Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አጋንንት የሚያሸንፍ የዘመኑ ኃይል

    እንደቅፍርናሆም ዕብድ በርኩሳን መናፍስት የተያዙ ዛሬም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እያወቁ ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ የሚርቁ ሰዎች የሰይጣን ተገዥዎች መሆናቸው ነው፡፡CLAmh 163.1

    ብዙዎች ደስታ የሚያገኙ እየመሰላቸው በኃጢአት ይጨማለቃሉ፡፡ ግን ቀስ በቀስ ራሳቸውን መቈጣጠር እስኪቅታቸው ድረስ በአጉል ልምድ ይያዛሉ፡፡CLAmh 163.2

    ከምሥጢራዊ ኃይሉ ሊያመልጥ አይችልም፡፡ የምስጢር ኃጢአት ወይም የመጥፎ ሱስ እሥረኛ ይሆንና እንደ ቅፍርናሆሙ ዕብድ እሥረኛ ይሆናል፡፡CLAmh 163.3

    ግን ይዞታው ተስፋ የሚያስቈርጥ አይደለም፡፡ እኛ ካልተስማማን እግዚአብሔር አሳባችንን በግድ አይጣጠርም፤ ግን እያንዳንዱ ሰው ለየትኛው ኃይል አገልጋይ እንደሚሆን የመምረጥ መብት አለው፡፡ ማንም የተዋረደ ቢዋረድ፤ የከፋ ቢከፋ ክርስቶሰ ሊያድነው ይችላል፡፡ ጋኔን ያደረበት ሰው በመጸለይ ፋንታ የሰይጣንን መልዕክት ይናገራል፤ በልቡ ግን ተማህጽኖ ይሰማል፡፡CLAmh 163.4

    አንድ ሰው በአፉ ባይናገርም የልቡ ፍላጎት በእግዚአብሔር ዘንድ ችላ አይባልበትም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመገባት የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ለሰይጣን ኃይል ወይም ለደካማው ተፈጥሮአቸው አይጋለጡም፡፡CLAmh 163.5

    ስለዚህ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ሰይጣንን እንደተሸነፈ ጠላት አድርገው መቁጠር አለባቸው፡፡ የሱስ በመስቀሉ ላይ ድል ነስቷል፤ ያን ድልም እንደራሳቸው አድረገው እንዲቀዳጁት ይፈልጋል፡፡CLAmh 163.6

    የላይኛውን ዙፋን የከበበው የተስፋ ቀስተ ዳመና “እግዚአብሔር እንዲሁ ዓለሙን ወዷልና አንድ ልጁን እስኪለውጥ ድረስ በእርሱ ያመነ ሁሉ እንዳይጠፋ የዘላለም ሕይወት ትሆንለት ዘንድ እንጅ” በሚለው የወንጌል ቃል ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ (ዮሐንስ 3፡16)CLAmh 163.7

    እግዚአብሔር ሰዎችን ከሰይጣን ጋር በሚያደርጉት ጦርነት አጋፍጦ እንደይተዋቸው ለዓለማት ሁሉ ያረጋግጣል የአምላክ ዙፋን ዘለዓለማዊ ነውና የዘለዓለም ጥበቃውና ብርታቱ እንደማይለየን ማረጋገጫ አለን፡፡CLAmh 163.8

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents