Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከአብ ጋር ግንኙነት

    የሱስ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ደቀመዛሙርት አንዳንድ ጊዜ ዘመዶቻቸውን እንዲጠይቁ ያሰናብታቸው ነበር፡፡ ግን ከሥራው ሊያርቁት በሚያደርጉት ሙከራቸው አይሳካላቸውም ነበር፡፡ በየቀኑ ወደ እርሱ የሚመጣውን ሕዝብ ሁሉ ያገለግል ነበር፡፡ ከአባቱ ጋር ለመገናኘት ወደ ተራራ ይሄድ ነበር፡፡CLAmh 143.1

    የዘወትር ሥራውና ሊቃውነቱ ከሚያስተምሩት ሀሰተኛ ትምህርት ጋር የሚያደርገው ትግል ስላደከመው ደቀመዛሙርቱ፣ እናቱ፣ እህቶቹና ወንድሞቹ ለሕይወቱ ሰግተውለት ነበር፡፡ ግን ሥራውን ካከናወነ በኋላ ከጸሎት ሲመለስ በፊቱ ላይ የሰላም ምልከት ያዩ ነበር፡፡ አቋሙ በሙሉ የነቃና ብርቱ ነበር፡፡CLAmh 143.2

    ከእግዚአብሔር ጋር በየጧቱ ከተነጋገረ በኋላ የሰማይን ብርሃን ለሰዎች ይገልጥላቸው ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱ የመጀመሪያውን የወንጌል ሥራቸውን አጠናቀው ከተመለሱ በኋላ የሱስ ኑና እረፉ አላቸው፡፡ ደቀመዛሙርቱ የወንጌል መልእክተኝነታቸው ስለተሳካላቸው ደስ ብሏቸው ሳለ መጥምቁ ዮሐንስን ሄሮድስ እንደገደለው መርዶ መጣላቸው፡፡ ከልባቸው ምርር ብለው አዘኑ፡፡CLAmh 143.3

    የሱስ መጥምቁ ዮሐንስ ሲሞት ምንም ባለማድረጉ ደቀመዛሙርቱን እንደፈተናቸው አውቋል፡፡ አዝነው ጉንጫቸው በዕንባ ሲርስ አይቶ አዘነላቸው፡፡ እርሱም “ኑ ወደ ምድረ በዳ ሄዳችሁ ዕረፉ” ያለው እንባ እያነቀው ነበር፡፡ (ማርቆስ 6፡31) ፡፡CLAmh 143.4

    በቤተሳይዳ አጠገብ ከገሊላ ባሕር በስከ ሰሜን ጫፍ በለምለም መስክ የተዋበች የተለየች ሥፍራ ነበረች፡፡ በዚያች ቦታ የሱስና ደቀመዛሙርቱ አረፉባት፡፡ በጀልባቸው እየቀዘፉ ወደዚያች ቦታ አመሩ፡፡ አሁን ከሕዝቡ ግርግር ገለል ብለው ሊያርፉ ነው፡፡ አሁን ደቀመዘሙርቱ የፈሪሣውያን አሳሳች ጥያቄ ሳያደናቅፋቸው የየሱስን ጣፋጭ ትምህርት ሊያዳምጡ ነው፡፡ አሁን ከጌታቸው ጋር ለጥቂት ጊዜ እንደሚደሰቱ ተስፋ አደረጉ፡፡CLAmh 143.5

    ጌታ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ብቻቸውን የቈዩት ጊዜ አጭር ቢሆንም በጣም ተደሰቱ፡፡ ስለወንጌል ሥራና ሰዎችን ሊያስተምሩ የሚችሉበትን የተሳካ ዘዴ አንስተው በሰፊው ተወያዩ፡፡ የሱስ የዕውነትን መዝገብ ከፍቶ ሲያፈስላቸው አዲስ ኃይልና ድፍረት አገኙ፡፡ ግን ብዙ ሳይቆይ ሕዝብ ሁሉ ፈለጉት፡፡ ወደ ዘወትር የዕረፍት ቦታ ሄዶ ይሆናል ብለው ተከተሉት፡፡CLAmh 143.6

    ያ መልካሙ ጠባቂ ለተቅበዘበዙት በጎች አዘነላቸው፡፡ ቀኑን ሙሉ ሲያገለግላቸው ውሎ በመሸ ጊዜ ወደየቤታቸው አሰናበራቸው፡፡CLAmh 144.1

    የሱስ ለሌሎች ደግ ለመዋል ባቀደው ኑሮው ከዕለት ተግባር ዘወር ብሎና ከሕዝብ ተለይቶ ከአባቱ ጋር መገናኘት እንደሚያሻው ተገነዘበ፡፡ ከሰዎች ሲለይ ወደ ገለልተኛ ቦታ ሄዶ ለእነዚያ ደካሞች፤ ኃጢአተኞችና ጎስቋሎች ነፍሳት ይጸልይላቸዋል፡፡CLAmh 144.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents