Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአደጋ ብዛት ጠንቅ

    በመጠጥ ጠንቅ የሚደርሱትን የየእለቱን አደጋዎች ተመልከቱ፡፡ በባቡር መንገድ ላይ ያለውን ምልክት አንዳንድ ነጂዎች ችላ ይሉታል፤ ወይም በተሳሳተ ትርጉም ያስተውሉታል፡፡ ባቡሩ መንገዱን ይቀጥልና ግጭት ይፈጠራል፡፡ ወይም ሀዲዱን ለቆ ገደል ይገባና ተሣፋሪዎቹ በሙሉ እርግፍ ይላሉ፡፤ ነገሩ ሲመረመር ከባድ ኃላፊነት የተጣለበት ሰው በመጠጥ ኃይል ስለተመረዘ አደጋው መድረሱ ይታወቃል፡፡ አንድ ሰው መጠጥ እስከምን ደረጃ ድረስ ቢጠጣ ነው በሰው ሕይወት ላይ ያለበትን ኃላፊነት ያለ ጉድለት ሊያጠናቅቅ የሚችል? ሥራውን በሚገባ ለማካሄድ ከፈለገ ፈጽሞ አለመንካት ይበጀዋል፡፡CLAmh 78.4

    ቢራ፣ ጠጅ፣ የጠንካራ መጠጥ ያህል ሊያሰክሩ ይችላሉ፡፡ ቀለል ያሉት መጠጦች የጠንካራ መጠጥን አምሮት ይፈጥና የጠጭነት ሱስ ይተከላል፡፡ መጠነኛ መጠጥ ሰዎች ስለ ሰካራምነት የሚሠለጥኑበት ትምህርት ቤት ነው፡፡ ነገሩ ውስጥ ለውስጥ ስለሚሠራ ጠጭው ሳይገነዘበው የመጠጥ ተገዥ ሆኖ ያገኘዋል፡፡CLAmh 78.5

    በጨጭነት ደረጃ የማይጠረጠሩ ሰዎች በስካር ጥላ ሥር መገኘታቸው ያስደንቃል፡፡ የትኩሳት በሽታ ያጠቃቸዋል፤ ወላዋይ ይሆናሉ፤ ያልተደላደለ አስተሳሰብ ይኖራቸዋል፡፡ በሰላም አለን ብለው ሲያስቡ መጠጡን ካላቋረጡ ያላቸው የመከላከያ ኃይል ያከትማል፡፡ ደንብና ሥርዓትን ጥሰው ከሕግ ውጭ ይሆናሉ፡፤ ጨክነው ቆረጥን ቢሉ አይሳካላቸውም፤ አመዛዝነው ፍላጎታቸውን እንግታ ቢሉም አሳባቸው ውድቅ ይሆናል፡፡CLAmh 79.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents