Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እምነታችሁን አጥታችኋልን?

    ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደ ተቀበላችሁት
    አድርጋችሁ ብታምኑ ይሆንላችኋል።
    ማር11፡24

    እምነት ካላችሁ በጸሎት የምትለምኑትን
    ሁሉ ትቀበላላችሁ፡፡
    ማቴ 212

    ጌታ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ደስተኛ፣ ሰላማዊና ታዛዦች እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡ በጌታ የሆኑትም በእምነት አማካኝነት እነዚህን ነገሮች መቀዳጀት ይችላሉ፡፡ በእምነት እያንዳንዱ የባህሪይ ጉደለት ሌስተካከል፣ እያንዳንዱ ርኩስት የጸዳ፣ እያንዳንዱ ስህተት ሊታረም፣ እንዲሁም እያንዳንዱ መልካም ባህሪይም ሊዳብር ይችላል፡፡እቃገ 53.1

    የምታገኙት ደስታ፣ ሰላምና ስኬት ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ባላችሁ እውነተኛ እምነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡እቃገ 53.2

    ከሰማይ ጋር የምንገናኘው ከጨለማውም ኃይላት ጋር ለመጋፈጥ የሚያስችለንን ብርታት የምናገኘው በእምነት ነው፡፡በክርስቶስ እግዚአብሔር እያንዳንዱን ክፉ አመል ለማሸነፍ፣የፈለገ ብርቱ ሲሆን እያንዳንዱን ፈተና ለመቋቋም የሚያስችል ኃይል ሰጥቶናል፡፡ ነገር ግን ብዙዎች እምነት እንደጎደላቸውና ከዚህም የተነሳ ከክርስቶስ መራቅ እንዳለባቸው ይሰማቸዋል፡፡ እነዚህ ነፍሳት ግን፣ ከነድካማቸው በሩህሩህ አዳኛቸው ምህረት ላይ የራሳቸዉን መጣል ይችላሉ። ወደ ክርስቶስ ተመልከቱ። በሰዎች መካከል ሲኖር ህሙማንን የፈወሰውና አጋንትን ያስወጣው ኃይሉ አዳኝ ዛሬም ከነሙሉ ጉልበቱ ነው።እምነት የሚመጣው ከእግዚአብሔር ቃል ነው።እቃገ 53.3

    እምነት በፊት ለፊት ከተጋረጠው ተራራ ባሻገር ያለውን ይመለከታል፤ የማይታየውን ሁሉን ቻይ ጌታን ይጠማጠማል፡፡ከዚህም የተነሳ በምንም መንገድ አይወድቅም፡፡ እምነት በእያንዳንዱ አደጋ ውስጥ የክርስቶስን እጅ መያዝ ነው፡፡ እምነትን ሰተግባር ከመለማመድ የበለጠ በፍጥነት የሚያጠነክረው ነገር የለም፡፡እቃገ 54.1

    እምነት እግዚአብሔር እንደሚወደንና ለእኛም የተሻለውን እንደሚያውቅልን መተማመንና በእርሱ ላይ መደገፍ ነው፡፡ከዚህም የተነሳ የእኛን መንገድ ወደ ጎን ትተን የእርሱን መንገድ ወደ መቀበል ይመራናል በእኛ አላማወቅ ፈንታ፣ የእርሱን ጥበብ እንቀበላለን፤ በእኛ ድካም ፈንታ፣ የእርሱን ብርታት እንወስዳለን! በእኛ በደል ፈንታ፣ የእርሱን ጽድቅ እንላበሳለን፡፡እምነት እያንዳንዱን ግድግዳ ደርምሶ የሚያልፍ፣ እንቅፋትን ሁሉ ዘሎ የሚሻገር፣ በጠላት ካምፕ መሃከል ላይ የድል አርማውን የሚተክል ህያው ኃይል ነው፡፡ በእርሱ ላይ ለሚታመኑት እግዚአብሔር አስደናቂን ነገር ያደርግላቸዋል፡፡ እምነታችንን የምናሳርፍበት በቂ ማስረጃ ሳይሰጠን እግዚአብሔር እንድናምን ፈጽሞ አይጠይቀንም፡፡ የእርሱ ህልውና፣ ባህሪይው፣ የቃሉ እውነተኛነት ሁሉ ሊያሳምነን በሚችሉ ምስክርነቶች ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ እነዚህም ምስክርነቶች በቂ ናቸው፡፡ ይህም ሆኖ ግን እግዚአብሔር የጥርጣሬን በር ሁሉ አይዘጋም፡፡ እቃገ 54.2

    እምነታችን በማስረጃዎች ላይ እንጂ በተገለጠ ነገር ላይ ማረፍ የለበትም፡፡ እውነትን ሊያውቁ የሚፈልጉ ሁሉ እምነታቸውን ለመመስረት የሚያስችሏቸው ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን መጠራጠር የማፈልጉም እድሉ አላቸው። እምነቱ ወደ ፈት የሚገሰግስ ሰው ፈጸኛ ኣይደክምም።ምንያቱም ወሰን የሰሹ የአምላክ ፍቅር ነገር ሁሉ የእርሱን መልካም ዓላማ ለማሳካት ተያይዞ እንዲሰራ ሲያደርግ ያያልና።እቃገ 55.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents