Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    2—የቤተ ሰብ ሕይወት

    ኅብረተሰብ የተመሰረተው በቤተሰብ ላይ ሲሆን አይነቱም የሚወሰነው በቤተሰብ መሪዎች ነው፡፡ “ሕይወት ከልብ ይመነጫል” ምሳ 4፡23፡፡ የቀበሌው፤ የቤትክርስቲያንና የአገር ልብ ቤተሰብ ነው፡፡ የኅብረተሰብ ሰላማዊነት፣ የቤተክርስቲያን ክንውንና የአገር ብልጽግና የሚወሰነው በቤተሰብ ነው፡፡CLAmh 9.1

    “የቤተሰብ ሕይወት ዋናነትና ዕድል በኢየሱስ ሕይወት ተገልጿል፡፡ ምሳሌአችንና መምህራችን ለመሆን ከሰማይ የወረደው ጌታችን በናዝሬት የቤተሰብ አባል ሆኖ ሰላሳ አመት ኖረ፡፡ ስለነዚህ አመታት የተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በጣም አጭር ነው፡፡ ሕዝቡን ወደ እርሱ የሳበ ታላቅ ተዓምር አልሰራም፡፡ ለመስማት ናፍቆት ያደረበት ሕዝብ ቃሉን ለመስማት አልተከተለውም፡፡ ቢሆንም በዚህ ጊዜ ውስጥ መለኮታዊ መልዕክቱን ፈጸመ፡፡ የቤተሰብን ሕግ በመጠበቅ የቤተሰብን ተግባር በመፈጸምና የቤተሰብ ችግርም በመካፈል እንደ እኛ የቤተሰብ ኑሮ ኖረ፡፡ በድሃ ቤተሰብ ተጠባባቂነት በኛ ላይ ሊደርስ የሚችለው ነገር ሁሉ የደረሰበት፤ “በጥበብና በቁመት ያድግ ነበር፤ በጸጋም በእግዚአብሄር በሰውም ዘንድ” ሉቃስ 2፡52CLAmh 9.2

    የጌታችን የወጣትነት ዘመን ለወጣት ሁሉ ጥሩ ምሳሌነቱ ከሚፈለገው በላይ ነው፡፡ የወጣትነቱ ጊዜዎች ትምህርት የሞላባቸው ስለሆኑ ለወላጅ ሁሉ የሚያደፋፍሩ ናቸው፡፡ የሰውን ሕይወት ለማሻሻል ለሚፈልጉ ሁሉ የቤተሰብንና የጉርብትናን ተግባሮች መፈጸም የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡ ለቤተሰብ መሥራቾችና ሞግዚቶች ከተሰጠው ሥራ የበለጠ ዋና ሥራ የለም፡፡ ለሰው ከተሰጡት የሥራ ኃላፊነቶች ሁሉ ለወላጆች የተሰጠውን ያህል ዘላቂ ውጤት ያለው ኃላፊነት የለም፡፡CLAmh 9.3

    ኅብረተሰብ ለወደፊቱ ምን እንደሚሆን የሚወሰነው በዛሬው ወጣቶችና ሕጸናት ነው፡፡ እነዚህም ወጣቶችና ሕጻናት ምን እንደሚሆኑ የሚወሰነው በቤተሰብ ነው፡፡ የሰብዓዊ ዘር ሁሉ መርገም የሆኑት አብዛኛዎቹ የወንጀል ሥራዎች ስቃይና በሽታዎች መነሻቸው የቤተሰብ ትምህርት ጉድለት ነው፡፡ የቤተሰብ ሕይወት ንጹህና እነውነተኛ ቢሆን ከቤተሰብም የሚወጡት ልጆች ለሕይወት ኃላፊነት የተዘጋጁ ቢሆኑ ኖሮ በዓለም ምን ያህል መለወጥ በታየ ነበር፡፡CLAmh 9.4

    የመጥፎ ጠባይ ተጠቂ የሆኑትን ሰዎች መርጃ ድርጅቶችን ለማቋቋም የሚደረገው ትልቅ ጥረት ብዙ ጊዜና አያሌ ገንዘብ ጠፍቶበታል፡፡ ይህም ዓይነት ጥረት ሊደረግ ከሚገባው እርዳታ ጋር ሲመዛዘን በቂ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ይሁን እንጂ ውጤቱ እጅግ ያነሰ ነው፡፡CLAmh 9.5

    አያሌ ሰዎች የተሻለ ሕይወት ለመኖር ይመኛሉ፡፡ ግን የመጥፎ ኑሯቸውን ልምድ ለማሸነፍ ድፍረትና ቆራጥነት ያንሳቸዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ከሚያስፈልገው ጥረት፣ ትግልና መስዋዕትነት ስለሚያፈገፍጉ ሕይወታቸው የተበላሸ ነው፡፡ በዕውቀታቸውም ሆነ በሌላ ነገር ገጣሚ በመሆናቸው ታማኝነትን የሚጠይቅ ኃላፊነት ሊጣልባቸው የሚቻል ከፍ ያለ ዓላማ ያላቸው አስተዋይ ሰዎች ሕይወታቸው የተበላሸ ከመሆኑ የተነሣ በያዝነው ሕይወት ሆነ በሚቀጥለው የተናቁና የማይፈለጉ ናቸው፡፡CLAmh 10.1

    ከመጥፎ ኑሯቸው ለሚመለሱ ሁሉ ሙሉ ሰብዓዊነታቸውን እንደገና ለማግኘት ያለባቸው ትግል እንዴት የከፋ ነው! በተጎሳቆለው ሰውነታቸው በወላዋይ ሐሳባቸው፣ በተበላሸ አዕምሯቸውና በኮሰሰው የነፍሳቸው ሐይል ምክንያት አያሌ ሰዎች የዘሩትን የመጥፎ ዘር መከር በህይወታቸው ሙሉ ይሰበስባሉ፡፡ መጥፎውን ጠባይ ከመጀመሪያው ለማጥፋት ጥረት ቢደረግ ኖሮ ምን ያህል ክንውን በተገኘ ነበር!CLAmh 10.2

    የዚህ ዓይነት ሥራ አብዛኛው ኃላፊነት የወላጆች ነው፡፡ የኅብረተሰብን ሕይወት እንደ ካንሰር የሚበዘብዙትን ራስን ያለመግታት ልምድና ሌሎችንም መጥፎ ጠባዮች ለማገድ በሚደረገው ጥረት ወላጆች እንዴት አድርገው የ56ልጆቻቸውን ጠባይ መገንባት እንደሚገባቸው ቢማሩ ውጤቱ መቶ እጥፍ በሆነ ነበር፡፡ የክፉ ነገር መሣሪያ የሚሆነውን ጠባይ የጥሩ ነገር መሣሪያ የማድረግ ስልጣን አላቸው፡፡ ከመነሻው ጀምረው ከያዙት የቀረው ትክክል የመምራት ጉዳይ ነው፡፡CLAmh 10.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents