Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በኃጢኣት ከወደቃችሁ

    ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝና
    የሚተው ግን ምሕረትን ያገኛል።
    ምሳ 28፡13

    ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን፣
    ከአመጽም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው፡፡
    1 ዮሐ 1፡9

    የእግዚአብሔር ፍቅር ከእርሱ ለመለየት የመረጠን፣ እንደገና ወደ እርሱ ለማስጠጋት ይጓጓል፡፡ ወደ ቀድሞ ቤት ለመመለስ የተለያዩ ነገሮችን ያደርጋል፡፡ በአደጋ ውስጥ በወደቀች በእያንዳንዱ ነፍስ ዙሪያ ወርቃማው የመለኮት ፍቅር፣ የምህረትና የርህራሄ ሰንሰለት ይታሰራል፡፡እቃገ 32.1

    ሁላችንም ለስህተት የተጋለጥን ሟች ፍጥረታት እንደሆንንና ክርስቶስም ሰድክመታችን እንደሚያዝንልን ብንሳሳትም፣ እንኳን እንደሚወደን ሁልጊዜ በአዕምሮአችን መያዝ አለብን፡፡ ስለ ጉድለቶቻችንና ስህተቶቻችን አዘውትረን በኢየሱስ እግር ስር ሰመውደቅ ልናለቅስ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም፤ በእግዚአብሔር አልተተውንም፤ አልተጣልንም፤ ፊትም አልተነሳንምና፡፡እቃገ 32.2

    በጸሎት ቃሉን በማጥናት፣ በእርሱም ሀልዎት በማመን ደካማ የሆኑት ሰብአዊ ፍጥረታት ከህያው ክርስቶስ ጋር ተቆራኝተው መኖር ይችላሉ፤ እርሱም ፈጽሞ በማይለቅ እጁ ይይዛቸዋል፡፡ ከኃጢአት ጋር እስካልተስማማን ድረስ፣ በነፍሳችን ላይ ነቁጥ ሊያሳርፍ የሚችል ሰብአዊም ሆነ ሰይጣናዊ ኃይል የለም፡፡እቃገ 32.3

    ከክፋት ልንጠበቅ የምንችልበት ብቸኛው መከላከያ በእምነት በልባችን ያለው የክርስቶስ ጽድቅ በቻ ነው፡፡ ብዙ መጥፎ ልማዶቻችንን ለመተው እንሞክር ይሆናል፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ከሰይጣን ጋር ልንለያይ እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን በየቅጽበቱ ራሳችንን ለእርሱ በማስረከሰ ከእግዚአብሔር ጋር ህያው ግንኙነት ከሌለን እንረታለን፡፡ ከክርስቶስ ጋር የግል ትውውቅ ከሌላን ቋሚ የሆነም ግንኙነት የማናደርግ ከሆነ በጠላት እጅ ውስጥ እንወድቃለን፡፡ በመጨረሻም የእርሱን ፈቃድ በመፈጸም እንጨርሳለን፡፡እቃገ 33.1

    በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝ ሰው፣ በክርስቶስ ላይ አተኩሮ ከመመልከት ላቅጽበት ዓይኑን ሲነቅልና ከትክክለኛው መንገድ ሲስት፣ ኃጢአት የሰራው በእቅድ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ስህተቱን በተረዳ ጊዜ እንደገና ይመለሳል፤ ዳግም በኢየሱስ ላይ ዓይኖቹን ይተክላል፡፡ በስህተት ውስጥ መውደቁ ግን እግዚአብሔር ለእርሱ ያለውን ፍቅር እንዲቀዘቅዝ አያደርገውም፡፡ ባለማወቃችን ምክንያት ተደናቅፈን ብንወድቅ ክርስቶስ አይተወንም፡፡እቃገ 33.2

    ክርስቶስ ከኃጢዓአት ነጻ ሊያወጣን ዝግጁ ነው፤ ነገር ግን ፈቃዳችንን በጉልበት አይጫንም፡፡ እናም ፈቃዳችንን ወደ ክፋት ሙሉ ለሙሉ በማዘንበል ከጸናንና ነጻ ለመውጣት ፍላጎታችን ካልሆነ፣ ጸጋውንም ለመቀበል ፈቃደኞች ካልሆንን እርሱ ከዚህ ውጪ ምን ሊያደርግልን ይችላል? የእርሱን ፍቅር በፈቃዳችን በመቃወም ራሳችንን ለጥፋት እንዳርጋለን። እቃገ 33.3

    ብዙዎች በህይወት መንገድ ላይ ሲጓዙ ስህተታቸውንና ውድቀታቸውን ሁልጊዜ በማሰብ ልባቸው በሃዘንና በተስፋ መቁረጥ የተሞላ ነው፡፡ ... ካላፈው የህይወታችን መዝገብ ደስ የማይሉትን የኃጢአትና የተስፋ መቁረጥ ትዝታዎች ዳግም መሰብሰብ፣ እንደገና በተስፋ መቁረጥ እስክንጥለቀላቅ ድረስ ስለእነርሱ ማውራትና ማልቀስ በጥበብ የተሞላ ድርጊት አይደለም፡፡ ተስፋ የቆረጠች ነፍስ ራስዋን ከአምላክ ብርሃን ሰማራቅ በጽልመት የተዋጠችና በሌሎችም መንገድ ላይ ጥላ የምታጠላ ናት፡፡እቃገ 34.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents