Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 4 - ኃጢያትን መናዘዝ

    ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝና የሚተው ግን ምህረትን ያገኛል» (ምሳ. 28፡13) ከእግዚአብሔር ምህረትን የማግኛው መንገድ ቀላልና ቀና ብቻ ሳይሆን ለማገናዘብም አስቸጋሪ አይደለም፡፡ ለኃጢአታች ይቅርታ እናገኝ ዘንድ ከባድና ራሳችንን የሚጎዳ ነገር እንድናደርግ ጌታ አይፈልግብንም:: መተላለፋችን እንዲደመሰስና ነፍሳችንን ለሰማይ አምላክ አደራ ለመስጠት ረጅምና አድካሚ የምናኔ ጉዞ ማድረግ ወይም ህመም ያለው የንስሐ ቅጣት መቀበል አያሻንም፡፡ ነገር ግን ኃጢአቱን የተናዘዘ ጠተዋትም ምህረትን ያገኛል፡፡ክየመ 35.1

    በዚህ ዙሪያ ሐዋርያው «ስለዚህ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ» (ያዕ. 5:16 በማለት ይናገራል፡፡ኃጢአታችሁን ሁሉ ይቅር ሊል ለሚችለው ለእግዚአብሔር ብቻ ተናዘዙ፤ስህተታችሁንም እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ፡፡ ጓደኛችሁን ወይም ጎረቤታችሁን ቅር ብታሰኙ ጥፋታችሁን አምናችሁ ተቀበሉ:: የበደላችሁትም ሰው በነጻ ይቅር ሊላችሁ ይገባዋል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ይቅር ይላችሁ ዘንድ ለምኑት:: ምክንያቱም ያ ያቆሰላችሁት ወንድም የእግዚአብሔር ንብረት በመሆኑ እርሱን በመጉዳታችሁ ፈጣሪ እና አዳኝ የሆነው ጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርታችኋል፡፡ ጉዳዩ የሚቀርበው ብቸኛና እውነተኛ አማላጅ የሆነው ሊቀ ካህናችን ፊት ሲሆን እርሱም «እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ይሁን እንጂ ምንም ኃጢአት አልሠራም» (ዕብ. 4:15)፡፡ክየመ 35.2

    እርሱ እያንዳንዱን የኃጢአት ጉድፍ ለማንጻት ይቻለዋል፡፡ መተ ላለፋቸውን በማሳወቅ ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት በትህትና ዝቅ አድርገው ያላቀረቡት፣ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ለማግኘት ገና ይቀራቸዋል፡፡ ንስሓ መግባት ስላለብን ነገር፣ ንስሓ መግባት ካልተ ለማመድን፣ በእውነተኛው መንገድ ነፍሳችንን ካላዋረድንና በተሰበረ መንፈስ ኃጢአታችንን ካልተናዘዝን መተላለፋችን በእውነት ይቅር ይባል ዘንድ አንፈልግም ማለት ነው:: እንዲህ ከሆነ ደግሞ የእግዚአብሔርን ሰላም ለማግኘት ፈጽሞ አንችልም፡፡ የኃጢአት ይቅርታ ለማግኘት ያልቻልንበት ብቸኛው ምክንያት ልባችንን በትህትና ለእግዚአብሔር ዝቅ ለማድረግ ፈቃደኞች አለመሆናችንና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር መስማማት አለመቻላችን ነው:: እርሱ ይህን አስመልክቶ ግልጽ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ በግልም ሆነ በሕብረት ኃጢአታችንን ስንናዘዝ ሳለ ከልብ በመነጨ እና በነፃነት መንፈስ ልናደርገው ይገባል እንጂ በግፊት መሆን የለበትም:: ከልብ የሚደረግ ንስሐ ርኅራኄው ወደማያልቅበት አምላክ በቀጥታ ያመራል፡፡ ይህንንም አስመልክቶ ባለ መዝሙሩ እንዲህ ይላል «እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል» (መዝ. 34፡18)፡፡ክየመ 35.3

    እውነተኛ ኑዛዜ ሁል ጊዜ ጠቅለል ተደርጎ የሚቀርብ ሳይሆን እያንዳንዷን ኃጢአት በዝርዝር ማውሳትን ይጠይቃል፡፡ ምናልባትም የሠራነው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ብቻ መቅረብ ያለበት ሊሆን ይችላል፡፡ ሰውን ጎድተን ከሆነ ወደዚያ ሰው ቀርበን ድርጊታችንን ማመን ተገቢ ነው በሕዝብ ፊት መናዘዝ የሚያስፈልገው ኃጢአት ሠርተንም ከሆነ መድረክ ላይ መናዘዝ ይጠበቅብናል፡፡ ይሁን እንጂ የትኛውም አይነት ኑዛዜ ግልጽና ቀጥተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ በደለኛ የሆንበት ጥፋት የቱ እንደሆነ የሚገልጽ መሆን አለበት።ክየመ 36.1

    ለኃጢአታችን ይቅርታ እናገኝ ዘንድ ከባድና ራሳችንን የሚጎዳ ነገር እንድናደርግ ጌታ አይፈልግብንም፡፡

    በሳሙኤል ዘመን የእስራኤል ልጆች ከእግዚአብሔር መንገድ ተቅበዝብዘው በመውጣታቸው በእርሱ ላይ የነበራቸውን እምነት አጡ፡፡ ይህን ተከትሎም ኃጢአት ባመጣው መዘዝ ይሰቃዩ ጀመር፡፡ ክፉና ደጉን ለመለየት የሚያስችላቸውን የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ ያጡት እነዚህ ሕዝቦች፤ ከታላቁ የዩኒቨርስ ገዢ ፊታቸውን በማዞር በአካባቢያቸው እንደነበሩት አሕዛብ ሊገዙ ተመኙ፡፡ እስራኤላውያኑ ሰላም ከማግኘታቸው አስቀድሞ «ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ጥፋት አደረግን» (1ኛ ሳሙ. 12:19) በማለት ግልፅ ኃጢያታቸውን ተናዘዙ፡፡ የሰሩትን ኃጢያት ስሙን በመጥቀስ መናዘዝ ነበረባቸው፡፡ የእነዚህ ሕዝቦች ምስጋናቢስነት የገዛ ነፍሳቸውን ደቆሰው፣ ከእግዚአብሔርም ለያቸው።ክየመ 36.2

    ኃጢአትን መናዘዝ ከልብ የመነጨ መጸጸትና መለወጥ ከሌለው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በሕይወት ውስጥ ለውጦች እንዲመጡ በመወሰን እያንዳንዱ ለእግዚአብሔር አጸያፊ የሆነው ነገር መወገድ ይኖርበታል፡፡ ይህም በእውነት ስለ ኃጢታችን የማዘናችን ውጤት ይሆናል፡፡ በእኛ በኩል ምን ማድረግ እንዳለብን ግልጽ ሆኖ ተቀምጦአል «ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትህን እሹ፤ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ» (ኢሳ. 1፡16 17)፡፡ «ለሰጠው ብድር የተቀበለውን መያዣ ቢመልስ፣ የሰረቀውንም መልሶ ቢሰጥ፣ ሕይወት የሚሰጡትን ትእዛዛት ቢከተል፣ ክፉ ነገርንም ባያደርግ፣በእርግጥ እርሱ በሕይወት ይኖራል፤ አይሞትምም» (ሕዝ. 33:15)።ጳውሎስ ስለ ንስሓ ሲናገር «ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነው ሐዘን እንዴት ያለ ትጋት፤ እንዴት ያለ መልስ የመስጠት ችሎታ፣ እንዴት ያለ ቁጣ፣ እንዴት ያለ ፍርሃት፣ እንዴት ያለ ናፍቆት፣ እንዴት ያለ በጎ ቅናት፣እንዴት ያለ ተግሳጽ እንዳስገኘላችሁ ተመልከቱ፡፡ በዚህም ጉዳይ ንጹሃን መሆናችሁን በሁሉ ረገድ አስመስክራችኋል» (2ኛ ቆሮ. 7:11)።ክየመ 37.1

    ኃጢአት ግብረገባዊውን አመለካከት ሙት በሚያደርገው ጊዜ በደለኛው የባህሪውን ጉድለት ለይቶ መመልከት አይችልም ወይም የሠራው ክፋት ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ መገንዘብ ይቸግረዋል:: ጥፋተኝነቱን ሊያመላክተ ው ለሚችለው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል መንገድ ካልከፈተ በቀር በከፊል ታውሮ ኃጢአቱን ሳያይ ይቀራል፡፡ የእንዲህ ዓይነቱ ግለሰብ ንስሐ ከልብ የመነጨና ፅኑ ዓላማ ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ «ይህ ባይደርስብኝ ኖሮ እንዲህ ባላረኩ ነበር» በማለት ለሠራው ስህተትና ለኃጢአቱ ሁሉ ምክንያት ይደረድራል፡፡ክየመ 37.2

    አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ ከበሉ በኋላ በፍርሃትና በሐፍረት ስሜት ተዋጡ፡፡ በመጀመሪያ ወደ አዕምሮአቸው የመጣው ሃሳብ፣ ለሠሩት ኃጢአት ምክንያት በማቅረብ ከአስከፊው የሞት ቅጣት ማምለጥ የሚችሉበትን መንገድ መቀየስ ነበር፡፡ የሠሩትን ኃጢአት አስመልክቶ እግዚአብሔር ጥያቄ ባቀረበላቸው ጊዜ አዳም ሲመልስ ለኃጢአቱ በከፊል ተጠያቂ ያደረገው እራሱን እግዚአብሔርን በከፊል ደግሞ ረዳቱን ነበር «ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት፤ እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ» (ዘፍ. 3:12)፡፡ ሴቲቱ ደግሞ በእባቡ በማመካኘት እባብ አሳተኝና በላሁ» (ዘፍ. 3:13) ስትል መልስ ሰጠች:: ሔዋን ለኃጢአቷ የሰጠችው ምክንያት «እባቡን ለምን ፈጠርክ? ለምንስ ወደ ገነት ይመጣ ዘንድ ፈቀድክለት?» የሚል ጥያቄ ያዘለ ሲሆን በዚህም በኃጢአት መውደቃቸው እግዚአብሔርን ተጠያቂ ሲያደርጉት ይስተዋላሉ፡፡ እራስን ፃድቅ አድርጎ የማቅረብ መንፈስ በመጀመሪያ የተጠነሰሰው በሐሰት አባት ልብ ውስጥ ሲሆን፤ ከዚያም በሁሉም የአዳም ወንድና ሴት ልጆች በጉልህ ለመታየት ቻለ፡፡ ይህ ዓይነቱ የኃጢአት ኑዛዜ ከመለኮታዊው መንፈስ ምሪት አይመነጭም በእግዚአብሔርም አዳምና ሔዋን ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡እውነተኛ ንስሐ ሰው የራሱን ስህተት ያለ ምንም ማታለልና ግብዝነት አምኖ ይቀበል ዘንድ ይመራል፡፡ ልክ እንደዚያ ዓይኑን እንኳን ወደ ሰማይ ለማንሳት እንዳልደፈረው ምስኪን ቀረጥ ሰብሳቢ «እግዚአብሔር አምላክ ሆይ እኔን ኃጢአተኛውን ይቅር በል» በማለት የልቅሶን ድምፅ ያሰማል፡፡ ንስሓ ለገባችው ነፍስ ክርስቶስ በደሙ ልመና ስለሚያቀርብላት እነሆ ስህተቱን አምኖ የሚቀበል ሁሉ ይጸድቃል።ክየመ 38.1

    አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ ከበሉ በኋላ በፍርሃትና በሐፍረት ስሜት ተዋጡ።

    በእግዚአብሔር ቃል ላይ በምሳሌ የቀረበው ከልብ የመነጨ ንስሐና እራስን ማዋረድ ለኃጢአት አንዳችም ምክንያት ለመስጠት የማይሞክሩበትን ወይም እራስን ጻድቅ የማያደርጉበትን የኑዛዜ መንፈስ ይገልጽልናል::ጳውሎስ ላደረገው ጥፋት ምክንያት በመደርደር እራሱን ለመከላከል አልፈለገም፤ ነገር ግን መተላለፉን ሳያሳንስ እንዳለ በጥቁር ቀለም አሰፈረው «ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተቀብዬ ብዙ ቅዱሳንን አሳስሬአለሁ፤በመገደላቸውም ተስማምቼአለሁ፤ ላስቀጣቸውም ብዙ ጊዜ ከምኩራብ ምኩራብ እየተዘዋወርሁ፣ የስድብ ቃል እንዲናገሩ አስገድዳቸው ነበር፤ በቁጣም ተሞልቼ በውጭ አገር እስከሚገኙ ከተሞች ድረስ ተከታትዬ አሳደድኋቸው» (ሐዋ. 26፡10-11)፡፡ ሐዋርያው እንዲህ ብሎ ከማወጅም ወደ ኋላ አላለም «ክርስቶስ ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኃጢያተኞችም ዋና እኔ ነኝ» (1ኛ ጢሞ. 1፡15)፡፡ክየመ 39.1

    በእውነተኛ ንስሐ ስር የሚገዛው ትህትናን የተላበሰውና የተሰበረው ልብ፤ለእግዚአብሔር ፍቅር እና ለከበረው ቀራኒዮ ያለውን አድናቆት ይቸራል፡፡ልጅ ለአፍቃሪው ወላጅ አባቱ ስህተቱን እንደሚያስታውቅ ሁሉ በእውነት ንስሐ የሚገባውም ሰው ኃጢአቱን በሙሉ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል «ኃጢአታችንን ብንናዘዝ፤ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመጻ ሁሉ ሊያነፃን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው::› (1ኛ ዮሐ. 1:9)፡፡ክየመ 39.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents