Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የምድር ባዶ መሆን

    ኃጢአቷ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሷልና እግዚአብሔርም ዓመፃዋን አሰበ ... በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤ ራሷን እንዳከበረችና እንደተቀማጠለች ልክ ስቃይና ሃዘን ስጧት። በልቧ ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ ባልቴትም አልሆንም ስላለች ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኅዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፥ በእሳት ትቃጠላለች፥ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና። ከእርሷ ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠሏን ጢስ ሲያዩ ስለ እርሷ ... ያለቅሳሉ፥ አንቺ ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን ወዮልሽ ወዮልሽ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሷልና እያሉ ይናገራሉ» (ራዕ. 18፡5-10)፡፡ታተ 79.1

    በእርሷ «የከበረ ድንጋይ ባለጠጋዎች የሆኑት» «የምድር ነጋዴዎች» «በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጎናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት ወዮላት ይህን የሚያህል ታላቅ ባለጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቷልና እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሳ በሩቁ ቆመው ... ያለቅሳሉ» (ራዕ. 18፡11, 15-17)ታተ 79.2

    ባቢሎን በእግዚአብሔር ቁጣ በምትጎበኝበት ጊዜ ፍርዷ ይህን ይመስላል። የበደሏን ጽዋ ሞልታለች፥ ጊዜዋ አሁን መጥቷል፥ ለመደምሰስ በስላለች።ታተ 79.3

    የእግዚአብሔር ድምጽ የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፥ በታላቁ የሕይወት ውዝግብ የተሸነፉት «ታውረው» ከነበሩበት ሁኔታ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ይነቃሉ። የምህረት የጊዜ ገደብ መዘጋት በተራዘመ ጊዜ ዓይናቸው በሰይጣን ማታለያዎች ታውሮ ነበር፡፡ የኃጥያት ተግባራቸውንም እንደ መልካም ተግባር ተቀብለው ነበር። የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላለፍ ብልጽግናቸውን ያካበቱት ባለጸጋዎች በበታቾቻቸው ላይ ኩራታቸውን ያሳዩ ነበር። ድሆችን መመገብን፣ የታረዙትን ማልበስን፣ ቅንነትንና ምህረትን መውደድ ዘንግተው ነበር። ራሳቸውን ከፍ በማድረግ እንደ እነርሱ ፍጡር ከሆኑት ክብርንና ዝናን ማግኘትን ተመኙ። አሁን ግን ዝናን ካስገኘላቸው ነገር ሁሉ ተነጥቀው ባዶአቸውን ያለ ከለላ ቀሩ። ከፈጣሪ ይልቅ የመረጧቸው ጣኦቶች ሲወድሙ ሲያዩ አሁን ሽብር ያዛቸው። በእግዚአብሔር ዘንድ ባለጸጋ መሆንን በመመኘት ፈንታ ለምድራዊ ብልጽግናና ተድላ ሲሉ ነፍሳቸውን ሸጡ። ውጤቱ ለሕይወታቸው ውድቀት ሆነ። ተድላቸው ወደ ኀዘን ተቀየረ፥ ብልጽግናቸውም ከንቱ ሆነ። በሕይወት ዘመን ያካበቱት ሃብታቸው በቅጽበት በኖ ጠፋ። ባለጸጋዎች ስለወደመው ግዙፉ ቤታቸው፣ ስለተበተነው ወርቃቸው እና ስለ ብራቸው አለቀሱ። ይህ ለቅሷቸው ግን እነርሱ ራሳቸው ከጣኦቶቻቸው ጋር በመጥፋታቸው ፍራቻ ጸጥ ተሰኘ።ታተ 79.4

    ኃጢአተኞች ጸጸት ተሰማቸው፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን እና ወገኖቻቸውን በመቃወማቸው ኃጢአት ሳይሆን የሚፀፀቱት፣ እግዚአብሔር ስላሸነፋቸው ነው የቆጫቸው። ውጤቱ አስለቀሳቸው፥ ነገር ግን ከጥፋታቸው ንስኃ አልገቡም። ማሸነፍ የሚያስችላቸው አጋጣሚ እንኳን ቢኖር ያንን ይሞክራሉ።ታተ 79.5

    ዓለም ሁሉ እነሱ የቀለዱባቸውንና የተሳለቁባቸውን፣ ሊያጠፏቸው የሞከሩትንና በመከራ፣ በመሬት መናወጥ ውስጥ ያለጉዳት ያለፉትን የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ተመለከተ። ለሕግ ተላላፊዎች የሚባላ እሳት የሆነው አምላክ፤ ለሕዝቦቹ አስተማማኝ ድንኳን ነው።ታተ 79.6

    የሰዎችን ተቀባይነት ለማግኘት ብሎ እውነትን መስዋዕት ያደርግ የነበረ አገልጋይ፤ አሁን ባህሪው እና ትምህርቱ ያስከተለውን ተጸዕኖ በግልጽ ተመለከተ። በእርግጥ በመድረኩ ላይ በቆመ ጊዜ፣ በመንገድ ሲራመድ፣ በሕይወት ዘመኑ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ሲቀላቀል፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ይከታተለው እንደነበር አሁን ግልፅ ሆነ። እያንዳንዱ የነፍስ ስሜት፣ እያንዳንዱ የተጻፈ ፅሁፍ፣ እያንዳንዱ የተነገረ ቃል፣ ሰው በሃሰት ላይ እንዲታመን የተደረገ እያንዳንዱ ድርጊት ዘሩን ዘርቶ ነበር፡፡ አሁን በዙሪያው ያሉትን በርኩሰት የጠፉትን ሰዎች ሲመለከት ይህ አገልጋይ መከሩን አጨደ።ታተ 79.7

    ጌታ እንዲህ ይላል፡- «የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፥ ሰላም ሳይኖር፥ ሰላም ሰላም ይላሉ።» «የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋል፥ በሕይወትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገዱ እንዳይመለስ የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና።» (ኤር. 8፡11 ፤ ሕዝ. 13፡22)ታተ 79.8

    «የመሰማሪያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው ይላል እግዚአብሔር፥ [ለክፋታችሁ] አባርራችኋለሁ።» «ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሷልና ... ሽሽት ከዕረኞች ማምለጥም ከመንጋ አውራዎች ይጠፋል» (ኤር. 23፡1-2 ፤ ኤር. 25፡34-35)ታተ 79.9

    አገልጋዮች እና ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር ቀና ግንኙነት እንዳልነበራቸው አሁን ተገነዘቡ። የጻድቅ እና የቅን ሕግ ምንጭ በሆነው ላይ እንዳመጹ አሁን ተመለከቱ። መለኮታዊው ሕግ ወደ ጎን መደረጉ በሺ ለሚቆጠሩ ክፋቶች፣ አለመግባባቶች፣ ጥላቻዎች፣ እና መተላለፎች ምክንያት ሆነ፤ ምድርም የጥል መንደር እና የጥፋት ረግረግ ሆነች። ይህ እይታ ነበር ለእነኝያ እውነትን ተቃውመው ስህተትን መርጠው ለነበሩት የታየው፡፡ የማይታዘዙና ታማኝ ያልነበሩት የዘላለም ሕይወትን የማግኘት ተስፋቸው ለዘላለም እንዳከተመ ሲገነዘቡ የተሰማቸውን ምኞት ቋንቋ ሊገልጸው አይችልም። ዓለም ስለ መክሊታቸው እና ስለ አንደበተ-ርቱዕነታቸው ሲያመልኳቸው የነበሩ ሰዎች አሁን ግን እነዚህን ነገሮች በእውነተኛ ብርሃን ተመለከቷቸው። በመተላለፋቸው ምክንያት ስለ ሰማይ ያላቸው ተስፋ ተሟጠጠ፥ አሁን ሲንቋቸው እና ሲጸየፏቸው በነበሩት ሰዎች ፊት በእግራቸው ሥር ወድቀው እግዚአብሔር ይወዳቸው እንደነበር ተናዘዙ።ታተ 80.1

    ሰዎቹ መታለላቸውን ተገነዘቡ። «ወደ ጥፋት የመራኸኝ አንተ ነህ!» በመባባል እርስ በእርስ ተካሰሱ፡፡ ነገር ግን ሁሉም በአንድነት፣ ምሬት በተሞላበት ውግዘት አገልጋዮችን ወቀሱ። ታማኝ ያልነበሩ መጋቢዎች (ፓስተሮች) የሚያረጋጋ ትንቢትን ይናገሩ ነበር፡፡ አድማጮቻቸው የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲያስወግዱ እና በቅድስና የሚጠብቁትንም ሰዎች እንዲያሳድዱ ይመሩ ነበር። አሁን ግን እነኚህ አስተማሪዎች ተስፋ በመቁረጥ የተሳሳተ ትምህርት ያስተምሩ እንደነበር በማመን በዓለም ሁሉ ፊት ተናዘዙ። እልፍ አዕላፍ ሰዎች በቁጣ ተሞልተው ወደ ሃሰተኞቹ እረኞች ዞረው፡- «ጠፍተናል! ለመጥፋታችን ምክንያቶቹ እናንተ ናችሁ» እያሉ አለቀሱ። ከዚህ ቀደም ከፍ ከፍ በማድረግ ያደንቋቸው የነበሩትን አገልጋዮች አሁን በዚያው መጠን የስድብ ናዳ አወረዱባቸው። የምስጋና አክሊል ሲጭንላቸው የነበረው እጅ መልሶ ሊያጠፋቸው ተነሳባቸው። የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማረድ ተዘጋጅቶ የነበረው ሰይፍ አሁን ጠላቶቻቸውን ለማጥፋት ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ ሁሉም ስፍራ ጥል እና በደም መፋሰስ ተሞላ።ታተ 80.2

    «እግዚአብሔር ከሕዝብ ጋር ክርክር አለውና ድምጽ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፥ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል።» (ኤር. 25፡31) ላለፉት ስድስት ሺህ ዘመናት ታላቁ ተጋድሎ ሲካሄድ ነበረ፥ የእግዚአብሔር ልጅ እና ሰማያዊ መልእክተኞቹ ከክፋት ኃይሎች ጋር በመጋደል የሰው ልጆችን ለማዳን በማስጠንቀቅና በማነቃቃት እንዲሁም ለማዳን ይጥሩ ነበር። አሁን ግን ሁሉም ወስነዋል፡፡ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ጋር በጀመረው ጦርነት ኃጢአን በአንድነት ከእርሱ ጋር ተባበሩ፡፡ እግዚአብሔር የተረገጠውን ሕጉን እውነተኛነት የሚያረጋግጥበት ጊዜ ደረሰ። አሁን ተጋድሎው ከሰይጣን ጋር ብቻ ሳይሆን ከሰዎችም ጋር ጭምር ሆነ። «እግዚአብሔር ከሕዝቦች ጋር ክርክር አለው» «ኃጢአንን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል»፡፡ታተ 80.3

    በመካከሏ «ስለተሰራው እርኩሰት ዘወትር በሚያለቅሱትና በሚተክዙ ፊት ላይ» የአርነት መውጣት ምልክት ታየባቸው። በሕዝቅኤል ራዕይ ላይ አጥፊውን ሰይፍ ይዘው በወጡ ሰዎች እና «ግደሉም፣ ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም፣ ሽማግሌውንና ጎበዙን ቆንጆይቱንም፣ ህጻናቶቹንም ሴቶችንም ፈጽማችሁ ግደሉ። ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው አትቅረቡ በመቅደሴም ጀምሩ» በሚል የተመሰለው የሞት መልአክ አሁን ወጣ። ነቢዩም በመቀጠል፡- «በቤቱም አንጻር ባሉት ሽማግሌዎች ጀምሩ» በማለት ተናገረ (ሕዝ 9፡1-6)፡፡ የማጥፋት ሥራ «የሕዝቡ መንፈሳዊ ሞግዚት ነን» በሚሉት ላይ ነው የሚጀምረው። ሃሰተኛ ጠባቂዎች ናቸው ቀድመው የሚወድቁት። የሚታዘንላቸውም ሆነ የሚተርፉ አይኖሩም። ወንዶች፣ ሴቶች፣ አገልጋዮች፣ እንዲሁም ህፃናቶች በአንድነት ይጠፋሉ።ታተ 80.4

    «በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቍጣውን ያመጣባቸው ዘንድ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፥ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።» (ኢሳ 26:21) «እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ይሆናል፤ እያንዳንዱም የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፥ እጁም በባልንጀራው እጅ ላይ ይነሣል።» (ዘካ. 14፡12-13) በመካከላቸው በሚፈጠረው የተቃወሰ የአለመግባባት ስሜት እና ሳይቀላቀል በሚፈስሰው የእግዚአብሔር ቁጣ፣ የምድር ነዋሪ የሆኑ፤ ካህናት፣ መሪዎች፥ ታላላቅ እና ታናናሽ ሰዎች ይወድቃሉ። «በዚያን ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ። አይለቀስላቸውም በምድር ላይ እንደጉድፍ ይሆናሉ እንጂ አይከማቹም፥ አይቀበሩም።» (ኤር. 25፡33)ታተ 80.5

    በክርስቶስ ዳግም ምፅአት ጊዜ ክፉዎች ከምድር ገፅ ሁሉ ላይ ይጠረጋሉ፣ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ ይበላሉ፥ በክብሩም ነጸብራቅ ይደመሰሳሉ። ክርስቶስ ሕዝቦቹን ወደ እግዚአብሔር ከተማ ይወስዳቸዋል፥ ምድርም ከነዋሪዎቿ የጸዳች ባዶ ትሆናለች። «እነሆ እግዚአብሔር ምድርን ባዶ ያደርጋታል፥ ባድማም ያደርጋታል፥ ይገለብጣትማል» «በርሷም የተቀመጡትን ይበትናል፥ ምድር መፈታትን ትፈታለች፥ ፈጽማም ትበላሻለች፥ እግዚአብሔር ይህንን ተናግሯልና።» «ሕጉን ተላልፈዋልና ስርዓቱንም ለውጠዋልና የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና፥ ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች በእርሷም የተቀመጡ ይቀጣሉ፥ ስለዚህ የምድር ሰዎች ይቃጠላሉ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።» (ኢሳ. 24፡1,3,5,6)ታተ 80.6

    ምድር ባዶ እና የተመሰቃቀለ ምድረበዳ መሰለች። በምድር መናወጥ፣ በዛፎች መገንደስ፣ በማዕበል ምክንያት በሚፈጠረው የድንጋይ ናዳ ከተሞች ተበላሹ፣ መንደሮችም ጠፉ፥ ተራሮች ከመሰረታቸው የተነሱበት አካባቢ እንደ ግዙፍ ዋሻ ሆኖ ታየ።ታተ 81.1

    ይህ እየሆነ ያለው ሁኔታ «የመንፃት ቀን» በመባል የሚታወቀው የተቀደሰ አገልግሎት እውነተኛ ክስተት ነው። በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የሚደረገው አገልግሎት ሲያበቃ፣ ለኃጢአት ስርየት ሲል በፈሰሰው ደም ኃይል የእስራኤል ኃጢአት ከቤተ መቅደስ በተወገደ ጊዜ፥ ወደ በረሃ ሊነዳ ዕጣ የወጣበት ፍየል ከነሕይወቱ በጌታ ፊት ይቀርባል። «በጉባኤው ፊትም ሊቀ ካህኑ እጁን ጭኖ ‹የእሥራኤል ልጆች ኃጢአት፣ እንዲሁም የኃጢአታቸው መተላለፍ ሁሉ በፍየሉ ላይ ይሁን› ብሎ ይናዘዛል።» (ዘሌዋ. 16፡21) በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የሰማዩ ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሲጠናቀቅ፥ በእግዚአብሔር እና በመላዕክት እንዲሁም በዳኑት ሠራዊት ፊት የእግዚአብሔር ሕዝብ ኃጢአት በሰይጣን ላይ ይጫናል። እርሱም እንዲፈጽሙ ላደረጋቸው ኃጢአቶች ሁሉ ተጠያቂ (በደለኛ) መሆኑ ይገለፃል። ወደ ምድረ በዳ እንደተነዳው የአዛዝኤል ፍየል ሰይጣንም ባዶ ወደሆነችው፣ ማንም ወደማይኖርባት፣ በእርግጥ ምድረበዳ ወደ ሆነችው ምድር ይነዳል።ታተ 81.2

    ባለ ራዕዩ የሰይጣንን መወገድ እና ዓለም የሚጠብቃትን ቀውስ ሲተነብይ ይህ ሁኔታ ለአንድ ሺህ ዓመታት እንደሚቆይ ገልጾታል። የጌታን ዳግም ምፅአት ሁኔታና የኃጥአንን መጥፋት ከገለፀ በኋላ ራዕዩ እንዲህ ይቀጥላል፡- «የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልዓክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፥ ሺህ ዓመትም አሰረው፣ ወደ ጥልቅም ጣለው፣ አህዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማህተም አደረገበት። ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባል።» (ራዕ. 20፡1-3)ታተ 81.3

    በሌሎች ጥቅሶች በምናገኘው መረጃ መሰረት ያ «ጥልቁ ጉድጓድ» የሚለው አባባል በግራ መጋባት እና በጨለማ ያለችውን ዓለም የሚወክል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በመጀመሪያ «ምድር ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበር» ይላል:: [እዚህ ላይ የተጠቀሰው በዕብራይስጥ ቃል «በጥልቁ» የሚለው ቃል በሰፕቱንጅንት ወይም «በግሪክ» ትርጉም በዚያው በተመሳሳይ ቃል በራዕ. 20፡1-3 ላይ «መጨረሻ የሌለው ጥልቅ» ተብሎ ሲጠቀም እናገኛለን] (ዘፍጥረት 1፡2)፡፡ ትንቢት እንደሚያስተምረን በከፊልም እንኳን ቢሆን ወደዚህ ሁኔታ ይመለሳል። ነብዩ ኤርሚያስ ታላቁን የእግዚአብሔር ቀን ወደፊት ሲመለከት እንዲህ ብሎ አውጆታል፡- «ምድሪቱን አየሁ፣ እነሆ፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም አልነበረባቸውም። ተራሮችንም አየሁ፥ እነሆም ተንቀጠቀጡ ኮሮብቶችም ሁሉ ተናወጡ። አየሁ፥ እነሆም ፥ ሰው አልነበረም፥ የሰማይ ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር። አየሁ፥ እነሆም ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፥ ከተሞችም ሁሉ ከጽኑ ቁጣው የተነሳ ፈርሰው ነበር።» (ኤር. 4፡23-26)ታተ 81.4

    የሰይጣን እና የክፉ መላእክቶቹ የአንድ ሺህ ዓመት ቤታቸው ይህን ይመስላል። ሰይጣን ካልወደቁት ከሌላ ዓለም ነዋሪዎች ጋር ተገናኝቶ መፈተኑ እና ማበሳጨቱ ሁሉ ቀርቶ በዚች ምድር ብቻ ተወስኖ ይቆያል። በዚህ አይነት ሁኔታ ነው የሚታሰረው። ስልጣኑን የሚለማመድበት አንድም ፍጡር አልቀረለትም። ለአያሌ ምዕተ-ዓመታት ብቸኛ የነፍሱ እርካታ ከነበረችው የማታለል እና የጥፋት ሥራው ፈጽሞ ተቆረጠ።ታተ 81.5

    ነቢዩ ኢሳይያስ ሰይጣን የሚጠብቀውን ፍርድ አስቀድሞ በማየት እንዲህ በማለት ጽፏል፡- «አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ ... አንተ በልብህ ወደ ሰማይ አርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አድርጋለሁ ... በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፥ ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ። የሚያዩህ ይመለከቱሃልና ‹በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ መንግሥታትንም ያናወጠ፥ ዓለሙን ባድማ ያደረገ፥ ከተሞችን ያፈረሰ፥ ምርኮኞችን ወደቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን?› ብለው ያስተውሉሃል።» (ኢሳ. 14፡12-17)ታተ 81.6

    ላለፉት ስድስት ሺህ ዓመታት የሰይጣን የአመጻ ሥራ «ዓለምን አናውጧታል» «ዓለምንም ምድረ በዳ አድርጓል፣ ከተሞችንም ለጥፋት ዳርጓቸዋል» እርሱ «እስር ቤቶችን ከፍቶ እስረኞችን ነጻ አልለቀቀም»፡፡ ለስድስት ሺህ ዓመታት እስር ቤቱ የእግዚአብሔር ልጆችን ለመቀበል ክፍት ነበር፥ ለዘላለምም ሊያስራቸው ምኞቱ ነበር፣ ነገር ግን ክርስቶስ ሰንሰለቱን ሰበረው፥ እስረኞችም ነጻ ወጡ።ታተ 81.7

    አሁን ግን ክፉዎች እንኳ ሳይቀሩ ከስልጣኑ ቁጥጥር ውጭ ሆኑ፥ ከእርኩሳን መላዕክቱ ጋር ብቻውን ቀርቶ የኃጢአት እርግማን ያመጣውን ውጤት ተመለከተ። «የአህዛብ ነግሥታት በየቤታቸው በክብር አንቀላፍተዋል። አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፥ ... ምድርህን አጥፍተሃልና፥ ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር አትሆንም።» (ኢሳ. 14፡18-20)ታተ 81.8

    ለአንድ ሺህ ዓመታት ሰይጣን በባዶ ምድረ በዳ በእግዚአብሔር ሕግ ላይ የማመጹን ውጤት እየተመለከተ ወዲያና ወዲህ ይንጎራደዳል። በእነዚህ ዓመታት የሚሰቃየው ስቃይ እጅግ የከፋ ነው። ከውድቀቱ ጊዜ ጀምሮ የነበረው ልፋት ምንም መልካም ውጤት አልታየበትም፥ አሁን ግን ኃይሉን ተነፍጎ በሰማያዊው መንግሥት ላይ ካመጸ ወዲህ የተጫወታቸውን ሚናዎች እያሰላሰለ፥ በፍርሃት እና በድንጋጤ እርሱ ራሱ ለሰራቸው ኃጢአቶች የሚደርስበትን ስቃይ እና ሌሎች እንዲሰሩ ላስገደዳቸው ኃጢአቶች የሚጠብቀውን ቅጣት በመንቀጥቀጥ እና በሽብር ይጠባበቃል።ታተ 82.1

    የሰይጣን መታሰር ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ደስታንና እርካታን አመጣላቸው። ነብዩ እንዲህ ይላል፡- «በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከኀዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል። ይህንም ምሳሌ በባቢሎን ንጉሥ [የባቢሎን ንጉሥ ሰይጣንን ይወክላል] ላይ ታነሣለህ እንዲህም ትላለህ። አስጨናቂ እንዴት ዐረፈ! አስገባሪም እንዴት ጸጥ አለ! አሕዛብንም በመዓትና በማያቋርጥ መምታት የመታውን፥ አሕዛብንም ባልተከለከለ መከራ በቍጣው የገዛውን የኀጥኣንን በትር የአለቆችንም ዘንግ እግዚአብሔር ሰብሯል። (ኢሳ. 14፡3-6)ታተ 82.2

    በመጀመሪያው ትንሳኤ እና በሁለተኛው ትንሳኤ መካከል በሺሁ ዓመት ጊዜ ውስጥ የኃጢአን ፍርድ ምርመራ ይሆናል። ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህ የፍርድ አፈጻጸም የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ተከትሎ እንደሆነ ይጠቁማል፡- «ስለዚህ በጨለማ የተሰወረውን ደግሞም ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።» (1ኛ ቆሮ. 4፡5)፡፡ ዳንኤል እንደሚገልፀው ደግሞ፣ ከዘመናት የሸመገለው ሲመጣ «ፍርድም ለልዑል ቅዱሳን እንደሚሰጥ ይገልጻል» (ዳን. 7፡22) በዚያን ጊዜ ቅዱሳን እንደ «የእግዚአብሔር ንጉሥ እና ካህናት» ሆነው ይነግሣሉ። ዮሐንስ በራዕዩ ሲናገር፡- «ዙፋኖችንም አየሁ፥ በእርሱ ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፥ ከኢየሱስ ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።» (ራዕ. 20፡4,6) በጳውሎስ የተነገረው ቃል የሚፈፀመው በዚህ ጊዜ ነው፡- «ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን?» (1ኛ ቆሮ. 6፡8)፡፡ ከኢየሱስ ጋር በህብረት ሆነው ተግባራቸውን በመጽሐፍ ከተጻፈው እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እያነጻጸሩ እያንዳንዷን ድርጊት በመመርመር ውሳኔ (ፍርድ) ይሰጣሉ፡፡ ከዚያም ክፉዎች የበደላቸው ውጤት ዕጣ ፈንታ በሞት መጽሐፍ ላይ በስማቸው አንጻር በተጻፈው መሰረት በሥራቸው መጠን ይፈረድባቸዋል።ታተ 82.3

    ሰይጣንና እርኩሳን መላዕክቱ በክርስቶስና በሕዝቡ አማካኝነት ይፈረድባቸዋል። ጳውሎስ ሲናገር፡- «በመላዕክት እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን?» (1ኛ ቆሮ. 6፡3)፡፡ ይሁዳም እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፡- «መኖሪያቸውን የተውትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላዕክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቋቸዋል።» (ይሁዳ 6)ታተ 82.4

    በሺህው ዓመት መጨረሻ ላይ ሁለተኛው ትንሳኤ ይከሰታል። ከዚያም ኃጢአተኞች ከሞት ተነስተው በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው «የተጻፈውን ፍርድ» ይቀበላሉ። ባለ ራዕዩ የጻድቃንን ትንሳኤ ከገለጸ በኋላ «የቀሩት ሙታን ግን ሺህው ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም» ሲል ገልጾታል። (ራዕ. 20፡5)። ኢሳይያስ ደግሞ የኃጢአተኞችን እጣ አስመልክቶ «ግዞተኞች በጉድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ፣ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ» በማለት ተናገረ፡፡ (ኢሳ. 24፡22)ታተ 82.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents