Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክርስቶስ ለሁሉ ይናገራል

    ይህን ቃል ክርስቶስ የተናገረው ለሁሉ ነው፡፡ ቢገነዘቡትም ባይገነዘቡትም ሁሉም ሸክም የከበደና ደካሞች ናቸው፡፡ ሁላቸውም ከክርስቶስ በቀር ማንም ሊያቀልላቸው የማይችል ሸክም አለባቸው፡፡ ከሁሉም የከበደው ሸክማችን የኃጢአት ሸክም ነው፡፡ ይህን ሸክም እኛ እንድንሸከመው ቢደረግ በደቆሰን ነበር፡፡ ግን በእኛ ፋንታ ንጹሁ ተሸከመው፡፡ “እግዚአብሔር የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረው፡፡ (ኢሣይያስ 53፡6) ፡፡ የእኛን የኃጢአት ሸክም ተሸከመ፡፡CLAmh 152.7

    ከደከመው ትከሻችን ላይ ሸክማችንን ያወርድልናል፡፡ ያሳርፈናልም፡፡ ከልቡ አያወጣንም፡፡CLAmh 153.1

    አርኣያችንና ምሳሌያችን በዘለዓለም ዙፋን ላይ ተቀምጧል፡፡ መድኃኒቴ ብሎ ወደርሱ የሚቀርበውን ሰው ሁሉ ፈቱን አያዞርበትም፡፡ እርሱም ደርሶበታልና የሰብዓዊን ፍጡር ደካማነት፤ ጉድለታችንን፤ ፈተና እንዴት እንደሚከብደን ያውቃል፡፡ “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደእኛ ተፈትኗልና” (ዕብራውያን 4፡15) ፡፡CLAmh 153.2

    የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ባትበረታም እግዚአብሔር ይመለከትሃል፡፡ ፈተና ደርሶብህ እንደሆን ይጠብቅሃል፤ ደክመህ እንደሆን ያበረታሃል፡፡ ቆስለህ እንደሆን ይጠግንሃል፡፡ መሃይም እንደሆንህ ያስተምርሃል፡፡ “እግዚአብሔር የከዋክብትን ብዛት ይቈጥራል፤ ልባቸው የቈሰሉትንም ይፈውሳል፡፡” (መዝሙር 147፡4፣3) ፡፡CLAmh 153.3

    እናት ልጅዋን ከምትወደው አብልጦ ክርስቶስ ወገኖቹን ያፈቅራል፡፡ “ሕይወቱን ስለለወጠልኝ አምነዋለሁ፤” እያልን በፍቅሩ ሥር የማረፍ መብት አለን፡፡ የሰው ፍቅር ቢለዋወጥም የእግዚአብሔር ፍቅር ግን አይለወጥም፡፡ ርዳታ ስንጠይቅ ሊያድነን እጁን ይዘረጋል፡፡CLAmh 153.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents