓት ያሳያሉ:: ወጣቶቻችን ለክርስቶስ ጥሪ «እነሆ እኔን ላክ» ብለው አይመልሱለትምን? ወጣቶች ሆይ! ወደፊት እየገፋችሁና ሥራውን እርሱ ካቆመበት በመቀበል እስከፍፃሜው በመሸከም ከክርስቶስ ጋር አብሮ ሠራተኛ መሆናችሁን አሳዩ:: Review and Herald, June16, 1891.MYPAmh 24.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents