Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 7—የታላላቅ ሰዎች ሕይወት

    «የጻድቅ ፍሬ ሕይወት ናት»EDA 53.1

    የቅድስና ትምህርት ታሪክ የእውነተኛ ትምህርት ውጤት የሆኑ ብዙ ማብራሪያዎችን ያቀርባል፡፡ ብዙ የተቀደሱ ሰዎችን ምሳሌነት ጠባያቸው በመለኮት መመሪያ ሥር የታቀፈና የተቀረፀ ሰዎችን ታሪክ፤ ሕይወታቸው ለሌሎች ወገኖቻቸው በረከት የሆነ፤ የእግዚአብሔር ወኪል መሆናቸው በጉልህ የሚታወቅ ሰዎችን ታሪክ ያቀርባል፡፡ ከእንደዚህ ዓይነቶቹ መካከል ዮሴፍ ዳንኤል ሙሴ ኤልያስና ጳውሎስ ነበሩ፡፡ የታወቀ ትልቅ የሃገሪቱ ሰው፤ አዋቂ የሕግ ሰው እጅግ ጥብቅ ታማኝ የተሃድሶ ሰው ሌላ ምንም እንደሱ ያልተናገረ፣ እጅግ ድንቅ ማብራራት የሚችል አስተማሪ በዚች ዓለም ታይቶ የማይታወቅ፡፡EDA 53.2

    በጥንት ዘመን ከወጣትነት ወደ ጐልማሳነት በሚሸጋገረበት ጊዜአቸው ላይ ዮሴፍና ዳንኤል ከቤታቸው ተለይተው እንደ ምርኮኛ ወደ አረማዊያን አገር ተወስደው ነበር፡፡ በተለይም ዮሴፍ ትልቅ የእድል ለውጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፈተናዎች ውስጥ ገብቶ ነበር፡፡ በአባቱ ቤት ውስጥ እጅግ የሚወደድ ልጅ፣ በጶጢፋር ቤት ውስጥ ደግሞ እንደባሪያ፣ ከዚያ በኋላ አሸናፊ አበጋዝ፣ የጐዳዮች ኃላፊ በጥናት በቀጥታ ከሰዎች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት፣ እርጋታና፣ ማስተዋል የተሞላበት በፈሪኦን ምድር ቤት በጨለማ ጠባብ ክፍል የመንግሥት እሥረኛ ሆኖ ያለ አግባብ ተወንጅሎ ለመፈታት ወይም ለይግባኝ ተስፋ በሌለበት ሁኔታ በታላቅ ችግር ጊዜ ሕዝቡን እንዲመራ የተጠራ ትልቅ ርጋታ ያለው ታላቅ ሰው ለመሆን ያበቃው ሚስጥሩ ምን ነበር? EDA 53.3

    ማንም ሰው አንድ በጣም ከፍተኛ አፋፍ ላይ ያለሥጋት መቆም አይችልም፡፡ በሸለቆ ውስጥ ያሉትን አበቦች ሳይነካ እተራራው ጫፍ ላይ ያለውን ዛፍ ግን ከሥሩ እንደሚፈነቅለው አውሎ ነፋስ ሁሉ በኑሮአቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ሰዎች ሳይነኩ በክብርና በስኬታማኝነት ተዋጥቶላቸው በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱትን ሰዎች አደገኛ የሆኑ ፈተናዎች ያዋዥቋቸዋል፡፡ ዮሴፍ ግን ሁለቱንም ማለትም የድህነትንም ሆነ የብልጽግና ፈተናዎች ተቋቁሞአቸዋል፡፡ በፈረኦን ቤተመንግሥት ውስጥ ያው ታማኘነቱ ብቻ ነበር የተገለጠው፡፡EDA 54.1

    ዮሴፍ በልጅነቱ እግዚአብሔርን ማፍቀርንና መፍራትን ይማር ነበር፡፡ ዘወትር በአባቱ ድንኳን ውስጥ በሦርያ አገር በመሽት ኮከቦችን እየተመለከተ፣ በቤቴል ስለታየው የአንድ ቀን ማታ ራዕይ ከሰማይ አንስቶ እስከ ምድር ስለተዘረጋው፣ መሰላል በዚህ ላይ ወደታች ይወርዱና ወደላይ ይወጡ ስለነበሩት መላዕክት፣ ከላይ በዙፋኑ ሆኖ ራሱን ለያዕቆብ ስለገለፀው አምላክ ታሪክ ይማር ነበር፡፡ ያዕቆብ አሸናፊ ሆኖ የእግዚአብሔር ልዑል የሚል ማዕረግ ያገኘበት በያቦክ ስለተደረገው ትግል ተነግሮት ነበር፡፡EDA 54.2

    የአባቱን በጐች በእረኝነት በሚጠብቅበት የልጅነት ጊዜው የያዕቆብ ፍፁም ንፁህና ቀላል ሕይወት የአካልና የአእምሮ ኃይሉን ለማሳደግና ለማዳበር ምቹ ሁኔታን ፈጥሮለት ነበር፡፡ ከአባት ወደልጅ እንደቅዱስ እምነት የወረዱትን ታላላቅ ዕውነቶች በማጥናትና ከእግዚአብሔር ጋር በተፈጥሮ አማካይነት በመገናኘት የአእምሮ ብርታትና በመሠረታዊ ሐሳቦች ላይም ጽናትን አግኝቷል፡፡EDA 54.3

    በሕይወቱ ውስጥ በደረሰው የኑሮ ቀውስ፣ ያንን አስቸጋሪ ጉዞ በከነዓን ከነበረው የልጅነት ቤት በግብጽ እስከ ጠበቀው እስር ቤት ድረስ በሕፃንነቱ ያደገበትን ድንኳን የከለሉበትን ኮረብቶች ለመጨረሻ ጊዜ መለስ ብሎ በመመልከት ዮሴፍ የአባቱን አምላክ አስታወሰ፡፡ በልጅነቱ የተሰጠውን ትምህርትም አሰበ፡፡ እሱ እውነተኛ መሆኑ ሲታወቅ ለዘለዓለም የሰማይ ንጉሥ ተገዥ መሆኑን በማረጋገጡ ነፍሱ ተደሰተች፡፡EDA 54.4

    እንግዳና ባርያ በነበረበት መራራ ሕይወቱ፣ የሚታየውና የሚሰማው ሁሉ የአረመኔዎች አምልኮ ክፋትና የሚማረክ ትዕይንት መካከል ሀብት ዕድገት፣ ንጉሣዊ በሆ የክብር ሰልፍ በተከበበ የታይታ አምልኮ መካከል ዮሴፍ ፀንቶ ቆመ፡፡ ለቁም ነገር ሥራ ብቻ መታዘዝን ተምሯል፡፡ በማንኛውም ደረጃ ታማኝነትን ከዝቅተኛው እስከ መጨረሻው ከፍተኛ ባለሥልጣን ድረስ ለማንም ያለአድሎ እያንዳንዱን ችሎታና ኃይሉን ለከፍተኛ አገልግሎት ያውለው ዘንድ ሰልጥኗል፡፡EDA 55.1

    ወደፈርኦን ችሎት እንዲቀርብ በተጠራ ጊዜ በዚያን ዘን ግብጽ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የበለጠ ኃያል የነበረችበት ዘመን ነበር፡፡ በሥልጣኔ፣ በጥበብ፣ በትምህርት የሚስተካከላት አልነበረም፡፡ እጅግ አስቸጋሪና አደገኛ በሆነ ወቅት በግዛቱ ውስጥ የአስተዳደርን ጉዳዮች በኃላፊነት ይዞ ነበር፡፡ በዚህም ሥራው ንጉሡና ሕዝቡ እምነት ጥለውበት ነበር፡፡ ፈርኦንም «...የቤቱ ጌታ የንብረቱ ሁሉ ገዥ አደረገው፡፡ አለቆችን እንደፈቃዱ የገሥጽ ዘንድ ሽማግሌዎችንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ፡፡» መዝ 105፡21-22፡፡EDA 55.2

    የዮሴፍ ሕይወት የተነቃቃበት ሚስጥር አፊታች ላይ ተቀምጧል፡፡ በመለኮት ኃይልና ውበት በተሞሉ ቃላት ያዕቆብ ልጆቹን ሲመርቅ እጅግ ለሚወደው ልጁ ግን ይኸንን ተናገረ፡፡ ‹ዮሴፍ በውኃ ምንጭ አጠገብ ተተክለው ሐረጐቹ በግድግዳ ላይ እንደሚዘረጉ ፍሬአማ ዛፍ ነው፡፡ ቀስተኞች አስቸገሩት ነደፉትም ተቃወሙትም ነገር ግን ቀስቱ እንደፀና ቀረ የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፡፡ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል አምድ በአባትህ አምላክ እርሱም የሚረዳህ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፡፡ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ በጥልቅም በረከት ከታች በሚሰራጭ በጡትና በማህፀን በረከት፡፡ የአባትህ በረከቶች ጽኑአን ከሆነ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው ዘለአለማውያን ከሆኑ ኮረብቶችም በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው እነርሱም በዮሴፍ ላይ ይሆናሉ፡፡ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ፡፡› ዘፍ 49፡22-26EDA 55.3

    ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን በአይን የማይታየውን አምላክ በማመን ላይ ነበር የዮሴፍ መልህቅ የተጣለው፡፡ የርሱ ኃይል ተደብቆ ያለው በዚህ ላይ ነበር፡፡ «እጅግ ኃያል በሆነው የያዕቆብ አምላክ የእጆቹ ክንዶች ይጠነክራሉ፡፡»EDA 56.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents