Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 6—የነቢያት ትምህርት ቤቶች

    «በእግርህ ሥር ተቀመጡ
    እያንዳንዱ ከሥራህ ያገኛሉ፡፡»
    EDA 46.1

    የእግዚአብሔር የትምህርት ፈቃድ በመላው እስራኤል ተግባራዊ ይሆን ነበር፡፡ ውጤቶቹም የአዘጋጂውን ችሎታ ይመሰክራሉ፡፡ ነገር ግን ከብዙ ቤተሰቦች መካከል በሰማዩ አምላክ የሚሰጠው ሥልጠና የባሕሪያቸው ብስለት እየታየ ስለሚሆን የሚመረጠው በስንት አንድ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ዕቅድ ተለይቶና በትክክል የሚፈፀም ነበር የእግዚአብሔርን መመሪያ ባለማመንና ችላ በማለት እስራኤላዊያን ከጥቂቶቹ በስተቀር ሊቋቋሙት በማይችሉት ፈተና ውስጥ ራሳቸውን አስገቡ፡፡ «እግዚአብሔር እንዳላቸው አህዛብን አላጠፉም፡፡ ከአህዛብ ጋር ተደባለቁ ሥራቸውንም ተማሩ፡፡ ለጣኦቶቻቸውም ተገዙ ወጥመድም ሆኑባቸው ነገር ግን እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምህረቱን አደረገ ኃጢአታቸውንም ይቅር አላቸው እንጅ አላጠፋቸውም፡፡ ብዙውን ጊዜ ቁጣውን መለሰ ብዙውን ጊዜ መዓቱን ገታ ካለፈ በኋላ እንደማይመለስ ነፋስ ሥጋ እንደሆነ አሰበ፡፡» መዝ 106፡3436 ምዕ 78፡37-39፡፡ እስራኤላዊያን እናቶችና አባቶች እግዚአብሔር ላስቀመጣቸው ግዴታዎች ደንታቢሶች ሆኑ የነበረባቸውን ግዴታ መወጣትና ልጆቻቸውንም ጭምር ችላ አሉ በቤታቸው ውስጥ ሃይማኖት የሌላቸው በመሆንና ልቅ ዘማዊ በመሆን ከእብራዊያን ወጣቶች አብዛኛዎቹ እግዚአብሔር ካቀደላቸው እጅግ የራቀና የተለየ ትምህርት ተቀበሉ፡፡ የአረመኔዎችን ትምህርት ተከተሉ፡፡EDA 46.2

    በትምህርት አሰጣጥ ሥራ ውስጥ ወላጆችን ለመርዳትና ይህን እያደገ የመጣ የሀጢአት ሥራ ለመቋቋም እንዲረዳ እግዚአብሔር ሌሎች ተቋሞችን መሠረተ፡፡ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ነቢያት ከመለኮት የተመረጡ መምህራን እንደሆኑ ታውቋል፡፡ በእውነተኛ ትርጉሙ ነቢይ ማለት በመንፈስ ተነቃቅቶ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን መልዕክት ለህዝቡ የሚያደርስ ልዑክ ማለት ነው፡፡ ይህ ስያሜ ግን እንዲህ በመንፈስ ተነቃቅተውና ተነሳስተው ለሚሰሩት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ሥራና መንገዶች ለሕዝቡ እንዲያስተምሩ በቀጥታ በመለኮት ለተመረጡትም ጭምር ያገለግላል፡፡ ለእንዲህ ዓይነት የመምህራን መደብ ሥልጠና የሚያገለግሉ የነቢያት ትምህርት ቤቶችን ሣሙኤል በጌታ ትዕዛዝ አቋቋመ፡፡EDA 47.1

    እነኝህ ት/ቤቶች እየተስፋፋ የሄደውን፣ በሀጢአት የመበከል ተግባር ለመገደብና ለወጣቱ ሕሊናዊና መንፈሳዊ ደህንነት ለማስገኘት፤ እንዲሁም በፈሪሀ እግዚአብሔር መንፈስ ለመሥራት የሰለጠኑ ሕዝቡን ለብልጽግና የሚያበቁ መሪና መካሪ ሰዎችን ለማፍራት እንዲቻል ታስቦ የተቋቋሙ ትምሀርት ቤቶች ናቸው፡፡ ለዚህ ዓላማም ሣሙኤል ብሩህ ልቦና ያላቸውን ከልባቸው የፀና ዕምነት ያላቸውን ታታሪ ወጣቶችን በቡድን በቡድን ሰብስቦ ማስተማር ጀመረ እነሱም የነቢያት ልጆች ይባሉ ነበረ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃልና ሥራዎችን እያጠኑ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ሳለ ሕይወት የሚሰጠው የርሱ ኃይል የአእምሮአቸውንና የነፍሳቸውን ብርታት አፋጠነው፡፡ ተማሪዎቹም ጥበብን ከላይ ተቀበሉ፡፡ አስተማሪዎቹም በመለኮት እውነት የተካኑ በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር በመገናኘታቸው በውስጣቸው ደስታ የተሞሉም ነበሩ፡፡ የተለየ የመንፈስ ቅዱስ በረከት ችሎታና ብቃት ታድሏቸው ነበር፡፡ ለመማርና ልባቸውን ለእግዚአብሔር ለማስገዛት የሕዝብን አመኔታና ክብር አግኝተው ነበር፡፡ በሣሙኤል ጊዜ የዚህ ዓይነቶቹ ትምህርት ቤቶች ሁለት ነበሩ፡፡ አንደኛው የነቢዩ አገር በነበረው በራማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በኪሪጃስኪሪም ነበር፡፡ ቆይቶ ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ተቋቋሙ፡፡EDA 47.2

    በዚህ ት/ቤት ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች በቆይታ ጊዜአቸው ራሳቸውን በመርዳት በእርሻ ወይም በሌላ የእጅ ሥራ ነበር የሚተዳደሩት፡፡ በእስራኤላዊያን ዘንድ ይህ ዓይነት አስተዳደግ እንደእንግዳ ነገር ወይም በንቀት ዝቅ ተደርጐ የሚታይ አልነበረም፡፡ እንዲያውም ልጆችን የሚጠቅም ተግባር ሳያስተምሩ ማሳደግ እንደሀጢአት ይቆጠር ነበር፡፡ ማንኛውም ልጅ ወላጆቹ ሀብታም ይሁኑ ድሀ ትንሽ ንግድ ዓይነት ነገር እንዲሞክር ትምህርት ይሰጠው ነበር፡፡ ለተቀደሰ ሥራ የቢሮ ኃላፊነት የሚማር ልጅ እንኳ ቢሆን ለከፊል ሕይወቱ የተግባር እውቀት ማግኘቱ የበለጠ ትልቅ ሰው እንዲሆን እንደሚረዳው ይታመን ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ መምህራንም ቢሆኑ በዚሁ ዓይነት የእጅ ሥራ ራሳቸውን ይረዱ ነበር፡፡EDA 48.1

    በትምህርት ቤትና በቤትም ውስጥ አብዛኛው ትምህርት የሚሰጠው በቃል ነበር፡፡ ወጣቶች ግን የእብራዊያንን ጽሁፎች ማንበብ ይማሩ ነበር፡፡ የብሉይ ኪዳን ጥቅል ብራናዎችና መጽሐፎች ሁሉ ለጥናት ተከፍተውላቸው ነበር፡፡ በእነኝህ ት/ቤቶች ውስጥ ይሰጡ የነበሩ ዋና ዋና ትምህርቶች የእግዚአብሔር ሕግ፤ ለሙሴ ከተሰጠው ትዕዛዝ ጋር በቅድስና ታሪክ መዛግብት ውስጥ የጀሆቫ ዱካዎች ታሪክ ክትትል ተደርጐባቸዋል፡፡ በቤተመቅደስ አገልግሎት ውስጥ ይገለፁ የነበሩ ታላላቅ እውነቶች ቁልጭ ብለው እንዲስተዋሉ ይደረግ ነበር፡፡ የዚያ ሥርዓት ሁሉ ዋና ዓላማ የሆነው የዓለምን ሀጢአት ሁሉ እንዲያስወግድ የተደረገው የእግዚአብሔር በግ በፀና እምነት ተይዞ ነበር፡፡ ልብን የሚገዛ የፀሎት መንፈስም በዚያ ቦታ እጅግ የሚወደድ ልማድ ነበር፡፡ ተማሪዎች ፀሎት ማድረግን ብቻ አልነበረም የሚማሩት እንዴት መፀለይ እንዳለባቸው፤ ወደ ፈጣሪያቸው እንዴት ብለው መቅረብ እንዳለባቸው በእርሱ ላይ እምነት መጣልን እንዴት አድርገው ሊለምዱ እንደሚችሉ ፣ የመንፈስ ቅዱስን ትምህርቶች እንዴት ማስተዋልና መታዘዝ እንደሚችሉ ጭምር ትምህርት ይሰጣቸው ነበር፡፡ የተቀደሰ እውቀት ከእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አዲስ አዳዲስና ጥንታዊ የሆኑ ልዩ ልዩ መዝገቦችን ያመጣ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስም በትንቢትና በተቀደሰ መዝሙር አማካይነት ይገለጥ ነበር፡፡EDA 48.2

    እነኝህ ትምህርት ቤቶች «ከአህዛብ ሁሉ የበለጠውን» ምሳ 14፡34 ጽድቅን በማስተላለፍ በኩል እጅግ ዋነኛ መንገዶች መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡ የዳዊትና የሰለሞን ዘመነ መንግስቶች ያደረጓቸውን ግሩም ድንቅ ብልጽግናዎች ለማስገኘት በተጣለው መሠረት ላይ ያበረከቱት አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡EDA 49.1

    በነቢያት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በትምህርትነት ይሰጡ የነበሩ መሠረተ ሀሳቦች ቀደም ሲል ይሰጡ የነበሩ የዳዊት ባህሪ ያስተካከሉ፤ ሕይወቱንም የቀረፀለት ትምህርቶች ነበሩ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የእርሱ አስተማሪ ነበር፡፡ በሀሳቦችህ ይላል ዳዊት «ከሕግህ ጥበብን አግኝቻለሁ፤ ... ሕግህ ዘላለማዊ ሀብቴ ነው፡፡» መዝ 119፡104-112 ጌታ ዳዊትን ገና በወጣትነቱ ወደዙፋን እንዲመጣ የጠራው ይኸንኑ በማየት ነው፡፡ «ዳዊት እንደልቤ የሆነ ሰው» እስከማለትም ደርሷል፡፡ የሐዋ፡ ሥራ 13፡22EDA 49.2

    በሰለሞን የመጀመሪያ የሕይወቱ ዘመናትም እንዲሁ የእግዚአብሔር የትምህርት ዘዴዎችና ውጤታቸው ታይተዋል፡፡ ሰለሞን በወጣትነቱ የዳዊትን ምርጫ አይቶ እሱም ያንኑ ምርጫ ተከተለ፡፡ በምድር ከሚገኘው ሀብትና ንብረት ሁሉ ይልቅ እግዚአብሔር ጠቢብና አስተዋይ ልብ ይሰጠው ዘንድ ጠየቀ፡፡ ጌታም ሰለሞን የተመኘውን ብቻ ሳይሆን ያላሰበውን ሁሉ ክብርንም ሀብትንም አሟልቶ ሰጠው፡፡ የማስተዋሉ ኃይል፣ የእውቀቱ ዝና የመንግሥቱ ክብርም በዓለም የሚደነቅ ሆነ፡፡EDA 49.3

    በዳዊትና በሰለሞን ዘመነ መንግሥታት እስራኤል እጅግ በጣም ኃያል አገር ሆነች፡፡ ለአብርሃምና ለሙሴ በተደጋጋሚ የተሰጠው ተስፋ ተግባራዊ ሆነ፡፡ «አምላካችሁ እግዚአብሔርን ትወዱ ዘንድ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፤ ከእርሱ ጋር ትጣበቁ ዘንድ፣ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትዕዛዝ ሁሉ ብትጠብቁ ብታደርጉትም እግዚአብሔር እነዚህን አህዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣል ከእናንተ የሚበልጡትንም የሚበቱትንም አህዛብ ትወርሳላችሁ፡፡ የእግራችሁ ጫማ የምትረግጣት ሥፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፡፡ ከምድረበዳም ከሊባኖስም ከታላቁም ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባህር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል፡፡ በእናንተም ፊት ማንም መቆም አይችልም፡፡» ዘዳግም 11፡22-25EDA 50.1

    ነገር ግን በብልጽግና መካከል አንድ አደጋ አድፍጦ ይጠብቃቸው ነበር፡፡ ወደኋለኛዎቹ ዘመኖች ዳዊት በሠራው ኃጢአት ከልቡ የተናዘዘና የተፀፀተ፤ ክፉኛ የተቀጣበት ቢሆንም ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዞች እንዲጥስ አደፋፍረውታል፡፡ የሰለሞን ሕይወትም ከአንድ የታላቅ ተስፋ ንጋት በኋላ በአመጽ ጨለመ፡፡ የፓለቲካ ኃይል ለማግኘትና ሐብት ወይም ግዛት የማጋበስ ፍላጐት ከአረማዊያን ጋር ወደማበር አመራ፡፡ የጠርሽሽ ብርና የኦፊር ወርቅ፣ ለሀገሮች ውህደት ሲባል የተቀደሱ እምነቶችን በመሸጥ ለግዛት አንድነት ተለወጡ፡፡ ከጣኦት አምላኪዎች ጋር ሕብረት መፍጠር፣ ሃይማኖት የለሽ አረመኔ ሴቶችን ማግባት የእሱን እምነት አረከሰው፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ለራሱ ሕዝብ አቁሞአቸው የነበሩ መከላከያ ገደቦች ተጣሱ፡፡ ሰለሞንም ሕይወቱን ለሀሰተኛ አምላክ ጨርሶ አስረከበ፡፡ ከኦሊቭ ተራራዎች ጫፍ ላይ ከአምላክ ቤተመቅደስ ትዩዩ ግዙፍ ምስሎችና ለአረማዊያን ጣኦቶች መሥዋዕት ማዘጋጃ ገንዳዎች ተሰሩ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ትስስር እንደጣለ ሰለሞን ወዲያውኑ ራሱን መቆጣጠር ተሳነው፡፡ ያ ግሩም ንቃቱ ፈዘዘ፡፡ መጀመሪያ እንደነገሰ አካባቢ በነበሩት ዓመታት የነበረው ሚዛናዊ የዳኝነት መንፈሱ ተለወጠ፡፡ ኩራት ከፈተኛ ምኞት፤ የአዋቂ አጥፊነት በኩንነት፤ ዝና ፈላጊነት፤ የጭካኔ ፍርደ ገመድልነትን አመጣ፡፡ ያን የመሰለ ቅን ዳኛ ትሁት እግዚአብሔርን የፈራ የነበረ መራ ጨካኝና ጨቋኝ ገዥ ሆነ፡፡ ያ ቤተመቅደሱን ሠርቶ ለእግዚአብሔር ለማስረከብ ሲል ሕዝቦቹ ለቦናቸው ሳይከፋፊል ለጌታ ይሰጡ ዘንድ ይፀለይ የነበረ ሰው አሁን ለሀጢአት ሥራ የሚያባብላቸው ሆነ፡፡ ሰለሞን የራሰንም የአስራኤልንም የአግዚአብሔርንም ክብር አዋረደ፡፡EDA 50.2

    ለሕዝቡ ክብራቸው ኩራታቸው ነበረና አመራሩን ተቀብለው ተከተሉ፡፡ ምንም እንኳ ወደኋላ ዘመናት ቢናዘዝም የእሱ መናዘዝ የዘራውን የሃጢአት ዘር ፍሬ ከማፍራት አሳስከረውም፡፡ እግዚአብሔር ለእስራኤላዊያን የሥነ ሥርዓት ሥልጠና በሕይወት መንገዳቸው ሁሉ ከሌሎች ሕክቦች የተለዩ እንዲሆኑ የሚያደርጓቸው ነበሩ፡፡ እንደልዩ ጥቅሞችና በረከቶች ይቆጠሩ የነበሩ እነኝህን መለያቸውን ሊጠበሉት አለፈቀዱም፡፡ ይህ ራሳቸውን ያስከብር የነበረ ያኗኗር ዘይቤና ለተመኙት ልማት እጅግ ይጠቅማል ብለው ያሰቡት ነበር በአረመኔዎች ያሸበረከ የአደባባይ የታይታ ሥራ ተገፋፍተውና ተማርከው ለመለወጥ አሰቡ፡፡ ‹እንደ አህዛብ ሁሉ ለመሆን ....ፈለጉ› 1ኛ ማሙ 8፡5፡፡ የእግዚአብሔር ትምህርት እቅድ ወደጐን ተጣለ ሥልጣኑንመ ገሸሸ አደረጉ፡፡EDA 51.1

    የእግዚአብሔር መንገዶች በመቃወም የሰውን መንገድ መምረጥ ሲጀምሩ የእስራኤላዊያን ውድቀትም አብሮ ጀመረ፡፡ እንዲ እያለ እየቀጠለ ሲሄድ የይሁዳ ሕዝብ የአምልኮ አሠራራቸውን የተከተሉላቸው የጐረቤት ሕዝቦች ምርኮኞች እስከመሆን ደረሱ፡፡EDA 51.2

    የእስራኤል ልጆች፣ እንደአንድ ሕዝብ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ያስበውን በረከት መቀበል አልፈለጉም፡፡ ዓላማዉን አድንቀውና አመስግነው አልተቀበሉትም፡፡ ወይም በአፈፃፀሙ አልተባበሩም፡፡ ምንም እንኳ ግለሰቦቹና ሕዝቦች ራሳቸውን ከእርሱ ቢለዩም እርሱን ለሚያምኑት ግን አይለወጥም፡፡ «እግዚአብሔር ያደረገው ነገር ሁሉ ለዘለዓለም እንዲኖር አወቅሁ፡፡» መክ 3፡14EDA 52.1

    በተለያዩ ዘመናት የነበሩ የሰዎችን ፍላጐት ለማሟላት ለተለያዩ የእድገት መጠንና የተለያዩ የርሱ ኃይል መግለጫዎች ያሉና የነበሩ ቢሆንም በዘመናት ሁሉ የነበረው የእግዚአብሔር ባሕሪይና እቅዱ ያው ናቸው፡፡ በርሱ ዘንድ «መለዋወጥ የለም፡፡ እንደጥላ አይዞርም፡፡» ያዕ 1፡17EDA 52.2

    እስራኤላዊያንን ያጋጠማቸው ነገር ሁሉ ለእኛ ትመህርት የሚሆን ነው፡፡ «ይህ ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገስፀን ተፃፈ፡፡» 1ኛ ቆሮ 10፡11 በጥንት ዘመን በእስራኤል ላይ እንደሆነው ሁሉ እኛም በዚህ ትመህርት ስኬታማነትን ለማግኘት የምንችለው የፈጣሪን ዕቅድ ለማስፈፀም በሚኖረን ታማኝነት ነው፡፡ እግዚአብሔርን ቃል መሠረታዊ ሀሳቦች አምኖ መቀበል ለእብራዊያን ሕዝብ ያመለጣቸውን ታላቅ በረከቶች ለእኛ ያመጣልናል፡፡EDA 52.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents