Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    7—የቤተሰብን ሞራል ማደርጀት

    ለልጆች ቤታቸው በዓለም ውስጥ ከማንኛውም ቦታ የበለጠ የሚወዱት መሆን አለበት፤ የተወዳጅነቱም ምክንያት የእናቲቱ መኖር መሆን አለበት፡፡ ልጆች ስሜታቸው በቀላሉ የሚለዋወጥና አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ በትንሽ ነገር ይደሰታሉ፤ በትንሽ ነገርም ያዝናሉ፡፡ ተጠንቅቆ በመቆጣት፣ በፍቅር ንግግርና ሥራ እናቶች ልጆቻቸው እንዲወዷቸው ለማድረግ ይችላሉ፡፡CLAmh 32.2

    ልጆች ጓደኝነትን ስለሚወዱ ብቸኝነት አያደስታቸውም፡፡ የሚራራላቸውንና የማያንገላታቸውን በጣም ይወዳሉ፡፡ እነሱ የሚወዱት ነገር ሁሉ እናታቸውንም የሚያስደስታት ይመስላቸዋል፡፡ ስለዚህ ለትንሹም ለትልቁም ኀዘንና ደስታ ወደ እናታቸው ይሮጣሉ፡፡ እናቲቱም ምን እንኳ ለእሷ ቁም ነገር የሌለው ቢመስላትም ለነሱ ዋና የሆነውን ነገር ችላ በማለት ልታሳዝናቸው አይገባትም፡፡ ርኅራኄዋና ፍርድዋ በጣም ዋና ነው፡፡ የመፍቀድ አስተያየት፤ የማይደፈር ወይም የምስጋና ቃል በልባቸው ላይ እንደ ፀሐይ እያበራ ቀኑም ሙሉ ሲያስደስታቸው ይውላል፡፡CLAmh 32.3

    እንዳይጮሁባት ወይም እንዳያስቸግሯት በማለት ከእስዋ እንዲርቁ ለማድረግ በመሞከር ፈንታ እናቲቱ ለልጆቹ ቀላል ሥራ ወይም ጨዋታ ማዘጋጀት አለባት፡፡CLAmh 32.4

    ውስጠ ስሜታቸውን በማወቅ፤ የሚያስደስታቸውን ነገርና የሚሰሩትን ሥራ በማዘጋጀት ልጆችዋ እንዲወዷትና እንዲያምኗት ለማድረግ የቻለች እናት የልጆቸዋን መጥፎ ጠባይና ራስን ብቻ የመውደድ ስሜት ለማረም ይመቻታል፡፡ በትክክለኛው ጊዜ የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ ወይም ተግሣጽ ከፍ ያለ ዋጋ አለው፡፡ እናቲቱ በትዕግስትና በፍቅር የልጆቿን አእምሮ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ለመመለስ ጥሩና ተወዳጅ የሆነ ጠባይ እንዲኖራቸው ለማድረግ ትችላለች፡፡CLAmh 32.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents