Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አዲስ ኑሮ መጀመር

    ያ ጊዜ የተቀደሰና ለጌታ ያደረ አዲስ ኑሮ የምትጀምርበት ወቅት ሆነላት፡፡ የሱስ ያችን ጎስቋላ ሴት ከወደቀችበት ለማንሳት የፈጸመው ተአምር ስጋዊ በሽተኛን ከመፈወስ በጣም የላቀ ነበር፡፡ ለዘለአለም ሞት ከሚያደርሰው ከመንፈስ ደዌ ገላገላት፡፡CLAmh 161.1

    ይች በኃጢአቷ ተጸጽታ የተመለሰች ሴት ከክርስቶስ ጽኑ ተከታዮች አንዷ ሆነች፡፡ ከልቧ በመነጨ ፍቅር አማካይነት በምሕረቱ ይቅር ስላላት ምሥጋናዋን ገለጠች፡፡ ይችን የተሳሳተች ሴት ዓለም በማፌዝና በማሽሟጠጥ ተቀበላት፡፡ ግን ነውር የሌለበት ጌታ ስለ ጉድለቷ አዘነላት፤ የርዳታ እጁንም ዘረጋላት፡፡ ግብዞቹ ፈሪሣውያን ሲያወግዟት የሱስ “ከዜሩ ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ “አላት፡፡CLAmh 161.2

    የሱስ የያንዳንዱን ሰው ችግር ያውቃል፡፤ የኃጢአተኛው ወንጀል እንደከበደ መጠን የመድኅን ርዳታ በበለጠ ያስፈልገዋል መለኮታዊውን ፍቅሩንና ርኅራኄውን በበለጠ በሚለግሰው በጠላት ወጥመድ ክፉኛ ለተያዙት ነፍሳት ነው፡፡CLAmh 161.3

    የሰዎችን ነፃ የመውጣት ሰነድ (መዝገብ) በደሙ አትሞታል፡፡ የሱስ በደሙ የገዛቸው ክቡር ነፍሳት የጠላት ፈተና መጫወቻ ሲሆኑ እጁን አጣምሮ አይመለከትም፡፡ እንድንሸነፍና እንድንጠፋ አይፈልግም፡፡CLAmh 161.4

    የዓናብስትን አፍ የዘጋ፤ ከታማኝ ወዳጆቹ ጋር በእሳት መካከል የተራመደ አምላክ ዛሬም ቢሆን ተከታዮቹን ከጉዳት ለማዳን ዝግጁ ነው፡፡CLAmh 161.5

    ዛሬም በምህረት መድረክ ላይ ቆሞ ርዳታ የሚጠይቁትን ጸሎት ሁሉ ወደ አብ ያቀርባል፡፡ የማንንም እንባ ሳያደርቅ አይተውም፡፡ ይቅርታ ሊጠይቁ ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ሙሉ ምሕረት ያደርግላቸዋል፡፡ የሚያደርገውን ሁሉ ለማንም ባይገልጥ የደነገጠውን ሰው ሁሉ ያበረታል፡፡ በእግዚአብሔር ለሚመካና ሰላምን ለሚሻ ሁሉ ሰላም ይሰጠዋል፡፡ ወደ እርሱ የሚጠጉትን ነፍሳት ሁሉ ከክስና ከመላስ ተናዳፊነት ይጠብቃቸዋል፡፡ ሰውም ሆነ ክፉ መናፍስት ሊጎዷቸው አይችሉም፡፡ ክርስቶስ በሰብአዊነትና በመለኮታዊነት ባሕርይው አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ ከእግዚአብሔር ዙፋን በሚፈነጥቀው ብርሃን አማካይነት በታላቁ የኃጢአት ዋስ አጠገብ ይቆማሉ፡፡CLAmh 161.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents