Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 9—የማስተማሪያ ዘዴዎቹ መግለጫ

    «አንተ የሰጠኸኝ ስም ለነሱ ገለጥሁላቸው»EDA 91.1

    እንደ አንድ መምህር የክርስቶስ ፍፁም የሆነውና የተሟላው የማስተማሪያ ዘዴዎች መግለጫ የተገኘው ለመጀመሪያ አሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት በሰጠው ስልጠና ላይ ነው፡፡ በአነዚህ ሰዎች ላይ ከባድ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር፡፡ በርሱ መንፈስ የሚሞሉ እንደሚሆኑ በማመንና እርሱ በዚህ ዓለም ላይ ሥራውን ካቆመበት ጀምረው ወደፊት ለመሸከም ተገቢ እንደሚሆኑ በማመን መርጧቸዋል፡፡ ከሌሎች በተለየ ሁኔታ ለእነሱ የአርሲ የራሱ ጓደኞች የመሆንን ጥቅም ሰጣቸው፡፡ በግላዊ ጓደኝነት በእነኝህ በተመረጡት ባልንጀሮቹ ላይ ራሱን አሳደረባቸው፡፡ «ሕይወት ተገለጠ፡፡» ይላል፡፡ ተወዳጅ ዮሐንስ «በዐይናችንም አይተን መስክረናል፡፡» 1ኛ ዮሐ 1፡2EDA 91.2

    በእንዲህ ዓይነት ግንኙነት ብቻ ያ መካፈል ያለበት የእውነተኛ ትምህርት ሥራ የሆነው ዋና ኃይል ሲኖር ሰብዓዊ ከመለኮታዊ አእምሮ ለአእምሮ ልብ ለልብ የሆነ ግንኙነት ሊፈጠር የሚችለው፡፡EDA 91.3

    ደቀ መዛሙርቱን በሚያስለጠንበት ጊዜ የዓለም መድህን ገና ጥንት በዓለም መጀመሪያ ላይ የተመሠረተውን ሥርዓተ ትምህርት ተጠቀመበት፡፡ የተመረጡት አሠራ ሁለቱና ሌሎችም ጥቂቶች ለራሳቸው ፍላጐት በማገልገል የተሳተፉ ሰዎች አንድ ላይ ሆነው ከጊዜ ወደጊዜ የየሱስን ቤተሰብ መሠረቱ፡፡ በቤት ውስጥም በምግብ ጠረጴዛ ዙሪያም፣ በጠባብ ክፍል ውስጥ በመስከም አብረውት ነበሩ፡፡ በጉዞ ላይ አብረውት ይሄዳሉ፡፡ ዱካውንና ችግሩን ሁሉ አብረውት ይካፈላሉ፡፡ ይህም እነርሱን የጠቀማቸውን ያክል ለእርሱ ሥራም አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡EDA 91.4

    አንዳንድ ጊዜ በተራራው ላይ እንደተቀመጡ ያስተምራቸዋል፡ አንደንድ ጊዜ ደግሞ በባህር ዳርቻ ሆነው እያሉ ወይም በአሳ አጥማጁ ጀልባ ላይ ሆኖ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በመንገድ ላይ አየሄዱም ያስተመራቸዋል፡፡ የትመ የት ቢሆን ለተሰበሰበው ሕዝብ ሲናገር ደቀመዛሙርቱ ከፊቱ የመጀመሪያው ረድፍ ላይ ከበውት ይቀመጣሉ፡፡ ከትመህርቱ አንዷም ነገር እንዳታመልጣቸውም ተጠጋግተው ስብስብ ይላሉ፡፡ እውነቶችን ለሀገር ሁሉና በሁሉም የእድሜ ደረጃ ለሚገኙ ሁሉ ለማስተማር እንዲችሉ ባላቸው ጉጉት በትጋት ያዳምጡት ነበር፡፡EDA 92.1

    የመጀሪያዎቹ የየሱስ ሰዎች የተመረጡት ከተራው ሕዝብ መካከል በደረጃ ነው፡፡ ትሁትና ያልተማሩ ነበሩ፡፡ አነኝህ የገሊላ አሳ አጥማጆች የረቢያዊያንን ትምህርትና ልማድ ያልተከታተሉ ነገር ግን በሥራ በልፋት በድካም ሥርዓት የሠለጠኑ ነበሩ፡ ብሩህ ያልተነካ ሕሊናና ችሎታ ቀና የመማር መንፈስ ያላቸው ነበሩ፡ ለመድህን አገልግሎት የሚስማሙ መንፈስ ያላቸው ነበሩ፡፡ ለመድህን አገለግሎት የሚስማሙ ቢያስተምሯቸው የሚቀበሉና የሚታነፁ ነበሩ፡፡ በተለመደው የሕይወት ኑሮ ውስጥ በዙሀን ሠራተኞች የርሱን የየቀን የሥራ ተግባሩን በትዕግስት እየተከታተሉ ለሥራ የሚያነሳሳውን ታላቅ የብርሃን ኃይል በታላላቅ የዓለም መሪዎች መካከል እንደሚያስመድበው ሳያውቁ ይረዱት ነበር፡፡ የርሱ ተባባሪዎች ይሆኑ ዘንድ በዓለም መድህን የተጠሩት እንዲህ ዓይነት የዋህ ሰዎች ዓለም አይታ በማታውቀው እጅግ ታላቅ መምህር ሥር በሦስት ዓመትት ያክል የስልጠና እድል አግኝተው ነበር፡EDA 92.2

    በእነዚህ የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ኑሮ ውስጥ ልዩ ሁኔታ ታየባቸው፡፡ ወደፊት የዓለም መምህራን እንዲሆኑ የታሰቡ ነበሩ፡፡ በጣም በሰፊዉ የተለያዩ ችሎታዎችና ባህሪያት ያሏቸው ነበሩ፡፡ እንደሌዋዊው ማቴዎስ የመሰሉ ሕዝባዊ የሆኑም ነበሩበት፡፡ ከተራ ሥራ የተጠሩ ናቸው፡፡ የሮማ አገልጋይ የነበረ፡፡ ቀናተኛው ሲሞን ጠላቶቹ ከነበሩት ንጉሣዊያን ባለሥልጣኖች ጋር ድርድር የማይመከረው ምልስ የሆነውና ለራሱ የሚበቃውን ብቻ የሚያስበው የጋለ ልብ የነበረው ጴጥሮስ ከወንድሙ ከእንደርያስ ጋር የነበረው ይሁዳ፤ ሰሙንሙን ትልቅ ችሎታ ያለው ግን ደካማ መንፈስ የነበረው ሲሆን ፊሊጶስና ቶማስ ታማኝና ቀና ሲሆኑ ነገር ግን ለማመን ዳተኛ ልብ ያላቸው ነበሩ፡፡ ያዕቆብና ዮዲ ከታዋቂ ወንድማማቾች መካከል ታናናሾቹ ናቸው ነገር ግን የኃይልና የቀልጣፋ አስተሳሰብ ባለቤቶች ነበሩ፡፡ ናትናኤል የፍጽምናና የእምነት ልጅ የዚያ ጥል የሚወደው የዞበድያ ልጅ፡፡EDA 92.3

    የተጠሩበትን ሥራቸውን ወደፊት በተሳካ መልኩ ማካሄድ ይችሉ ዘንድ እነኝህ ደቀመዛሙርት በተፈጥሮ ባህሪ በሥልጠና በሮ ልማዳቸው እጅግ የተራራቀ ልዩነት የነራቸው ይሁኑ እንጅ ለሀሳብና ለተግባር ምግብ በሆነው ማዕድ አንድ ላይ መሆን የግድ ሆነባቸው፡፡ ይኸንን አንድነት መጠበቅ የክርስቶስ ዓላማ ነበር፡፡ ለዚህ ግብ ይጠቅመው ዘንድ አንድነታቸው እርስ በራሳቸው ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ጋርም እንዲሆን አደረገ፡፡ ለነርሱ ያዘጋጀላቸው የእርሱ ሥራ ሸክም ለአባቱ ባቀረበው ፀሎት ተገልጾአል «ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ ከቃላቸው የተነሳ በእኔ እንዳለህ እኔም ባንተ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ፡፡ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደወደድካቸው ያውቃል፡፡» ዮሐ 17፡21-23፡፡EDA 93.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents