Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በመሞት የሚገኝ ሕይወት

    የዘሩ አዘራርና አበቃቀል ጉዳይ የነፃነትን ትምህርት ያስተምራል፡፡ «በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፡፡ በበረከት የዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል፡፡» 1ኛ ቆሮን 9፡6EDA 119.2

    ጌታ እንዲህ ይላል «በውኃ ሁሉ አጠገብ የምትዘሩ ብፁአን ናችሁ፡፡» ኢሳ 32፡24 በውሃ ሁሉ አጠገብ መዝራት ማለት እርዳታችን በሚፈለግበት ቦታ ሁሉ መስጠት ማለት ነው፡፡ ይህ ወደ ድህነት የሚያወርድ ማለት አይደለም፡፡ «በበረከት የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል» ዘሪው ፍሬዋን መሬት ላይ በመጣል እንድትባዛ ያደርጋታል፡፡ ስለዚህ እኛም ከፍለን በመስጠት በረከቶችን እናበዛለን፡፡ መስጠትን እናዘወትር ዘንድ የሚያስተምረን የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሉ በረከት እንደሚጨምርበት አረጋግጦልናል፡፡EDA 119.3

    ከዚህም በላይ የዚህን ሕይወት በረከቶች ባካፈልን መጠን በተቀባዩ በኩል የሚቀርበው ልባዊ ምስጋና ልብ መንፈሳዊ እውነታን መቀበል እንድትችል አዝመራውም ለዘላለማዊ ሕይወት የሚያበቃ እንዲሆን አድርጐ ያዘጋጀዋል፡፡EDA 119.4

    የዘር ፍሬን ወደ መሬት የመጣል ትምህርት መድህናችን ራሱን ለእኛ መስዋዕት እንደሚያደርግ በምሳሌ የተናገረው ነው፡፡ «የስንዴ ቅንጣት በምድር ላይ ወድቃ ካልሞተች በስተቀር» ይላል «ብቻዋን ትቀራለች ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች፡፡» ዮሐ 12፡24 ዘሩ ለእግዚአብሔር መንግሥት የሚያበቃ ሙሉ ፍሬ መስጠት የሚችለው በክርስቶስ መስዋዕትነት በኩል ብቻ ነው፡፡ በጓሮ አትክልቶች ዘር ሁሉ ባለው ሕግ እንደሚሆነው ሁሉ ሕይወት የርሱ ሞት ውጤት ነው፡፡EDA 120.1

    ፍሬን ሁሉ ከሚሰጠው ከክርስቶስ ጋር ለሚሰሩ ሁሉ የራስ ፍቅርን የግል ፍላጐትን ማጥፋተ አለባቸው፡፡ ሕይወት የዓለም ፍላጐት በሆነው ማሳ ላይ መጣል አለባት፡፡ ራስን መስዋዕት የማድረግ ሕግ ግን ራስን የመጠበቅ ሕግ ነው፡፡ ዘሪው የስንዴዋን ፍሬ መሬት ላይ በመጣል ይጠብቃታል፡፡ ስለዚህም መጠበቅ ያለበት ሕይወት ለእግዚአብሔርና ለሰው አገልግሎት በነፃ የምትሰጥ ሕይወት ናት፡፡EDA 120.2

    ወደ አዲስ ሕይወት ለመሸጋገር ትችል ዘንድ ዘራት፡፡ በዚህም ትንሳኤ መኖሩን እንማራለን፡፡ እንዲበሰብስ ወደጨለማ መቃብር የተጣለ የሰው ሰውነት «በመበስበስ ይዘራል ባለመበስበስ ይነሳል፡፡ በውርደት ይዘራል በክብር ይነሳል፡፡ በድካም ይዘራል በኃይል ይነሳል፡፡» 1ኛ ቆሮ 15፡42‚43EDA 120.3

    ወላጆችና መምህራን እነኝህን ትምህርቶች ለማስተማር በሚሞክሩበት ጊዜ ሥራ ሥራው ተግባራዊ መሆን አለበት፡፡ ልጆቹ ራሳቸው መሬቱን አዘጋጅተው ዘሩን እንዲዘሩ ይደረግ፡፡ እየሠሩ እያለ ወላጁ ወይንም መምህሩ የልብን ማሳ በግልጽ ያብራራው በዚያ ላይ ለሚዘራው ጥሩ ወይም መጥፎ ዘር ምቹ ይሆንለታል፡፡ ማሳው ለተፈጥሮ ዘር መዘጋጀት እንዳለበት ሁሉ ልብም በእውነት ዘር መዘጋጀት አለባት፡፡ ዘሩ ወደመሬት እየተጣለ እያለ ስለክርስቶስ ሞት አስተምሯቸው ቡቃያው ብቅ ማለት እንደጀመረ የትንሳኤን እውነትነት አስረዷቸው፡፡ እያደገች በሄደች ቁጥር በተፈጥሮና በመንፈሳዊው አዘራር መካከል ያለው ዝምድና ያለማቋረጥ ይቀጥላል፡፡EDA 120.4

    ወጣቱም በተመሳሳይ መንገድ መመራት አለበት፡፡ መሬቱን ከማረስ ጀምሮ ትምህርቱ ያለማቋረጥ መስጠት አለበት፡፡ ማንም ሰው ገና ምርት አገኛለሁ ብሎ በአዲስ መሬት ላይ የሚሰፍር የለም፡፡ ያላሰለሰ ትጋት የተሞላበት በመሬት ላይ ብዙ የእንክብካቤ ሥራ በዘሩ አዘራርና በአዝመራ አሰባሰብም ላይ ብዙ ሥራ መከናወን አለበት፡፡ በመንፈሳዊዩ ዘርም እንደዚሁ ነው፡፡ የልብ ማሳ መኮትኮት አለበት፡፡ መሬቱ ላይ ያለው ጓልም ንስሐ በመግባት መከስከስ አለበት፡፡ መልካሙን ስንዴ የሚያፍነው አረም ከሥሩ መነቀል አለበት፡፡ ባንድ ወቅት እሾክ በቅሎበት የነበረ መሬት በትጋት በመሥራት ብቻ ሊፀዳ እንደሚችል በልብ ውስጥ ያሉ ጠማማ የክፋት ዝንባሌዎችም በክርስቶስ ስምና በርሱ ብርታት አማካይነት በሚደረግ ልባዊ ጥረት ብቻ ነው ሊሸነፍ የሚችለው፡፡EDA 121.1

    መሬቱን በሚኮተኩትበት ጊዜ ጐበዝ ሠራተኛ ያላሰበውን የሲሳይ መዛግብት እንደተከፈቱ ያገኛል፡፡ በእርሻ ሥራ ውስጥ ወይም በጓሮ አትክልት ሥራ ላይ በውስጡ የሚካተቱትን ሕጐች በሚገባ ካላጤነ ማንኛውም ሰው አይሳካለትም፡፡ የእያንዳንዱ የተለያየ የአትክልት ዝርያ መጠናት አለበት፡፡ የተለያዩ ዝርያዎች የተለያዩ የአፈር አይነቶች እና የተለያየ አያያዝ ወይም ኩትኳቶ ይፈልጋሉ፡፡ ከዚህም ጋር እያንዳንዳቸውን የሚገዛቸውን ሕግ ማወቅ ለስኬታማነት ይረዳል፡፡ ችግኙን አዛውሮ በመትከልም ላይ የሚያስፈልገው ጥንቃቄ አንዲት ጭራ የምታክል ሥር እንኳ እንዳትጨቆን ወይም ያለቦታዋ እንዳትሆን ማድረግ ለቡቃያው መጠንቀቅ መለምለም ማረምና ውሃ ማጠጣት ከማታ ቁር መከላከልና ከቀን ፀሐይ መጠበቅና ከበሽታና ከልዩ ልዩ ተባዮች መከላከል መግረዝና ማስተካከል የባህሪን ዕድገት በሚመለከት ጠቃሚ ትምህርቶች የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ሥራው ራሱ ለልማት የሚጠቅም መንገድ ነው፡፡ በኩትኳቶ ወይም በእንክብካቤ ሥራ ውስጥ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን ትዕግሥተኛ እያንዳንዷን ጥቃቅን ነገር በዝርዝር መከታተል ለሕግ መታዘዝ ትልቅ ትምህርትን እና በሥራውም ላይ ሥልጠናን ይሰጣል፡፡ ከሕይወት ሚስጥር ጋር ያላቋረጠ ግንኙነት እና የተፈጥሮ ተወዳጅነት ለእነኝህ የእግዚአብሔር የሚያምሩ ውብ ፍጥረቶች አገልገሎት ለመስጠት በርህራሄ መነሳት አአምሮን ቀልጣፋና ብሩህ እንዲሆን ወደማድረግ የሚያመራና ባህሪን የሚያነሳሳ ይሆናል፡፡ ከዚህ የሚገኙ ትምህርቶችም ሠራተኛው የሌሎች ሰዎችን አአምሮ ጥሩ አድርጐ በተሳካ መልኩ ለመያዝ እንዲችል ያዘጋጀዋል፡፡EDA 121.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents