Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እግዚአብሔር ቃል ገብቷል!

    የተስፋን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለሆነ፣ አምነን
    የምንናገርለትን ተስፋ አጥብቀን እንያዝ፡፡
    ዕብ 10፡23

    ወደ ልጁ፣ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት
    የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው፡፡
    1 ቆሮ 19

    እኔ ግዚአብሔር ለመስጠት ቃል የገባውን ስጦታ ሁሉ፣ መጠየቅ እንችላለን፤ ከዚያም የጠየቅነውን እንደምንቀበል ማመን ያስፈልገናል:: እንዲሁም እንደተቀበልነው በመቁጠር ለእግዚአብሔር የምስጋናን ምላሽ መስጠት ይኖርብናል፡፡እግዚአብሔር ከሚሰጠው ከእያንዳንዱ የተስፋ ቃል በስተጀርባይቆማል፡፡እቃገ 7.1

    በሰማይ አባታችሁ መታመን አትችሉምን? ሰከበረው የተስፋ ቃሉ ላይ ማረፍ አትችሉምን? የተስፋውን ቃል የሰጠው እርሱ የታመነ ሆኑን በማወቅ በውስጣችሁ የተሰወረ መታመን ሌኖር አይችልምን? እየተናወጠ ያለው እምነታችሁ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይጠማጠም ዘንድ አደራ እላችኋለሁ፡፡ ሰማይናወጥ እምነት በተስፋው ቃል ላይ በመቆም ሸክማችሁን ሁሉ ተሸከሙ፤ የተስፋው ቃል ፈጽሞ አይጥላችሁም፤ ሊጥላችሁም አይችልም፡፡እቃገ 7.2

    የተባረከው የተስፋው ቃል፣ በእምነት ማእቀፍ ውስጥ ተደርጎ በአምሮአችሁ አዳራሽ ይንጠለጠላል። አንዱም እንኳን አይጠፋም፡፡እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ ያደርገዋል፡፡የተስፋውን ቃል የሰጠው እርሱ የታመነ ነውና። የተስፋ ቃሉን እውነተኛነት በማረጋገጥ ራሳችንን ከእግዚአብሔር ጋር አሁኑኑ ልናስተዋውቅ ይገባል፡፡ በእውነትና በትጋት የሚጸለየውን ጸሎት ሁሉ መላእክት ይመዘገባሉ፡፡ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ቸል ከምንል ይልቅ በራስ ወዳድነት የተሞላውን መሻታችንን ወደ ጎን መተው ይገባናል፡፡እቃገ 7.3

    ሰማያዊ አባታችን ፍላጎታችንን የሚያሚሳባቸው እኛ ፈጽሞ የማናውቃቸው አንድ ሺህ መንገዶች አሉት፡፡ ስለ ክርስቶስ አስቡ፡፡ የተስፋውን ቃል በማመን፣ በእምነት ወደ እርሱ ተመልከቱ፡፡ አዕምሮአችሁን ሰመታመን እንዲጸና አድርጉ፡፡እርሱም ማረፊያ ይሆናችኋል፡፡ ተደገፉት፣ ተማመኑበት፤ ...ክንዶቹ ፈጽሞ በማይጥሉት በእርሱ ላይ መታመናችሁን አድርጉ፡፡ ... ወደ ክርስቶስ በመመልከት መበረታታት ይሆንላችኋል፡፡እቃገ 8.1

    ክርስቶስ በስሙ ሊልክልን ተስፋ የሰጠው አጽናኝ ከእኛ ጋር አሉ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ከተማ በሚወስደው መንገድ በእርሱ የሚታመኑ ሊያልፉ የማይችሉት ምንም አይነት አስቸጋሪ መሰናክል የለም፡፡ ሊያመልጡት የማይችሉት አደጋ የለም፡፡ እርሱ መፍትሔውን ያላዘጋጀለት ምንም አይነት ሃዘን ወይም መከፋት እንዲሁም ሰብአዊ ድክመት የለም፡፡እቃገ 8.2

    ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል፤ ማንኛውንም ነገር በጸሎት ብንፈልጎ እንዳገኘነውም አድርገን ብንቆጥረው ይሆንልናል፡፡እንዲህ ያለው እምነት ተስፋ ለቆረጠችውና ሰሃዘን ለተመታችው ነፍስ፣ የጠቆረውን ደመና ሰንጥቆ የብርሃንን ጨረር ይፈነጥቅላታል፡፡ በአንጻሩ እንዲህ ያለውን እምነት ማጣት መደነጋገር፣ ጭንቀት፣ ፍርሃትና ክፋት እጅ መስጠትን ያስከትላል፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሙሉ መታመናቸውን በእርሱ ላይ በሚያደርጉበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ደግሞ ታላቅን ነገር ያደርግላቸዋል፡፡እቃገ 8.3

    እግዚአብሔር ስጦታዎቹን ሁሉ ለመስጠት ቃል የገባው እርሱን መታዘዝን እንደ መስፈርት በማስቀመጥ ነው፡፡ በክርስቶስ የተስፋ ቃሉች የምትታመነውን ነፍስ ጠላት ፈጽሞ ከጌታ እጆች ሊነጥቃት አይችልም፡፡እቃገ 9.1

    ራሳችሁን ለክርስቶስ ከሰጣችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል ናችሁ፤ በአብ ቤት ያለውም ሁሉ የእናንተ ነው፡፡ በዚህ ዓለምም ሆነ ሰሚመጣው የእግዚአብሔር ግምጃ ቤት ሁሉ ለእናንተ ክፍት ነው፡፡ የመላእክት አገልግሎት፣ የመንፈስ ስጦታ፣ የአገልጋዮቹ ልፋት እነዚህ ሁሉ ለእናንተ ናቸው፡፡ ዓላምና በውስጧ ያለው ሁሉ እስከጠቀማችሁ ድረስ የእናንተው ነው፡፡ የክፉዎች የጠላትነት ተግባር እንኳን ሳይቀር እናንተን ለሰማይ እንድትዘጋጁ በማድረጎ ወደ ሰረከት ይለወጥላችኋል፡፡ የክርስቶስ ከሆናችሁ› ‹ሁሉም ነገር የእናንተው ነው፡፡”እቃገ 9.2

    ያልተገባውን እንደተቀበለ በማሰብ የሚረካ፣ እንዲህ ያለውን የፍቅር ውለታ ለመመለስ እንደማይችል የሚሰማው፣ ጥርጣሬንና አላማመንን ወደ ጎን በማድረግ ህጻን በወላጆቹ ላይ በሚደገፍበት እምነት ወደ ኢየሱስ እግር የሚቀርብ የጌታን ሃብት በሙሉ በነጻ ይቀበላል፡፡እቃገ 9.3

    በረከትን ሁሉ የምንቀበለው በአንዱ ስጦታ በክርስቶስ በኩል ነው፡፡ በዚያ ስጦታም አማካኝነት በየዕለቱ የእግዚአብሔር መልካምነት እንደ ማያቋርጥ ጅረት ወደ እኛ ይፈሳል፡፡ እያንዳንዱ አበባ፣ በሚያስደምም ውሰቱ፣ በሚማርክ መዓዛው እንደሰትበት ዘንድ የተሰጠን ነው፡፡ ፀሐይና ጨረቃ በእርሱ የተፈጠሩ ናቸው፤ ሰማያትን ካስዋቡት ከዋክብት መካከልም እርሱ ያልፈጠረው የለም፡፡ በህይወት እንኖር ዘንድ እርሱ ካበረከተልን መብል ውጭ ሰማእዳችን ላይ የቀረበ አንዳች ነገር የለም፡፡ የክርስቶስም ስም በሁሉም ላይ ተጽፎበታል፡፡እቃገ 9.4

    አዳኙ ኢየሱስ ለተከታዮቹ፣ የዚህን ዓለም ቅንጦት እንደሚሰጣቸው ቃል አልገባላቸውም፤ እጣ ፈንታቸው ድህነት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ እንደሚያሟላላቸው ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ የእርሱ መገኘት ይዞልን የሚመጣውን ከምድራዊ ቁሳቁስ የሚበልጥ መጽናናት ሊሰጠንቃል ገብቶልናል፡፡እቃገ 10.1

    ክርስቶስ በጉዞአችን መጀመሪያና መጨረሻ ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዷ እርምጃችን ከእኛ ጋር ነው፡፡ ወላጆች ጆሮአቸውን የረሃብ ጩኸት ከሚያሰማው ልጃቸው ሊመልሱ ይችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የተቸገረችውን ነፍስ ጩኸት ፈጽሞ ቸል ሊል አይችልም፡፡እቃገ 10.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents