Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 13 - በጌታ መደሰት

    በእግዚአብሔር ልጆች የተጠሩት የክርስቶስ ወኪሎች በመሆን የጌታን በጎነት እና ቸርነት እንዲያሳዩ ነው:: ክርስቶስ እውነተኛውን የአብን ባሕርይ ለእኛ እንደገለፀልን እኛ ደግሞ ርህራሄውንና አዛኝ ፍቅሩን ለማያውቀው ዓለም ክርስቶስን ልንገልጽ ይገባናል፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሎአል፡- «ወደ ዓለም እንደላክኸኝ እኔ ደግሞ እነርሱን ወደ ዓለም ልኬያቸዋለሁ» እንደዚሁም «እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን . . . በዚህም ዓለም አንተ እንደላክኸኝ ያውቃል፡፡» (ዮሐ. 17፡18፣23)፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለኢየሱስ ደቀ መዛሙርት «ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልዕክታችን ናችሁ» «የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው» (2ኛ ቆሮ. 3:2-3) ይላል፡፡ ኢየሱስ በእያንዳንዱ ልጁ በኩል ወደ ዓለም ደብዳቤ ልኳል፡፡ እናንተ የክርስቶስ ተከታዮች ከሆናችሁ በእናንተ ወደየቤተሰቦቻችሁ፣ መንደሮቻችሁ፣ ጎዳናዎች እና የምትኖሩበት ቦታ ሁሉ ደብዳቤ ልኳል ማለት ነው:: በእናንተ የሚኖረው ኢየሱስ፣ ከእርሱ ጋር ላልተዋወቁ ሰዎች ልብ በአኗኗራችሁ በኩል መናገር ይፈልጋል፡፡ምናልባትም እነዚህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አላነበቡም ይሆናል ወይም አንብበውትም እንኳን በየገፁ ለልባቸው የሚጮኸውን ድምፅ አልሰሙም ይሆናል፤ የእግዚአብሔር ፍቅር ሲሰራም አላስተዋሉትም ይሆናል፡፡ እናንተ ግን የኢየሱስ እውነተኛ ወኪል ከሆናችሁ፣ እነዚህ ሰዎች የእርሱን በጎነት በእናንተ በኩል በመረዳት ለፍቅሩና ለአገልግሎቱ እጃቸውን ይሰጣሉ፡፡ክየመ 111.1

    ክርስቲያኖች ለመንግስተ ሰማይ መንገድ ብርሃን አብሪዎች ናቸው፡፡ ከክርስቶስ የሚመነጨውና በእነርሱ ላይ የሚያበራው ብርሃን አንፀባራቂዎች ናቸው:: ሕይወታቸውና ባሕርያቸው ለሌሎች ስለክርስቶስና አገልግሎቱ ትክክለኛውን አመለካከት የሚያስጨብጡ ሊሆኑ ይገባል፡፡ክየመ 111.2

    እኛ ክርስቶስን የምንወክል ከሆንን፣ አገልግሎቱን ማራኪ አድርገን ልናቀርበው ይገባል፤ በእርግጥም ማራኪ ነውና፡፡ ክርስቲያኖች ወደ ነፍሳቸው ጭጋግና ሀዘን፣ ማጉረምረም እና ምሬት የሚሰበስቡ ከሆነ ለሌሎች ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ክርስትና ሕይወት የተሳሳተ ስዕልን ያሳያሉ፡፡ ልጆቹ ደስተኞች በመሆናቸው እግዚአብሔር ደስ የማይሰኝ እንደሆነ በማስመሰል ለሰማያዊ አባታችንም አሉታዊ ምስክር ይሆናሉ፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሔር ልጆችን ከእምነታቸው ፈቀቅ ሲያደርጋቸውና በሐዘን ፊታቸውን ሲያጠቁረው ይከብራል፡፡ እንደዚሁም እግዚአብሔርን ስንክድ፣ የማዳን ኃይሉን እና ፈቃዱን ስንጠራጠረው ሰይጣን ይፈነድቃል፡፡ክየመ 112.1

    ሰይጣን ጌታ በሚሰጠን ነገሮች እንደተጎዳን ስናስብ ደስ ይለዋል፡፡ ጌታን፣ፍቅር እና ርህራሄ እንደሌለው አድርጎ ማቅረብም የሰይጣን ሥራ ነው።ሰይጣን ስለ እግዚአብሔር የተጻፈውን እውነት ያጣምማል፣ አእምሮአችንንም በተሳሳተ ሃሳብ መሙላት ይፈልጋል፡፡ ስለ ሰማያዊው አባታችን እውነት የሆነውን ከማሰብ ይልቅ እኛም ብዙውን ጊዜ በሰይጣን ውሽት አእምሮአችንን እንሞላና እርሱን ባለማመን እና በእርሱም ላይ በማጉረምረም እግዚአብሔርን እናዋርደዋለን፡፡ ሰይጣን ሁል ጊዜ የሚፈልገው ነገር የክርስትና ሕይወት የሃዘን ጥላ ያጠላበት እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ ነው። አድካሚና አሰልቺ እንዲመስልም ይጥራል።ክርስቲያንም በሕይወቱ እንዲህ ዓይነቱን የኃይማኖት ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ እምነት በጎደለው ድርጊቱ ለሰይጣን ውሽት የድጋፍ እጁን ያወጣል።ክየመ 112.2

    በክርስትና ሕይወታቸው ብዙዎች ትኩረታቸውን በስህተታቸው፣ በውድቀታቸው፣ በሀዘናቸው፣ በልባቸው ውስጥ በሞላ ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ ላይ ያኖራሉ፡፡ አንድ ጊዜ አውሮጳ ውስጥ እያለሁ በእንደዚህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ ትኖር የነበረችና ጥልቅ በሆነ ድብርት የተዋጠች እህት ጥቂት የማፅናኛ ቃል እንድልክላት ደብዳቤ ፃፈችልኝ።ያን ደብዳቤ ባነበብኩበት ሌሊት በሕልሜ በአንድ የአትክልት ሥፍራ፣ የአትክልት ስፍራው ባለቤት ከሚመስል ሰው ጋር እመላለስ ነበር፡፡ አበቦችን እየሰበሰብኩ እና በመልካም መዓዛቸው እየተደሰትኩ ባለሁበት በዚያ ሌሊት ትኩረቴ ከጎኔ ስፍራው ባለቤት ከሚመስል ሰው ጋር እመላለስ ነበር፡፡ አበቦችን እየሰበሰብኩ እና በመልካም መዓዛቸው እየተደሰትኩ ባለሁበት በዚያ ሌሊት ትኩረቴ ከጎኔ ትጓዝ የነበረችውን ይህቺን እህት ወዳሰናከላት አንድ የማይታይ እንቅፋት ላይ አረፈ። በእዚያ ቦታ ላይ እርሷ ታዝንና ትተክዝም ነበር፡፡ በትክክለኛው መንገድ ይመራት የበረውን መሪ መከተሏን ትታ በእሾህ እና አሜኬላ መካከል ትጓዝ ነበር፡፡ እያለችም ታዝን ነበር፡፡ «ወይኔ ይህ የሚያምር የአትክልት ስፍራ በእሾሆች ሲበከል አያሳዝንም? » መንገድ ይመራ የነበረውም፡- «እሾሆቹ ስለሚያቆስሉሽ እነርሱን ተያቸውና ጽጌሬዳዎቹን እና ሌሎቹን አበቦች ብቻ ሰብስቢ» አላት፡፡ክየመ 112.3

    እንዲህ «እሸሆቹ ስስሚያቆስሉስ እነርሱን ተያቸውና ጽጌሬዳዎቹን አና ሌሎቹን አበቦች ብቻ ሰብስቢ»።

    በሕይወታችሁ እጅግ የተደሰታችሁበት ጊዜ የለም? የብርሃን ፍንጣቂ የነበረበት ጊዜ የለምን? ለእግዚአብሔር መንፈስ መልስ በመስጠት ልባችሁ በደስታ የተፍለቀለቀበት ጊዜ አልነበረም? የሕይወታችሁን ምዕራፎች ዘወር ብላችሁ ባያችሁ ጊዜ ጥቂት አስደሳች ጊዜያት የሉምን? የእግዚአብሔር ቃል ኪዳኖች በመንገዳችሁ ላይ በሁሉም አቅጣጫ እንደ አበባ መዓዛ አይደሉም? ውበታቸው እና ጣፋጭነታቸው ልባችሁን በደስታ እንዲሞላው አትፈቅዱላቸውምን?ክየመ 113.1

    እሾህ እና አሜኬላዎች ያቆስሏችሁና ያሳዝኗችሁ ይሆናል፡፡ እነዚህን ብቻ እየለቀማችሁ ለሌሎች የምትሰጧቸው ከሆነ የእግዚአብሔርን መልካምነት ዝቅ ከማድረጋችሁ ያለፈ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰዎች በእውነተኛው የሕይወት ጎዳና እንዳይሄዱ መከልከላችሁ አይደለምን?ክየመ 113.2

    ያለፈ ሕይወታችንን ደስ የማያሰኙ የኃጢአትና የተስፋ መቁረጥ ትዝታ ዎች እያነሳን በሽንፈት እስክንዘረር ድረስ ስለ እነርሱ ደጋግሞ ማውራትና ማለቃቀስ ብልህነት አይደለም፡፡ ተስፋ የቆረጠች ነፍስ በጨለማ የተሞላች፣ለእግዚአብሔር ብርሃን ራሷን የዘጋችና በሌሎች ሕይወት ላይ ጥላን ያጠላች ናት፡፡ክየመ 113.3

    እግዚአብሔር ለእኛ ስለገለፀው ብሩህ ምስል የተመሰገነ ይሁን፡፡የእግዚአብሔር ፍቅር ማረጋገጫ የሆኑትን በረከቶች ካለማቋረጥ እናስታውሳቸው። እኛን ከሰይጣን ኃይል ለመታደግ ሲል የእግዚአብሔር ልጅ የአባቱን ዙፋን ለቅቆ መለኮታዊ ማንነቱን በሰብአዊነት ሸፈነ፡፡ በእኛ ምትክ ድልን በመቀዳጀት ሰማይን ከፈተልን፤ ክብሩንም አሳየን፡፡ ሰብአዊ ዘር ሁሉ ተወርውሮ ከነበረበት ከኃጢያት አዘቅት በማውጣት እንደገና ወደ ዘለዓለማዊ አምላክ ህብረት መለሰን፡፡ በአዳኛችን ላይ በመታመን ፈተናን በማሸነፍ፣ የክርስቶስን ጽድቅ በመልበስ ወደ ዙፋኑ ከፍ አደረገን፡፡ክየመ 114.1

    እግዚአብሔር እንድናሰላስል የሚፈልገው እንደዚህ ያሉትን የተዋቡ ስዕሎች ነው። የእግዚአብሔርን ፍቅር ስንጠራጠርና ቃል ኪዳኑን ሳናምን ስንቀር እርሱን እናዋርደዋለን፧ ቅዱስ መንፈሱን እናሳዝናለን፡፡ ሕይወቷን በሙሉ የልጆችዋን ፍላጎት ለማሟላትና ለእነርሱ ምቾት ለሰዋች አንዲት እናት፣ ልጆቿ ያደረገችውን ነገር ሁሉ ከምንም ሳይቆጥሩ ያለማቋረጥ ቢያማርራት ምን ይሰማታል? ፍቅሯን ተጠራጠሩት እንበል፣ ይህ ታዲያ መንፈሷን አይሰብረውምን? ልጆቹ ለአባታቸው ያለው ምላሽ እንደዚህ ከሆነ የአባታቸው ስሜት ምን አይነት ይሆን? ታዲያ ሰማያዊ አባታችን እኛ ሕይወት እንዲኖረን አንድያ ልጁን እስኪሰጠን ድረስ ያስገደደውን ፍቅሩን ስናጣጥል ምን ይሰማው ይሆን? (ሐዋርያው በሮሜ 8፡32 ላይ «ለገዛ የሰጠው፣ ከክርስቶስ ጋር ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለሁላችን ደግሞ ሁሉንም ነገር ደግሞ ሁሉንም ነገር እንዴት አይሰጠንም!» ሲል ፍቅሩን ስናጣጥል ምን ይሰማው ይሆን?( ሐዋርያው በሮሜ 8፡32 ላይ «ለገዛ የሰጠው፣ ከክርስቶስ ጋር ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለሁላችን ደግሞ ሁሉንም ነገር ደግሞ ሁሉንም ነገር እንዴት አይሰጠንም!» ሲል ጽፏል፡፡ ይህ የተስፋ ቃል ቢሰጣቸውም ስንቶች ናቸው በድርጊታቸው አልፎም በቃላቸው «ለእኔ ጌታ እንዲህ አይደለም፡፡ ምናልባት ሌሎችን ይወድ ይሆናል፡፡ እኔን ግን አይወደኝም፡፡» የሚሉ፡፡ክየመ 114.2

    «ለገዛልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለሁላችን አሳልፎ አሳልፎ የሰጠው፣ ከክርስቶስ ጋር አንዴት አይሰጠንም?»

    እንደዚህ አይነት ሃሳቦች ካሉን ራሳችንን ነው የምንጎዳው፡፡ ከአፋችን የሚወጣው እያንዳንዱ የጥርጣሬ ቃል ለሰይጣን ፈተና ይዳርገናል፡፡ ይህ ነገር የበለጠ ተጠራጣሪዎች እንድንሆን ያደርገናል፣ አገልጋይ መላእክትንም ከእኛ በኃዘን እንዲለዩ ያደርጋል:: ሰይጣን በሚፈትናችሁ ጊዜ የጥርጣሬ ወይም የጭለማን ነገር ትንፍሽ አትበሉ:: የልባችሁ በር ለሰይጣን ምክር የተከፈተ ከሆነ አዕምሯችሁ በጥርጣሬና በአመፅ ጥያቄዎች ይሞላል፡፡ ስሜታችሁንና ጥርጣሬያችሁን አውጥታችሁ የምትናገሩ ከሆነ የተናገራችሁት ቃል በራሳችሁ ላይ ከመፍረዱም በላይ አቆጥቁጦ በሌሎች ሕይወት ላይ ፍሬ የሚያፈራና እንዲሁም ቃላችሁ የሚያመጣው ተፅእኖ ሊቀለበስ የማይችል ይሆናል፡፡ እናንተ ከሰይጣን ፈተና ትተርፉ ከወጥመዱም ታመልጡ ይሆናል፤ ሌሎች በእናንተ ቃል ተፅእኖ ምክንያት የዋዠቁ ሰዎች ግን እናንተ ከመራችኋቸው የዓለማመን አካሄድ ማምለጥ አይችሉም፡፡ መንፈሳዊ ጥንካሬና ሕይወት የሚሰጡ ነገሮችን ብቻ መናገር ምንኛ ወሳኝ ነገር ነው!ክየመ 114.3

    ስለ ሰማያዊ አባታችን ለዓለም የምታቀርቡትን ዘገባ ለማድመጥ መላዕክት በዙሪያችሁ ይከብቧችኋል:: የምትናገሩት ንግግር በአብ ፊት ስለ እናንተ የሚማልደውን የሚያከብር መሆን አለበት:: የጓደኛችሁን እጅ ለሰላምታ በምትጨብጡበት ጊዜ በአፋችሁ እና በልባችሁ ለእግዚአብሔር ክብር ስጡ፡፡ይህ የጓደኛችሁን ልብ ለኢየሱስ ይማርካል፡፡ክየመ 115.1

    ሁሉም ሰው ይፈተናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ሊሸከመው ከባድ የሆነበት ሀዘን፣ ሊቋቋመው በብርቱ የበዛበት ፈተና አለበት:: የሚያስጨንቋችሁን ነገሮች እንደ እናንተ ጠፊ ለሆኑት ሰዎች አትንገሩ፡፡ ይልቁንም በፀሎት ሁሉንም ነገር ወደ እግዚአብሔር አምጡት፡፡ ከአፋችሁ የጥርጣሬ እና የተስፋ መቁረጥ ቃል እንዳይወጣ የራሳችሁ ሕግ አድርጉት:: ይህን በማድረጋችሁና በተስፋ ቃል እንዲሁም በተቀደሰ ፈገግታ የሌሎችን ሕይወት ብሩህ ልታደርጉ እንዲሁም በሕይወት ተግዳሮት ላይ ላለባቸው ትግል ጥንካሬ ልትሆኗቸው ትችላላችሁ፡፡ክየመ 115.2

    የብዙ ሰዎች ነፍስ ከራሳቸው ጋር በሚያደርጉት ግጭት እና ከኃጢአት ኃይል የተነሳ ፈፅሞ ለመውደቅ እየተፍገመገመች በአደገኛ ሁኔታ በፈተና ውስጥ አለች:፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰው በሚያደርገው ግብግብ ተስፋ አታስቆርጡት:: በማበረታቻና እርሱን በመንገዱ ሊያነቃቁት በሚችሉ በተስፋ ቃላት አስደስቱት:: በዚህም የክርስቶስ ብርሃን በእናንተ ያብረቀርቃል፤«ለራሳችን አንኖርም እና» (ሮሜ 14፡7)፡፡ ሳታስተውሉት በምታደርጉት ነገር ሌሎች ሊበረታቱ እና ሊጠነክሩ ወይም ደግሞ በአንጻሩ ተስፋ ሊቆርጡ እንዲሁም ከክርስቶስ እና ከእውነት ሊርቁ ይችላሉ፡፡ክየመ 115.3

    ስለክርስቶስ ባህርይ እና ሕይወት ብዙዎች የተሳሳተ አስተሳሰብ አላቸው።እነዚህ ሰዎች፣ ክርስቶስ የደስታ ጸዳል የሌለው፣ ወና፣ ባዶ፣ ጎስቋላና ደስታ የራቀው እንደሆነ አድርገው ያስቡታል፡፡ በብዙ ሁኔታ፤ ሁሉም ሃይማኖቶች ማለት ይቻላል፤ የክርስቶስን የምድር ሕይወት በዚህ ዓይነት ጭጋጋማ ዕይታ ያዩታል፡፡ክየመ 116.1

    ብዙ ጊዜ ኢየሱስ እንዳነባ ሲጠቀስ እንደሳቀ ፈፅሞ አይታወቅም:: እርግጥ ነው፣ አዳኛችን ልቡ በሀዘን ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ የተከፈተ በመሆኑ እና ሐዘናቸውን ይካፈል ስለነበር የሕማም ሰው ነበር፡፡ ምንም እንኳ ሕይወቱ እራስን በመካድ፣ በህመም እና ጥንቃቄ የተሞላ ቢሆንም መንፈሰ ሰባራ ግን አልነበረም፡፡ገፅታው የሀዘንና የጉስቁልና አልነበረም፡፡ ነገር ግን የሰላም ድባብ ሸፍኖት ነበር፡፡እርሱ መልካም የሕይወት ምንጭ ነበር፡፡ በሄደበት ሁሉ ሰላም፣ ዕረፍት፣ደስታና እርካታ ይዞ ይሄድ ነበር፡፡ክየመ 116.2

    ሳታስታውሱ በምታደርጉት ነገር ሌሎች ሲበረታቱና ሲጠነክሩ ወይም ደግሞ በአንጻሩ ተስፋ ሲቆርጡ አንዲሁም ከጌታ እና ከእውነት ሲርቁ ይችላሱ።

    አዳኛችን በእርግጥ ከልቡ በአቋሙ የጸና እና ታማኝ የነበረ እንጂ ጨፍጋጋ እና እምነት የጎደለው አልነበረም፡፡ የእርሱን ሕይወት የሚጋሩ ሰዎች ሁሉ፣ በሙሉ ልባቸው የሚታመኑለት ዓላማ እና ሃላፊነት ይኖራቸዋል፤ አስመሳይነትና ኩራት አይታይባቸውም፧ በበላይነት የመኮፈስ ንግግርና አጉል ቀልድ ከአንደበታቸው አይደመጥም፡፡ ከዚህ ይልቅ በኢየሱስ ያላቸው እምነት እንደወንዝ የሚፈስ ሰላምን ይሰጣቸዋል። ይህ እምነት የደስታቸውን ብርሃን አያጠፋም:: ደስተኛነትንና የሚያሞቅ ፈገግተኛ ፊትን አያጨፈግግም፡፡ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ሊገለገል ሳይሆን ሊያገለግል ነው:: የእርሱ ፍቅር በእኛ ልብ ውስጥ ሲነግስ የእርሱን ምሳሌ እንከተላለን፡፡ክየመ 116.3

    የሌሎችን መልካም ያልሆኑና ትክክል ያልሆኑ ሥራዎች በአዕምሯችን ውስጥ ደብቀን የምንይዝ ከሆነ ክርስቶስ እኛን እንደወደደን እነርሱን መውደድ ያቅተናል፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ ለእኛ የሰጠው አስደናቂ እና የርህራሄ ፍቅር ገብቶን ከሆነ እኛም ለሌሎች ተመሳሳይ ፍቅር ይኖረናል፡፡ ምንም እንኳን የምንመለከታቸው ኃጢአትና በደሎች ቢኖሩም እነርሱን ከማሰብ ይልቅ እርስ በርሳችን መፈቃቅር እና መከባበር አለብን፡፡ ትህትናና ራስን ዝቅ ማድረግ፣ ለሌሎችም ከነበደላቸው ትዕግስት እና ርህራሄን ማሳየት ከእኛ ሊገኝ ይገባል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ልምምድ በእኛ ማንነት ውስጥ ጠባብነትንና እራስ ወዳድነትን ገድሎ ልበ-ሰፊነትንና ሩህሩህነትን ያነግሳል፡፡ክየመ 117.1

    ዘማሪው «በእግዚአብሔር ታመን መልካምንም አድርግ» (መዝ. 37:3) ይላል፡፡ እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ ሸክም፣ ጣጣና ውጣውረዶች አሉት:: እኛም በተሰበሰብን ጊዜ እነዚህን ችግሮችና ፈተናዎች ለማውራት ብዙ ጊዜ ይቃጣናል:: ብዙ አላስፈላጊ መከራዎች ከበውናል ፤ ፍርሃት ሃሳባችንን አንቆታል ፤ እጅግ የከበደውን ጭንቀት ለመሸከም አልቻልንም፡፡ ይህንን ሁሉ በአንድ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የሚያይ ሰው የጸሎት ጥያቄዎችን ሊሰማ የተዘጋጀና በመከራ ጊዜም የቅርብ ረዳት የሆነ ሩህሩህና አፍቃሪ አዳኝ እንደሌለ ሊያስብ ይችላል፡፡ክየመ 117.2

    አንዳንዶች በየዕለቱ በእግዚአብሔር የፍቅር ስጦታዎች እየተጎበኙ፣ በየዕለቱ በቸርነቱ ሙላቶች እየተደሰቱ እነዚህን ስጦታዎች ሁሉ ቸል በማለት ሁልጊዜም በፍርሀትና በአስጨናቂ ሁከት ውስጥ ናቸው:: የእነዚህ ሰዎች አዕምሮ «ይመጣል» ብለው በሚፈሩት ነገር የተጠመደ ስለሆነ ያለማቋረጥ ከሚያገኙት መልካም ነገር ጋር ሳይስማሙ ይኖራሉ፡፡ ወይም ሊያደንቋቸውና ሊያመሰግኑ ለሚገባቸው ትልልቅ ነገሮች ዓይናቸውን በመጨፈናቸው፣ ጥቃቅን በሆኑ ችግሮች ሁልጊዜ እንደተወጠሩ ይታያሉ፡፡ ከእነዚህ ከሚያጋጥሟቸው ጥቃቅን ችግሮች የተነሳ የረድኤታቸው ብቸኛ ምንጭ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ከመቅረብ ይልቅ ያለ ዕረፍት በመሆንና እርካታ በማጣት ውስጥ ተጠምደዋል፡፡ ክየመ 117.3

    ስለዚህ ዓለማመናችን ትክክል ነው? ለምን ምስጋና ቢስ እና እምነተ ቢስ እንሆናለን? ኢየሱስ ጓደኛችን ነው፤ መላው ሰማይ ደግሞ የእኛ ደህንነት የጠበቀ እንዲሆን ጽኑ ፍላጎት አለው፡፡ ስለዚህ የእለት ተእለት ሕይወት ጭንቀትና ችግር አዕምሮአችንን እንዲያሸብረውና ግንባራችንንም እንዲያጨማድደው ልንፈቅድለት አይገባም፡፡ ለእነዚህ እራሳችንን ያስገዛን ከሆነ ሁልጊዜም የሚያበሳጨን እና የሚያናድደን ነገር አናጣም:: ፈተናዎችን ለመቋቋም የማይረዱን ሆኖ ሳለ ለእነዚህ እንደ እርካታ ማጣት እና ጭንቀት ላሉ ነገሮች እራሳችንን በመስጠት የራሳችንን ሕይወት ማጎሳቆል የለብንም፡፡ክየመ 118.1

    ምናልባት በስራ ቦታችሁ ችግር ገጥሟችሁ ይሆናል ወይም የወደፊት ተስፋችሁ እየጨላለመባችሁ ሊሆን ይችላል ፤ የውድቀት ስጋት አድሮባችሁ ሊሆንም ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ተስፋ አትቁረጡ፡፡ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ጣሉና ጉዳያችሁን እንዴት እንደምትፈቱና ጥበብም እንድታገኙ በመፀለይ ውድቀት እና አደጋን ተከላከሉ፡፡ መልካም ውጤት ለማምጣት ልታደርጉ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ ኢየሱስ ሊያግዛችሁ ቃል ቢገባም የራሳችሁ ጥረትም ሊታከልበት ይገባል፡፡ በሰማዩ አባታችሁ በመታመን የምትችሉትን ሁሉ ካደረጋችሁ በኋላ ከዚያ በኋላ የሚመጣውን ውጤት ሁሉ በደስታ ተቀበሉት፡፡ክየመ 118.2

    እግዚአብሔር ልጆቹ በችግር ብዛት እንዲጎሳቆሉ አይፈቅድም፡፡ ጌታችን ፈፅሞ አላታለለንም፡፡ እርሱ ለእኛ «መንገዳችሁ ምንም አደጋ ስለሌለበት አትፍሩ» አላለንም:: እርሱ ፈተናና ችግሮች እንዳሉ ያውቃልና በግልፅ ተናግሯል፡፡ እርሱ እኛን ኃጢአትና ጥፋት ካለበት ዓለም ለማውጣት ሳይሆን ዓላማው፤ ወደዘለዓለማዊና ብርቱ መጠጊያችን ወደሆነው ለመምራት ነው:: ስለደቀመዛሙርቱ የፀለየው የእርሱ ፀሎት ከዓለም እንድታወጣቸው አልልም፤ በዓለም ውስጥ ከዓለም ክፋት እንድትጠብቃቸው እንጂ» (ዮሐ. 17:15) ብሎ ነበር፡፡ «መከራ አለባችሁ:: ነገር ግን ዓለምን አሸንፌአለሁና በመከራ ደስ ይበላችሁ» ዮሐ 16:33)፡፡ በተራራው ስብከቱ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ በእግዚአብሔር ስለመታመን አስደናቂ ትምህርቶችን አስተምሯል፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ማፅናኛ እንዲሆኑ በሁሉም ዕድሜ ክልል ለሚገኙ ለእግዚአብሔር ልጆች የተሰጡ ሲሆኑ፣ በዘመናችንም ሕያው ሆነው ይሰራሉ፡፡ አዳኛችን ተከታዮቹን ወደ ሰማይ ወፎች በመጠቆም ውዳሴያቸውን በዝማሬ እንደሚያቀርቡ እና ስለነገ ሮች በ መጨነቅ እንደማይዋጡ ሲያሳያቸው «አይዘሩም አያጭዱም» ይሁን እንጂ ትልቁ አባት የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣቸዋል ብሏል፡፡ አዳኛችን «ከእነዚህ በብዙ አትበልጡምን?» (ማቴ. 6:26) በማለትም ጠይቋል፡፡ ይህ ታላቅ እግዚአብሔር እጁን ለፍጥረቱ ሁሉ በመዘርጋት ለሰውና ለእንስሳ ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣል፡፡ እርሱ ለሰማይ ወፎች እንኳን ሳይቀር ይጠነቀቃል፡፡ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ይሰጣቸዋል፡፡በርግጥ ምንቃራቸውን በመያዝና አፋቸውን በማስከፈት ምግባቸውን አፋቸው ውስጥ አይጥልላቸውም:: የበተነላቸውን ጥራጥሬ ራሳቸው መለቃቀም አለባቸው:: ለትንሿ ጎጆአቸው ግንባታ የሚሆናቸውን ዕቃም ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ ጫጩቶቻቸውን መመገብም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለስራ ሲሰማሩ የሰማይ አባታችሁ ስለሚመግባቸው» ይዘምራሉ፡፡ እናም «እናንተ ከእነርሱ በብዙ አትበልጡም?» እናንተ ግን አስተዋዮችና መንፈሳዊ አምላኪ ዎች ስትሆኑ ከሰማይ ወፎች የበለጠ ዋጋ የላችሁም? እኛ በእርሱ ከታመንን፤ የማንነታችን ፈጣሪ፣ የሕይወታችን ጠባቂ እና በመለኮታዊ አምሳሉ የፈጠረን አምላክ የሚያስፈልገንን እንዴት አብልጦ አይሰጠንም?ክየመ 118.3

    የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእግዚአብሄር ላይ ጣሉና ጉዳያችሁን እንዴት እንደምትፈቱ ጥበብን ለማኘት ጸልዩ።

    ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ የሰማይ አባት ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር ለማሳየት ለአበቦች በቀላሉ እንዲያምሩ የሰጣቸውን ውበት እና ብልፅግና በማመላከት ወደ አበባዎች ጠቁሟቸዋል፡፡ እርሱ «የሜዳ አበቦችን እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ» ብሏል:: የእነዚህ አበቦች የተፈጥሮ ጸጋና አንጸባራቂ የሆነ ውበት ሰለሞን በዛ ሁሉ ሀብቱ እንኳን እንደእነርሱ ሊለብስ እና ሊዋብ አልቻለም:: እጅግ በጣም ውብ የሆነ በእጅ ጥበብ ክህሎት የተሰራ ሥዕል የእግዚአብሔር ፍጥረት የሆኑ አበቦችን ውበት ሊያገኝ አይችልም፡፡ኢየሱስ «እናንተ እምነት የጎደላችሁ እግዚአብሔር ዛሬ ታይቶ ነገ በእሳት የሚጠፋን ሳር እንዲህ ካለበሰ እናንተን የበለጠ እንዴት አያለብሳችሁም?» (ማቴ. 6:28 ና 30)፡፡ መለኮታዊ ጥበብ የተሞላው እግዚአብሔር ታይተው ለሚጠፉ አበቦች እንዲህ የሚያሳሳ እና የተለያዩ ቀለማት ሰጥቶ እንዲያምሩ ካደረጋቸው በእርሱ አምሳል ለተፈጠሩ እንዴት የበለጠ ክብካቤ አያደርግላቸውም? እንዲህ ዓይነቱን የክርስቶስ ትምህርት የማያምን ልብ ያላቸውን፣ በተዘበራረቀ ሃሳብ እና በጥርጣሬ የተሞሉትን ክርስቶስ ይገስጻቸዋል፡፡ክየመ 119.1

    ጌታ ሴቶችና ወንዶች ልጆቹን ደስተኛ፣ ሰላም የሞላቸው እና ታዛዥ እንዲሆኑለት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- «ሰላምን እተውላችኋለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም፡፡» «ደስታዬ በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈፀም ይህን ነግሬአችኋለሁ» ዮሐ 14:27 ና 15:11)፡፡ክየመ 120.1

    ከራስ ወዳድነት ስሜትና ኃላፊነት የጎደለው ጎዳና የሚገኝ ደስታ ሚዛናዊነት የጎደለው፣ አጥፊ እና አላፊ ነው፡፡ ይህ ደስታ ባለፈ ጊዜ ነፍስ በብቸኝነትና በሀዘን ትሞላለች:: እግዚአብሔርን በማገልገል ግን ደስታና እርካታ አለ፡፡ ክርስቲያኖች ባልተረጋገጠ መንገድ እንዲጓዙ አልተተውም፤ ለፀፀትና ለተስፋ መቁረጥ አልተተውም፡፡ አሁን ባለው ሕይወት ደስተኞች ባንሆን እንኳን ከዚህ ባሻገር በሚኖረው ሕይወት ደስታ እናገኛለን፡፡ክየመ 120.2

    በዚህ ዓለምም ቢሆን ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር ባላቸው ህብረት ደስታ አላቸው:: የፍቅሩ ብርሃን በውስጣቸው ደስታን ይሰጣቸዋል፡፡ የእርሱ አብሮነት የማይቋረጥ መፅናናት ይሰጣቸዋል፡፡ ወደ ኢየሱስ የሚያቀርበን እያንዳንዱ የሕይወት እርምጃ የእርሱን ፍቅር በጥልቅ እንድንለማመድ እና ወደተባረከው የሰላም ቤት አንድ ደረጃ እንድንቀርብ ያደርገናል፡፡ ስለዚህ መተማመናችንን አንጣ ይልቁንም አብልጠን ዋስትናችንን ከበፊት ይልቅ እናፅና፡፡ «እስከአሁን ድረስ ጌታ እረድቶናል» እርሱ እስከፍፃሜም ይረዳናል (1ኛ ሣሙ. 7:12)፡፡ ከአጥፊው እጅ ሊያድነንና ሊያፅናናን ጌታ ለእኛ ያደረገልንን አስደናቂ ነገሮች ጌታ የሚያሳስቡንን ታላላቅ የመታሰቢያ ሃውልቶቻችንንና ማስታወሻዎቻችንን ድረስ እንይ፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያሳየውን ርህራሄ፣ ያፈሰሰልንን እንባ፣የፈወሰንን ቁስል፣ የወሰደልንን ሀዘን፣ ያስወገደልንን ፍርሃት፣ የሞላልንን ፍላጎት፣ ያበዛልንን በረከት፣ ሁልጊዜ በየዕለቱ እናስብ፡፡ ይህንን ማሰብ በሚቀረን መንፈሳዊ ጉዙአችን ሁሉ ለጥንካሬያችን ይረዳናል፡፡ክየመ 120.3

    እስከ አሁን ድረስ እረድቶናል አስከፍጻሜም እርሱ ይረዳናል።

    ከፊት ለፊታችን ባለን የሕይወት ዘመን ውስጥ የሚገጥመንን ውጣ ውረድ ከማሰብ ይልቅ ያለፈውንና መጪውንም እያሰብን «እስከአሁን ድረስ ጌታ እረድቶናል» «እንደ እድሜህ እንዲሁ ጥንካሬህ ይሆናል» በማለት እናውጅ (ዘዳ. 33:25)፡፡ የሚገጥሙን ፈተናዎች እነርሱን ልንቋቋምበት ከሚሰጠን ጥንካሬ አይበልጡም:: ምንም ቢመጣ ከዚያ ተግዳሮት የበለጠ ጥንካሬ እንደሚሰጠን በማመን የተሰጠንን ስራ ባገኘንበት ሁሉ ለመስራት እንትጋ፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች «እናንተ የአባቴ ብሩካን ኑ ዓለም ሳይፈጠር በፊት የተዘጋጀላችሁን የእግዚአብሔር መንግስት ውሰዱ» (ማቴ. 25:34 የሚሉ በጆሮአቸው የሚያስተጋቡ ፣ ሙዚቃዊ ቃና ያላቸው ፣ ከንጉሱ አፍ የሚፈሱ ክቡር የባርኮት ቃላትን እያደመጡ ሳለ የገነት ደጆች እነርሱን ለመቀበል ወለል ብለው ይከፈታሉ።ክየመ 121.1

    በዚያን ጊዜ የተዋጁት ይገቡበት ዘንድ አስቀድሞ ለእነርሱ በኢየሱስ ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ «እንኳን ደህና መጣችሁ!» ይባላል፡፡ በዚያ ስፍራ አብረዋቸው የሚሆኑት የምድር ከንቱነት የተጠናወታቸው፣ ውሸታሞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ እራሳቸውን ያላነፁና ያላመኑ ሳይሆኑ፤ አብረዋቸው የሚሆኑት ሰይጣንን አሸንፈው በመለኮታዊ ፀጋ ፍፁም የሆነውን ባህሪ ያገኙ ናቸው:: በዚህ ምድር ሲያጎሳቁላቸው የነበረው የኃጢአት ዝንባሌ ሁሉ ኃጢአትና ግሳንግሱ በክርስቶስ ደም ከእነርሱ ተወግዷልና የእርሱ ልሒቅነት እና ከፀሐይ ብርሃን የሚልቀው የክብሩ ብርሃን ይከብባቸዋል፡፡ የክርስቶስ ውበት፣ የባህሪው ፍፁምነት በእነርሱ ውስጥ ያበራል:: ይህ በእነርሱ ላይ በሚሆን ጊዜ በውጭ ከሚታይ ውበት በእጅጉ ይበልጣል፡፡ በታላቁ ነጭ ዙፋን ፊት የመላዕክትን ክብርና በረከት በመጋራት ያለነቀፋ ይሆናሉ፡፡ክየመ 121.2

    ከተዘጋጀልን ዘላለማዊና ባለ ታላቅ ግርማ ውርስ አንጻር ሲታይ «ሰው ስለነፍሱ ምን ዋጋ ሊከፍል ይችላል? ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?» (ማቴ. 16:26)፡፡ አንድ ሰው እጅግ ድሃ ቢሆንም ዓለም ፈፅሞ ሊያገኘው የማይችል ሃብትና ክብር ሊኖረው ይችላል:: ከኃጢአት ተዋጅቶ እና ነፅቶ በሙሉ ኃይሉ ሕይወቱን ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሰጠ ሰው በእግዚአብሔር ዓይን ታላቅ ዋጋ አለው:: እንደዚሁም አንዲት ነፍስ በተዋጀች ጊዜ በላይ በሰማይ በእግዚአብሔር ማደሪያ እና በመላዕክት ዘንድ በቅዱስ የድል ዝማሬ የሚገለጽ ታላቅ ደስታ ይሆናል፡፡ክየመ 122.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents