Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሸክማችሁ ከአቅም በላይ ሆኖባችኋል?

    ... ከተጸነሳችሁ ጊዜ ጀምሮ የያዝኋችሁ’ ከተወለዳችሁ
    ጊዜ ጀምሮ የተሸከምኋችሁ ስሙኝ፡፡
    እስከ ሽምግልናችሁ፣ እስከ ብትም፣ የምሸከማችሁ እኔ
    ነኝ እኔው ነኝ፡፡ ሠርቻችኋለሁ፤ እሸከማችኋለሁ፤
    እደግፋችኋለሁ፤ አድናችኋለሁ፡፡
    ኢሳ 46፡4

    ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣
    አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ ይባረክ፡፡
    መዝ 88፡19

    በመከራዎቻችን ሁሉ ውስጥ ስናልፍ ፈጽሞ የማያሳፍረን በዳት አላን፡ ለብቻትን ከፈተናዎች ጋር እንድንታገል፣ ከክፋት ጋር እንድንዋጋና በመጨረሻም በሽክሞቻችንና በ ሃዘኖቻችን ክብደት እንድንጨፈለቅ አይተወንም።እቃገ 14.1

    ፍላጎታችሁን፣ ደስታችሁን፣ ሃዘናችሁን፣ ጭንቀታችሁንና ፍርሃታችሁን ሁሉ ለእግዚአብሔር አሳውቁ። በስማችሁ ብዛት ልታጨናንቁተ ወይም ልታደክሙት አትችሉም። የራስ ጸጉራችሁን በቁጥር የሚያውቀው እርሱ፣ ለልጆቹ ፍላጎት ግድየለሽ አይደለም፡፡ ጌታ ሩህሩህና መሐሪ ነው::” አፍቃሪ ልቡ ሰሰቆቃችሁና በምሬታችሁ ይነካል። አእምሮአችሁን የሚያስጨንቀውን ነገር ሁሉ ወደ እርሱ ይዛችሁት ቅረቡ። እርሱ ሊሸከመው የማይችለው ከባድ ሸክም የለም። ዓላማትን ሁሉ የተሸከመ በዩንቨርስ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ የሚያስተዳደር እርሱ ነውና፡፡ የእኛን ሰላም የሚያደፈርስ ማንኛውም ነገር በእርሱ ዘንድ በቀላሉ አይታይም:: በጽልመት ከመዋጡ የተነሳ እርሱ ሊያነበው የማይችል የህይወት ምዕራፍ የላችሁም:: እርሱ ሊፈታው የማይችል ምንም አይነት የተወሳሰሰ ነገር የለም፡፡የሰማዩ አባታችን የማይሰማውና ትኩረቱንም የማይስበው እውነተኛ ጸሎት የለም፡፡እቃገ 14.2

    ጭንቀታችሁና መከራችሁ ምንም ቢሆን ምን ጉዳያችሁን በጌታ ፈት ዘርጉት:: መንፈሳችሁ በጽናት አጥር ይታጠራል።መንገዱም ለእናንተ ይከፈታል። ደካማና ረዳተሲስ እንደሆናችሁ አብልጦ በተሰማችሁ መጠን፣ በዚያው ልክ በእርሱ ብርታት ትጠነክሪላችሁ:: ስነምን ሁሉ ሰሚሸከመው በእርሱ ላይ ጭነታችሁን ሰምታኖሩት ጊዜ፣ የሚሰማችሁም እረፍት በሽክማችሁ ክብደት ትልቅነት ልክ ታላቅ ይሆናል፡፡እቃገ 15.1

    ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች እንደሚያጋጥሙን እሙን ነው; ስደትን መጠባበቅ አለብን፥ ነገር ግን ትልቅም ይሁን ትንሽ ሁሉንም ለእግዚአብሔር ማስረከብ ያስፈልገናል፡፡ እርሱ በምሬታችን ብዛት አይደናገርም፧ በሽክማችንም ክብደት አይዘረርም። የእርሱ ጥበቃ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ይዘረጋል፤ሁሉንም ሰው ይከባል; ስለ እያንዳንዱ ጉዳያችንና ሰቆቃችን ግድይለዋል። እያንዳንዱን የእንባ ጠብታ ልብ ይላታል፤ በድካም ስሜታችን ስሜቱን ይነካል፡ ስቃያችንና መከራዎቻችን ሁሉ ለእኛ ያለውን የእርሱን የፍቅር ዓላማ ለማሳካት ተፈቅዶላቸው የመጡብን ናቸው::እቃገ 15.2

    በየዕለቱ፣ እንዲሁም በየሰዓቱ ሰኢየሱስ መታመን ያስፈልገናል፥ እርሱ የሚያስፈልገንን ብርታት ሊሰጠን ቃል ገብቶልናል፡፡ በእርሱ ጸጋ የወቅቱን ሽክሞቻችንን ሁሉ መሸከምና ግዴታዎቻችንንም መወጣት እንችላለን፡፡ ነገር ግን ብዙዎች የጎበጡት ስለወደፊቱ ችግር ከወዲሁ በማሰብና በመጨነቅ ነው።እነርሱም የነገን ሽም ወደ ዛሬ ጎትተው ለማምጣት ብዙ ይጥራሉ። ከዚህም የተነሳ አብዛኛው የመከራቸው ክፍል ሃሳባዊ ነው። የነገን ጭንቀት ዛሬ ለመሸከም ደግሞ ጌታ ያዘጋጀው ምንም ኃይል የለም። እርሱ ቃል የገባው ለቀኑ የሚበቃን ጸጋ ለመስጠት ነው።እቃገ 15.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents