Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 33—መተባበር

    ‹‹ሁላችን የአንድ ቤተሰብ አባል ነን››EDA 317.1

    በባሕሪይ አመሠራረት ላይ የቤተሰብ ስበትን ያክል የሚሆን ሌላ ማራኪ ነገር የለም፡፡ የመምህሩ ሥራ የወላጆችን ጥረት የሚያግዝ እንጅ ሙሉ ለሙሉ በቦታው የሚተካ አይደለም፡፡ የልጁን አጠቃላይ ደህንነት በሚመለከት ወላጆችና መምህራን ለመተባበር ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡EDA 317.2

    የትብብር ሥራ በቤት ውስጥ ሕይወት፤ በአባትና በእናት መጀመር አለበት፡፡ ልጆቻቸውን በማሰልጠን ሂደት የጋራ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ አንድ ላይ በጋራ እየሠፉ የማያቋርጥ ጥረትም ማድረግ አለባቸው፡፡ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ፡፡ እርስ በራሳቸው የሚያበረታታቸው እርዳታ ከርሱ ያገኙ ዘንድ ይፈልጉ፡፡ ልጆቻቸው ለእግዚአብሔር እውነተኛ፣ ለመርህ እውነተኛ፣ ለራሳቸውና ከእነርሱ ጋር ለሚገናኙ ሁሉ እውነተኛ ይሆኑ ዘንድ ያስተምሯቸው፡፡ ልጆች እንዲህ ዓይነት ትምህርት ተምረው ወደ ትምህርት ቤት ሲላኩ የጥል ወይም የሁከት መነሻ አይሆኑም፡፡ ለመምሮቻቸው የሚያግዙ ረዳቶች ለተማሪ ጓደኞቻቸውም ምሳሌና ማበረታቻ ይሆናሉ፡፡EDA 317.3

    ይኸንን ሥልጠና የሚሰጡት ወላጆች መምህሩን የሚተቹ መሆን የለባቸውም፡፡ የልጆቻቸው ፍላጎትና ትምህርት ቤቱ ለሚጠይቀው ፍትህ ኃላፊነታቸውን የሚጋራላቸው በተቻላቸው መጠን ማበረታታትና ማክበር እንዳለባቸው ይሰማቸዋል፡፡EDA 317.4

    ብዙ ወላጆች እዚህ ላይ ይሳሳታሉ፡፡ በመቻኮልና መሠረተቢስ በሆነ ትችታቸው ታማኝ ራሱን መስዋዕት የሚያደርገውን መምህር የሥራ ፍላጎት ክፉኛ ይጎዱታል፡፡ ልጆቻቸው በመጥፎ ተግባር የተበላሹባቸው ወላጆች እነርሱ የናቁትና ብልሽት መምህሩ እንዲያስተካክልላቸው የማያስደስት ኃላፊነት ይጥሉበትና የራሳቸው የአሠራር ስህተትም የመምህሩን ግዳጅ ተስፋ ቢስ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ አስተዳደር ላይ የሚኖራቸው የነቀፌታ ትችት ልጆቹን አንገታቸውን ደፍተው የሚታዘዙ እንዳይሆኑ ስለሚያበረታታቸው በጥፋት ሥራ ይቀጥሉበታል፡፡EDA 318.1

    የመምህሩን ሥራ በሚመለከት ተቃውሞ ወይም አስተያየት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ መምህሩን ራሱን ለብቻው ማነጋገር የሚበጅ ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ የማይሠራ ሆኖ ከተገኘ ጉዳዩን የትምህርት ቤቱን የሥራ አመራር ወደሚመሩት አካላት እንዲቀርብ ይደረግ፡፡ ልጆቹን ደህንነታቸውን በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለሚያደርጉላቸው ሰዎች የሚኖራቸውን ከበሬታ የሚያዳክም ነገር መናገርም ሆነ መፈጸም ተገቢ አይደለም፡፡EDA 318.2

    ወላጆች ስለ ልጆቻቸው ባህሪይና አካላዊ ለውጦች ሁለንተናዊ ሁኔታዎች ያላቸውን እውቀት ከመምህሩ ጋር ቢካፈሉ ለእርሱ ትልቅ እርዳታ ነው፡፡ ብዙዎች ይኸንን አለመገንዘባቸው የሚያሳዝን ነው፡፡ ብዙ ወላጆች ራሳቸውን ግልጽ አድርገው ለመምህሩ ይኽንን መንገር ወይም ከርሱ ጋር በሥራው ለመተባበር የሚያሳዩት ፍላጎት አነስተኛ ነው፡፡EDA 318.3

    ራሳቸውን ከመምህሩ ጋር የማያስተዋውቁ ወላጆች ከስንት አንድ በመሆናቸው መምህሩ ራሱን ከወላጆቹ ጋር ማስተዋወቁ በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ የተማሪዎቻቸውን ወላጆች ቤት መጎብኘት ስለሚኖሩበት አካባቢ ሁኔታ በቂ እውቀት ሊያገኝም ይገባዋል፡፡ ስለቤተሰቦቻቸውና ስለ አሯሯራቸው ለማጥናት የግል ግንኙነት በመፍጠሩ ከተማሪዎቹ ጋር የሚኖረውን ትስስር የሚያጠብቅለት ሲሆን የተለያዩ ባሕሪያቸውና ጠባያቸውን እንዴት አድርጎ በመያዝ ለስኬታማነት እንደሚበቃ ለመማር ይችላል፡፡EDA 318.4

    ቤተሰቦችን በማጥናት ሥራ ላይ ፍላጎት ሲያሳድር መምህሩ እጥፍ ጠቀሜታን ያካፍላል፡፡ ብዙ ወላጆች በብዙ ሥራ ተጠምደው ወይም እንክብካቤ በማድረግ እጅግ ሥራ ስለሚበዛባቸው የልጆቻቸውን ሕይወት ወደ መልካም አቅጣጫ እንዲያዘነብል የማድረግ እድሉ ሳይታያቸው ይቀራል፡፡ ወላጆች እነዚህን ጠቀሜታዎችና መልካም እድሎች ሁሉ በሚገባ እንዲጠቀሙባቸው በማነሣሣት ረገድ መምህሩ ብዙ ሊረዳ ይችላል፡፡ ልጆቻቸው ጠቃሚ ወንድና ሴት ልጆች እንዲሆኑ ከፍተኛ ጉጉት ያላቸው የኃላፊነት ሸክም የከበዳቸው ሰዎችን ያገኛል፡፡ መምህሩ የእነዚህ ወላጆች ሸክም ዘወትር በማገዝ ብዙ ሊረዳቸው ይችላል፡፡ በሚኖራቸው የጋራ ውይይት ወላጆችም መምህሩም ይበረታታሉ፣ ይጠነክራሉ፡፡EDA 319.1

    ወጣቶች በማሰልጠን ረገድ የትብብር መሠረተ ሃሳብ እጅግ ዋጋ ያለው ጉዳይ ነው፡፡ ገና ከህፃንነታቸው ጀምረው የቤተሰቡ አንድ አካል መሆናቸው እንዲሰማቸው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ትንንሽ ልጆችም ጭምር በዕለት ተዕለት የቤት ውስጥ ተግባር ላይ እንዲካፈሉ ማሰልጠንና የእነርሱ እርዳታ ደግሞ እጅግ ተፈላጊና የሚመሰገን መሆኑ እንዲሰማቸው አድርጎ መምራት ያሻል፡፡ በእድሜ ከፍ ያሉት ደግሞ የወላጆቻቸው ዋና ረዳት መሆን አለባቸው፡፡ በወላጆች እቅድ ውስጥ ገብተው ኃላፊነታቸውንና ሸክሞቻቸውን በመካፈል ማገዝ አለባቸው፡፡ አባትና እናት ጊዜ ወስደው ልጆቻቸውን ያስተምሩ፡፡ እርዳታቸውን ዋጋ እንደሚሰጡት እምነት ሊጥሉባቸው እንደሚፈልጉ፤ በጓደኝነታቸው እንደሚደሰቱ በግልጽ ያሳዩአቸው፡፡ ልጆችም ምላሽ ለመስጠት የሚዘገዩ አይደሉም፡፡ በዚህም የወላጆች ሸክም የሚቃለልና ልጆችም ዋጋ ያለው ትምህርት የሚያገኙበት መሆኑ ብቻ ሣይሆን የቤተሰቡን ትስስር የሚያጠናክር ለባሕሪይ መሠረትም ጥልቀት የሚሰጥ ይሆናል፡፡EDA 319.2

    ትብብር የት/ቤቱ መንፈስና የትምህርት ቤት ሕይወት ሕግም መሆን አለበት፡፡ የተማሪዎቹን ትብብር የሚያገኝ መምህር ሥርዓትን በማስጠበቅ ረገድ እጅግ ከፍተኛ ጥቅም ያለው ድጋፍ ያገኛል፡፡ በመማሪያ ክፍል ውስጥ በሚያገለግልበት ጊዜ ረፍት የለሽ የሆነ ፀባይ ያላቸው አንዳንድ ልጆች ወደ ሥርዓት አልበኝነትና አለመታዘዝ ሲያመራ ቀና የሆነው ምግባሩ ሥራ ላይ ለመዋል መንገድ ያገኛል በእድሜ ከፍ ያሉት ለታናሾቻቸው፤ ጠንካሮችም ደካሞችን ይርዷቸው፡፡ በተቻለ መጠንም እያንዳንዱ ሰው ከሌላው በሚበልጥበት ጠንካራ ጎን ሁሉ ሌላውን ያግዘው፡፡ ይህም ለራስ ከበሬታና ጠቃሚ የመሆን መንፈስን ያበረታታል፡፡EDA 320.1

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በትምህርትነት እንደተሰጠው የትብብርን ጠቃሚነት ማጥናት ለወጣቱ ለወላጆቹ እንዲሁም ለመምህራኑም ሁሉ በጣም የሚረዳ ይሆናል፡፡ ከብዙ መግለጫዎች ውስጥ የቤተ መቅደሱን አሠራር ሁኔታ ተመልክቱ፡፡ ባህሪይን ለመገንባት ትክክለኛው ምሳሌ የነበረና ሕዝቡ በሙሉ በአንድነት የተሳተፈበት ነበር፡፡ ‹‹ሰው ሁሉ ልቡ እንዳነሳሳው መንፈሱም እሽ እንዳሰኘው›› ዘፀ 35፡21 ይሠራ ነበር፡፡ መድኅናችንም ሕዝቡን በተዓምር በሚመግብበት ጊዜ ደቀ መዛሙርት የነበራቸውን የሥራ ድርሻ አስቡ፡፡ በክርስቶስ እጅ የተባዛውን ምግብ ደቀ መዛሙርቱ ለሚጠብቀው ሕዝብ ያከፋፍሉ ነበር፡፡ የእየሩሳሌም ግምብ ከምርኮ ተመልሰው እንደገና በሚሠሩበት ጊዜ የነበረው የድህነት፣ የችግር፤ የአደጋ ሁኔታ ውስጥ ታላቁ የሥራ ግዳጅ በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ፡፡ ምክንያቱም ‹‹የሕዝቡም ልብ ለሥራው ጨከነ›› ነህ 4፡6EDA 320.2

    ‹‹እርስ በራሳችን ብልቶች ሆነናል፡፡ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተናገሩ፡፡›› ‹‹. . . የፀጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ፀጋ እርስ በራሳችሁ አገልግሉ፡፡›› ኤፌ 4፡25 1ኛ ጴጥ 4፡10EDA 321.1

    ስለ ጥንታዊያን ግንበኞች የተነገሩ ቃላት ከፍተኛ ዋጋ ካለው ዓላማ ጋር በዛሬዎቹ ባህሪይ ገንቢዎች ዘንድ በእጅጉ እንደ መፈክር ተደርገው ሊያዙ ይገባል፡፡EDA 321.2

    ‹‹እያንዳንዱ ባልንጀራውን ይረዳው ነበር ወንድሙንም አይዞህ! ይለው ነበር፡፡›› ኢሳ 41፡6EDA 321.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents