Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተሟላ ኑሮ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አንድም እንቢ አልተባለም

    ስለ የሱስ የተባለውን ሁሉ ያሰላስል ነበር፡፡ ማንም የየሱስን እርዳታ ፈልጎ አልተነፈገውም፡፡ ያ ጎስቋላ ሰው መድኅንን ሊገናኝ ፈለገ፤ ቆረጠም፡፡ ከከተማ ውጭ እንዲኖር ቢገደድም እንደምንም ብሎ ከከተማ ውጭ ወይም በተራራ ላይ ሲያስተምር ሊያገኘው ፈለገ፡፡ ብዙ ችግር ቢኖርበትም ተስፋው በየሱስ ላይ ብቻ መሆኑ ገባው፡፡CLAmh 150.4

    ከሩቅ ቆሞ ከየሱስ ንግግር አንዳንዱን ይሰማ ነበር፡፡ የሱስ እጁን በበሽተኞች ላይ ሲጭን አየው፡፡ አንካሶች፣ ዕውራን፣ ሽባዎች፣ በአጋንንት የተያዙ ሁሉ ሙሉ ባለጤኖች ሆነው ከሞት ሲድኑ ተመለከተ፡፡ ያን ጊዜ ሃይማኖቱ ጸና፡፡ ቀስ በቀስ ወደ ጉባዔው ቀረበ፡፡ የተጣለበት ገደብ (መታገድ) የሕዝቡ ደኅንነት፤ ሰዎች ስለራሱ የሚሠነዝሩበት ምፀትና አሽሙር ሁሉ ተረሳው፡፡ ያን ጊዜ ያስብ የነበር ስለተባረከው የመዳን ተስፋ ብቻ ነበር፡፡CLAmh 150.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents