Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 4—ትምህርት ከማዳን ጋር ያለው ግንኙነት

    «የእግዚአብሔር የክብር ዕውቀት
    ብርሃን በክርስቶስ ፊት ላይ ያበራ
    ነበር፡፡»
    EDA 26.1

    ሰው በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ፊት ተገልሎ ነበር፡፡ የመታደግ (በነፍስ ደርሶ የማዳን) ዕቅድ ባይቀየስ ኖሮ ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ፊት ተለይቶ ንጋት በሌለበት የማያልቅ ጭለማ ውስጥ ወድቆ በቀረ ነበር፡፡ በአዳኙ መስዋዕትነት አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር እንደገና መገናኘት ቻለ፡፡ እርሱ ወደ አለበት በአካል መቅረብ ባንችልም፤ በኃጢአታችን ምክንያት ፊቱን ለማየት ባንችልም እንኳ አዳኝ በሆነው ታዳዚአችን የሱስ አማካይነት ወደ እርሱ ልንቀርብና ልናገኘው እንችላለን፡፡ «በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ» «እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር፡፡» 2ኛ ቆሮ 4፡6 ምዕ 5፡10EDA 26.2

    «ቃልም ሥጋ ሆነ ፀጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ ውስጥ አደረ፡፡» «በእርሱ ሕይወት ነበረች ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች፡፡» ዮሐ 1፡14፣ ምዕ 1፡4 የክርስቶስ ሕይወትና ሞት የመዳናችንና ለደህንነታችን የተከፈለው ዋጋ ለህይወታችን ዋስትና ቃል የገባልን ብቻ ሳይሆን የጥበብን ሁሉ መዝገብ ለእኛ መልሶ ለሚከፍትልን መንገድ ብቻ ሳይሆን በኤደን ውስጥ የነበሩ ቅዱሳን ከሚያውቁት በበለጠ የእርሱን ባሕሪይ በስፋትና በምጥቀት የሚገልጽልን ነው፡፡EDA 26.3

    ክርስቶስም ሰማይን ለሰው ልጅ በሚከፍትበት ጊዜ ከርሱ ዘንድ ተከፍሎ የሚወጣው ሕይወት ሰው ሰማይን ይመለከት ዘንድ የሰውን ልቦና ይከፍታል፡፡ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ዘንድ አግልሎ የሚዘጋብን ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ ነፍስ ውስጥ ያለውን እርሱን ለማወቅ ያለንን ፍላጐትና ችሎታም ያጠፋብናል፡፡ ይህ ሁሉ የክፋት ሥራ እንዳይፈፀም ነው የክርስቶስ ተልዕኮ፡፡ የነፍስ ችሎታዎች በኃጢአት ሽባ ቢሆን፣ አእምሮ ቢጨልምበት፣ ፍላጐት ቢዘጋ፣ እርሱ በፍጥነት እንዲያንሠራራ ብርታቱ ሁሉ እንዲመለስለት ለማድረግ ታላቅ ኃይል አለው፡፡ የፍጥረተ ዓለሙን ሐብት ሁሉ ይከፍትልናል፡፡ በእርሱም እነዚህን መዝገቦች ወይም ንብረቶች ለይቶ ለማስተዋልና በአግባቡ ለመያዝም የሚያስችል ኃይል እናገኛለን፡፡EDA 26.4

    ክርስቶስ «ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደዓለም ይመጣ ነበር፡፡» ዮሐ 1፡9 እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር በክርስቶስ የሱስ ሕይወት እንደሚያገኝ ሁሉ እያንዳንዷ ነፍስም በእርሱ አማካይነት ከመለኮት ኃይል ከሚወጣው ብርሃን ጨረር ታገኛለች፡፡ የእውቀት ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ኃይልም፤ ስለትክክለኛ ነገር ግንዛቤ ማግኘት፣ እግዚአብሔርን የማምለክ ፍላጐት ማደግ በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ ያኖራል፡፡ ነገር ግን ከነዚህ መሠረታዊ ሐሳቦች በተፃራሪ አንድ የሚታገል ኃይል አለ፡፡ ክፉና በጐውን የምታስታውቀውን ዛፍ ፍሬ የመመገብ ውጤት በእያንዳንዱ ሰው ኑሮ ይገለጣል፡፡ በተፈጥሮ ውስጥ እርዳታ ካላገኘ በስተቀር ብቻውን የማይችለው ወደክፉ እንዲያዘነብል የሚገፋው ኃይል አለ፡፡ ይኸንን ግፊት ለመቋቋም በነፍሱ ውስጥ አንድ ትልቅ ዋጋ ያለው ከፍተኛ መሠረታዊ ሀሳብ ነው ብሎ ከሚያስበው ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፈለገ እርዳታ ሊያገኝ የሚችለው ከአንድ ኃይል ብቻ ነው፡፡ ያ ኃይልም ክርስቶስ ነው ለሰው እጅግ የሚያስፈልገው ታላቁ ነገር ከዚያ ኃይል ጋር መተባበር ብቻ ነው፡፡ በማንኛውም ዓይነት የትምህርት ጥረት ሁሉ ይህ ትብብር ታላቁ ዓላማ ሊሆን አይገባውምን?EDA 27.1

    እውነተኛ መምህር ሁለተኛ በሆነ ሥራ የሚረካ አይደለም፡፡ አንደኛ ማዕረግ ወደሆነው ከፍተኛ ደረጃ መድረስ ሲችሉ ተማሪዎቹን ከዚያ ወደሚያንስ ዝቅተኛ ደረጃ በመምራት የሚደሰት አይደለም፡፡ ተማሪዎቹ ጐበዝ የሂሳብ አያያዝ ሠራተኛ፤ ባለሙያ የእጅ ጥበብ አዋቂ እና የተዋጣላቸው የንግድ በማድረግ ቴክኒካዊ የሆነው ዕውቀት በማካፈል ብቻ የሚረካ አይደለም፡፡ በእውነት መርሆች በመታዘዝ፣ በክብር፣ ራሱን የገዛና በንጽህና መንፈስ አና ሕብረተሰብን በሚያረጋጉና በሚያነቃቁ መርሆዎች ሊያነሳሳቸው ሐሳብ አለው፡፡ ከሁሉም በላይ ከሌሎች ሁሉ የላቀ ራስን ባለመውደድ መንፈስ ማገልገልን የመሰለ ታላቅ የሕይወት ትምህርት እንዲማሩለት ይመኛል፡፡EDA 28.1

    ባህሪን አስተካክሎ ለመግራት ፣ ነፍስ ከክርስቶስ ጋር በሚኖራት ግንኙነት፣ የእርሱን ጥበብ መመሪያ አድርጐ በመቀበል ረገድ፣ የእርሱን ኃየል የልብና የሕይወት ብርታት ለማድረግ እነኝህ መሠረታዊ ሀሳቦች ሕያው ኃይል ናቸው፡፡ ይኸንን የአንድነት ተግባር ሲፈጽም ተማሪው የጥበብን ምንጭ አገኘ ማለት ነው፡፡ በራሱ ውስጥ የራሱ ከሆኑት ክቡር ሐሳቦች ላይ ለመድረስ መቻሉን የሚረዳበት ኃይል በውስጡ ያገኛል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት እድሎች የርሱ ይሆናሉ፡፡ ከዚህ በሚኖረው ስልጠናም የሚገኘው ጥቅም ዘላለማዊነትን ወደሚያካትት ክፍለ ትምህርት ውስጥ መዝለቅ ነው፡፡EDA 28.2

    በከፍተኛ ትርጉሙ የትምህርት ሥራና የመዳን ተግባር አንድ ናቸው፡፡ ምክንያቱም በመዳን ውስጥ እንዳለው ሁሉ በትምህርትም ውስጥ «ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና እርሱም እየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡» «እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በርሱ እንዲኖር፡፡» 1ኛ ቆሮ 3፡11 እና ቆላ 1፡19EDA 28.3

    በሚለዋወጡ ሁኔታዎች ውስጥ እውነተኛ ትምህርት የኤደን ት/ቤት ዕቅድ ከነበረው ከፈጣሪ እቅድ ጋር በጽናት የሚስማማ ነው፡፡ አዳምና ሄዋን ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ በመገናኘት መመሪያ ይቀበሉ ነበር፡፡ እነሆ እኛም ከእርሱ ክብር እውቀት በክርስቶስ ፊት በኩል ብርሃን እናገኛለን፡፡EDA 29.1

    የትምህርት ታላላቅ መርሆዎች የሚለወጡ አይደሉም፡፡ «ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ፀንተው ይኖራሉ፡፡» መዝሙር 11፡8 ምክንያቱም የፈጣሪ አምላክ ባሕሪይ መሠረቱ ናቸውና፡፡ ተማሪው እነዚህን ዋና የሕይወት መቆጣጠሪያ የሆኑትን መሠረታዊ ሀሳቦች በሚገባ እንዲያስተውል ለመርዳትና ከክርስቶስ ጋር ወደሚኖረው ግንኙነት ዘልቆ ለመግባት እንዲችል ማገዝ የመምህሩ ተቀዳሚ ጥረትና የማያቋርጥ ዓላማው መሆን አለበት፡፡ ይኸንን ዓላማ የሚቀበል መምህር እንደ እውነቱ ከሆነ የክርስቶስ ተባባሪ ወይም አጋር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ የሚሠራም ነው፡፡EDA 29.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents