Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጥሩ የመተንፈስ ልምድ

    ሳንባ የሚያስፈልገውን ያህል ለመለጠጥና ለመኮማተር መቻል አለበት፡፡ ሳንባ ብዙ አየር የመያዝ ችሎታው የሚሻሻለው ያስፈለገውን ያህል ለመንቀሳቀስ ሲችል ነው፡፡ ሳንባ የተጨበጠ እንደሆን አየር የመያዝ ችሎታው ይቀንሳል፤ በዚህ ምክንያት በቅምጥ ወደፊት ታጥፈው ሲሰሩ የሚውሉ ሰዎች የሳንባ ሕመም ይደርስባቸዋል፡፡ ሳንባ እንዲታጠፍ ሆኖ ከተቀመጡ ብዙ አየር ለመሳብ አይቻልም፡፡CLAmh 50.2

    ሳንባ ሁልጊዜ ቆሻሻ ስለሚያወጣ ሁልጊዜ ንጹሕ አየር ማግኘት አለበት፡፡ ቆሻሻ አየር በቂ ኦክስጅን ስለሌለው ያለዚህ አየር ደም ወደ አንጎልና ወደ ሌላ ብልቶች ይሄዳል፡፡ በክፍል ውስጥ በቂ ንጹሕ አየር ማግኘት የሚገባው ስለዚህ ነው፡፡ በተዘጋና ንጹሕ አየር በሌለው ክፍል ወይም ቤት ውስጥ መኖር መላውን አካል ያደክማል፡፡ አካል በቅዝቃዜ የሚጎዳ ከመሆኑ በላይ በቀላሉ ሕመም የሚያጠቃው ይሆናል፡፡ ብዙ ሴቶች የሚገረጡና ደካማ የሚሆኑት በቂ አየር በሌለው ቤት ውስጥ ስለሚውሉ ነው፡፡ ከአካላችን የሚወጣው ቆሻሻ በብዛት እስኪጠራቀምበት ያንኑ አየር ደጋግመው ይስባሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ቆሻሻው ተመልሶ ወደ ደማቸው ይገባል፡፡CLAmh 50.3

    ለሕዝብ አገልግሎት ሆነ ለግል መኖርያ የሚሠራ ቤት ሁሉ አየርና ጸሐይ የሚያስገባ ሆኖ መሠራት አለበት፡፡ የቤተክርስቲያን ሕንጻዎችና የመማሪያ ክፍሎች በዚህ በኩል ብዙ ጉድለት አለባቸው፡፡ የብዙ ስብከትን ጥቅም የሚያጠፋ ያስተማሪዎችን ሥራ የሚያከብድና ድካማቸውንም ዋጋ የሌለው የሚያደርገው በቂ ተዘዋዋሪ አየር ባለመኖሩ ምንያት የሚመጣው እንቅልፍና መፍዘዝ ነው፡፡CLAmh 50.4

    በተቻለ መጠን ለሰው መኖሪያ የሚሠራ ቤት ሁሉ ከፍ ካለና ቆሻው በውሃ ተጠርጐ ሊሄድ ከሚችልበት ቦታ ላይ መሆን አለበት፡፡ ይህ ዓይነት ቦታ ደረቅ ስለሚሆን ከእርጥበትና ከበሰበሰ ቆሻሻ የሚመጣ ሕመም አይገኝበትም፡፡ ቤትን በእንደዚህ ያለ አኳኋን የመሥራት በጣም አይታሰብበትም፡፡ ጤና ማጣት፣ ሃይለኛ ሕመምና ብዙ ሞት የሚደርሰው እርጥበት በሚበዛበት ቦታ ሲሆን የወባ በሽታ የሚገንነውም በቆላና ጨቀጨቅ በሚበዛበት ቦታ ነው፡፡CLAmh 51.1

    ቤት በሚሠራበት ጊዜ በቂ አየርና ፀሐይ እንዲገኝ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ከቤቱ ውስጥ በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ በቂ አየርና የፀሐይ ብርሃን መኖር አለበት፡፡ በመኝታ ክፍል ቀን ተሌት ንጹሕ አየር መኖር አለበት፡፡ በየቀኑ ተከፍቶ የፀሐይ ብርሃንና ንጹሕ አየር ሊገባበት የማይችል ክፍል የመኝታ ክፍል መሆን አይገባውም፡፡CLAmh 51.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents