Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወጣቶች ለምን ትንባሆ ያጨሳሉ?

    ትንባሆ ልጆችንና ወጣቶችን በጣም ይጎዳል፡፡ ያለፈው ትውልድ በጤናው በመጫወቱ ጠንቁ ለዛሬ ልጆች ተርፏል፡፡ የአእምሮ ውድቅት፤ የአካል ድቀት፣ የነርቮች መወሳሰብ፣ አደገኛ ሱስ ከወላጅ ወደ ልጅ እንደ ውርስ ይተላለፋሉ፡፡ ያንኑ የቆየ አጉል መንገድ ልጆች ሲከተሉ ጉዳቱ እፅፍ ድርብ ይሆናል፡፡ ይህ ጠንቅ የአካልን፣ የአእምሮንና የመንፈስን ውድቀት መበላሸት ስለሚያስከትል ውጤቱ አስደንጋጭና የሚዘገንን ይሆናል፡፡CLAmh 76.4

    ወንዶች ልጆ ሲጃራ ማጨስን አስቀድመው ይጀምሩታል፡፡ ያን ጊዜ የጀመረው ሱስ አእምሮንና አካልን ካጠመደ የሰውነት ብርታት ይላሽቃል፤ የአካል እድገት ይደኩራል፤ የአእምሮ አስተሳሰብ ይወሰናል፤ ግብረገብ ይወድቃል፡፡CLAmh 76.5

    ታድያ ወላጆች መምህራንና መንፈሳውያን መሪዎች አርኣያ እየሆኑ የሚያሳዩአቸውን አጉል አድራጎት መዘዝ ለልጆችና ለወጣቶች በምን በኩል ማስረዳት ይቻል ይሆን?CLAmh 76.6

    የሕፃንነት ጊዜያቸውን ያልጨረሱ ልጆች ሲያጨሱ አይቶ ለምን ታጨሳላችሁ ቢሏቸው “አባቴ ትንባሆ ያጨሳል” ይላሉ፡፡ ቄሱን ወይም የሰንበት መምህራቸውን በመጥቀስ “እነርሱ ካጨሱ እኔ የማላጨስበት ምን ምክንያት አለ?” ይላሉ፡፤ በመሻትን መግዛት ድርጅት ውስጥ የሚያገለግሉ ብዙ ሠራተኞች የዚህ ሱስ ተገዥዎች የሆኑ አሉ፡፡CLAmh 77.1

    የዚህ ዓይነት ሰዎች የመሻትን መግዛት መውደቅ ለመናገር ምን ሥልጣን ይኖራቸዋል?CLAmh 77.2

    የእግዚአብሔርን ቃል አምነን እንታዘዛለን ለሚሉ ሁሉ እንዲህ ብዬ እማጸናቸዋለሁ፤ ክርስቲያን ሆናችሁ ማስተዋላችሁን የሚያደነዝ፣ የዘለዓለምን እውነት እንዳታስተውሉ አእምሮአችሁን የሚጋርድ ልምድ መቀጠል ትችላላችሁ? በየዕለቱ እግዚአብሔርን ማገልገል ያለባችሁን ግዴታ፤ ወገኖቻችሁን ማገልገልና ለእነርሱ አርኣያ ለመሆን የተጣለባችሁን ኃላፊነት ችላ ማለት ትችላላችሁ?CLAmh 77.3

    በእጃችሁ ላለ ሀብት ሁሉ የእግዚአብሔር መጋቢ የመሆን ኃላፊነት እዳለባችሁ አውቃችኋል? ከእግዚአብሔር ገንዘብ ስንቱን ለትንባሆ ታባክናላችሁ? በዕድሜያችሁ ሙሉ ያከሰራችሁትን የገንዘብ ልክ አስሉት፡፡ በዚህ አጉል ልምድ ያባከናችሁት ገንዘብ ወንጌልን ለማዳረስ ድኆችን ለመርዳት ካወጣችሁት ገንዘብ ጋር ሲወዳደር የትኛው ይበልጣል?CLAmh 77.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents