Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በሃዘን ተውጣችኋል?

    ሌሊቱን በለቅሶ ሲታደርም፣ በማለዳ ደስታ ይመጣል።
    መዝ 30፡5

    እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ሆን
    ይገባሉ፤ የዘላለማዊ ደስታን አክሊል ይቀዳጃሉ፤ ተድላና
    ደስታ ያገኛሉI ሐዘንና ልቅሶም ከእነርሱ ይሸሻል።
    ኢሳ 51፡11

    ሰማይ ሁሉ የሰውን ደስታ ለማየት ይመኛል፡ሰማያዊ አባታችንም ለፍጥረታቱ ደስታን ሊያመጣ የሚችልን የትኛውንም መንገድ አይዘጋም።እቃገ 17.1

    የራሳችን አድርገን ብንይዘው ደስታን ሊያመጣልን የሚችልን ማንኛውንም ነገር እግዚአብሔር ሊያስጥለን እንደሚፈልግ አድርገን ልናስብ አይገባም። እርሱ እንድንጥላው የሚጠይቀን ለራሳችን ይዘን ብናስቀረው መልካም የማይሆነውንና እውነተኛ ደስታ የማያመጣልንን ነገር ነው::እቃገ 17.2

    በሰቆቃ፣ በምሬትና በተሰበረ ልብ ተጨናልተን እንድንቀር እግዚአብሔር አይፈልግም:: ... ኦ፣ የተባረከው አዳኝ ዓይናቸው በእንባ ተሸፍኖ እርሱን ማየት ለተሳናቸው ብዙ ሰዎች አጠገብ “ቆሚል። ሰቀላል እምነት እርሱን ስንጠማጠመውና እንዲመራንም ስንማጸነው፣ እጃችንን አጥብቆ ለመያዝ ይናፍቃል፡፡ የአየሱስ መጽናናትና ሰላም ወደ ሕይወታችን እንዳገባ ብንፈቅድ፣ በታላቅ ፍቅር ወደ ተሞላው ልቡ እንጠጋለን።እቃገ 17.3

    ብዙዎች ሐዘንተኛት፣ ተስፋ የቆረጡና በመታመን የደከሙ ናቸው። ከእርስዎ ይልቅ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ያለን ሰው ለመርዳት አንድ ነገር ያድርጉ፡፡ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ብርታት እየጠነከሩ ያድጋሉ።እቃገ 18.1

    የየዕለቱ ሕይወት ችግሮችና ጭንቀቶች አዕምሮአችሁን እንዳያናውጡት እንዲሁም ግንባራችሁን እንዲያጨማድዳት አትፍቀዱ። የምትፈቅዱሳቸው ከሆነ ግን፣ ሁልጊዜ ለመናደድና ላመነፋት ምክንያት አታጡም: ሕይወት እኛ እንደምናደርጋትናት፧ ከሕይወት ምናገኘውም የምንፈልገውን ነው። ሐዘንንና ችግርን የምናሳድድ ከሆነ ብዙ እናገኛለን፤ ሃሳባችንንና ንግግራችንም በእነርሱ ይዋጣሉ፡፡ ነገር ግን የነገሮችን ብሩህ ጎን ብንመለከት፣ ደስተኛና ፈገግተኛ ሊያደርገን የሚችልን ሰቲ ነገር እናገኛ'ለን።እቃገ 18.2

    ኃላፊነታችንን ሚገባ ሰመወጣታችንና ለሌሎች ደስታ ማግኘት ምክንያት በመሆናችን ከምናገኘው እርካታ የተነሳ መላው ሰውነታችን አዲስ ሕይወትን ያገኛል። ክርስቶስን እንደ ቃሉ የሚቀበሉ፣ ነፍሳቸውን ለእርሱ ጥበቃ አሳልፈው የሚሰጡ፣ሕይወታቸውንም በእርሱ አመራር ስር የሚያደርጉ ሁሉ ሰላምና ፀጥታ ያሉ: ኢየሱስ በመገኘቱ የሚያጎናጽፋቸውን ደስታ ከዓለም የሆነ ምንም ነገር ሊሰርቃቸው አይችልም።እቃገ 18.3

    የእግዚአብሔር መንፈስ ልብን ሲቆጣጠር፣ ሕይወትን ይለውጣል፡፡ በኃጢአት የቆሸሱ አስተሳሰቦች ወደ ጎን ይደረጋሉ፡፡ሰነፋት የተሞሉ ድርጊቶች ይወገዳሉ፤ ፍቅር፣ ትህትናና ሰላም የቁጣን፣ የቅንአትንና የጥልን ስፍራ ይወስዳሉ። ደስታ የሐዘንን ስናራ ይወስዳል፤ የፊትም ገጽታ የሰማይን ብርሃን ያንጸባርቃል፧ሸክሙን የሚያንከባልላውን እጀ ወይንም ከሰማይ ዙፋን የሚወርደውን ብርሃን ማንም አያየውም: በረከት የሚመጣው ነፍስ በእምነት ራሷን ለእግዚአብሔር ስታስረክብ ነው። ደስተኛ መሆን የእግዚአብሔር ልጆች ተግባር ነው። ደስተኛ የሆነን አስተሳሰብ ሊያደፋፍሩ ይገባል፡፡ ዘወትር ሰሃዘን ጽልመት ተውጠውና በሄዱበት ሁሉ የሃዘንን ጥላ እያጠሉ ሰሚኖሩ ልጆቹ እግዚአብሔር ሊከብር አይችልም::እቃገ 18.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents