Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 17—ሥነ-ግጥምና መዝሙር

    «በእምነት ላሉት መንግሥት እንዲያሸንፉ በጽድቅ
    የተገዙትንም ከድካም አንስተህ ብርታት ሰጣቸው፡፡»
    EDA 176.1

    ጥንታዊ የሆኑና በሰው ልጅ ታሪክ እጅግ በከፍተኛ ደረጃ ከታወቁት የሥነግጥም ቃላት ውስጥ በቅዱስ መፃህፍት ውስጥ የሚገኙት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በዓለም ላይ እጅግ ጥንታዊ ሥነግጥሞች ከመዝሙረኛው በፊት ቀደም ሲል በሜዲያን በግ እረኛ የነበረው፣ እግዚአብሔር ለኢዮብ የተናገራቸውን ቃላት... ማንም ሊወዳደራቸው በማይቻል ከፍተኛ ደረጃ የሰው ልጅ እውቀት ሊደርስበት በማይችል ብዛት መዝግቦ አውጥቷቸዋል፡፡EDA 176.2

    «ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ?...
    ባሕርን በመዝጊያዎች የዘጋ ማን ነው? ዳመናው
    ለልብሱ ጨለማንም ለመጠቅለያው አደረግሁ፡፡ ድንበሩን
    በዙሪያው አድርጌ መወርወሪያዎችንና መዝጊያዎቹን
    አኑሬ አስከዚህ ድረስ አትለፊ በዚህም ለትዕቢተኛው
    ማዕበልሽ ገደብ ይሁን አልሁ፡፡...

    «በውኑ ከተወሰድህ ጀምሮ ማለዳን አዝዘሀልን?
    ለወገግታም ስፍራውን አስታውቀኸዋልን?...
    «ወደ ባሕር ምንጭስ ውስጥ ገብተሃልን? በቀላዩስ
    መሠረት ውስጥ ተመላልሰሃልን? የሞት በሮች
    ተገልጠውልሃልን? የሞትንስ ጥላ ደጆች አይተሃልን?
    ምድርንስ በስፋትዋ አስተውለሃታልን? ሁሉን አውቀህ
    እንደ ሆነ ተናገረ፡፡...
    EDA 176.3

    «የብርሃን መኖሪያ መንገድ የት ነው? የጨለማውስ
    ቦታ ወዴት አለ ?

    «የበረዶውንስ ቅንጣት ቤተመዛግብት አይተሃልን?
    በውኑ ወደ በረዶው ቤተመዛግብት ገብተሃልን?
    ብርሃንስ በምን መንገድ ይከፈላል?
    ለፈሳሹ ውሃ መንዶልዶሊያውን ወይስ
    ለሚያንጐደጉድ መብረቅ መንገድን ያበጀ
    ማንም በሌለበት ምድር ላይ ሰውም በሌለባት ምድረበዳ
    ላይ ዝናብን ያዘንብ ዘንድ ባድማውንና ውድማውን
    እንዲያጠግብ ሣሩንም እንዲያበቅል፡፡

    «በውኑ የሰባቱን ከዋክብት ዘለላ ታሥር ዘንድ ወይስ
    ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ ትፈታ ዘንድ ትችላለህን?
    ወይስ ማሳሮት የሚባሉትን ከዋክብት በጊዜአቸው
    ታወጣ ዘንድ ወይስ ድብ የሚባለውን ኮከብ ከልጆቹ
    ጋር ትመራ ዘንድ ትችለለህን? ኢዮብ 38፡4-27፤38፡31-32፡፡

    የፀደይ ወራትን እንዴት በግሩም ሁኔታ ውበቱን
    እንደገለፀው ለማወቅ ከመሐልየ መኃልይ ከሰለሞን
    ይኸንን አንብቡ፡፡

    «እነሆ ክረምት አለፈ ዝናቡም አልፎ ሄደ አበቦች
    በምድር ላይ ተገለጡ የዜማም ጊዜ ደረሰ የቁርዩውም
    ቃል በምድራችን ተሰማ በለሱ ጐመራ ወይኖችም
    አበቡ መዓዛውንም ሰጡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ» መኃል2፡11-13

    ከዚህ ባላነሰ ሁኔታ በዓለም ለእስራኤል ያለፍላጐቱ
    በምርቃት የተነበየውም ውበት የተጐናፀፈ ነበር፡፡
    «ባላቅ ከአራም አመጣኝ የሞአብ ንጉሥ ከምስራቅ
    ተራሮች ና ያዕቆብን ርገምልኝ ና እስራኤልን ተጣላልኝ
    ብሎ እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ?
    በአምቦች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ በኮረብቶችም ላይ
    EDA 177.1

    ሆኘ እመለከተዋለሁ፡፡ እነሆ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው ከአህዛብም መካከል አይቆጠርም፡፡... «እነሆ ለመባረክ ትዕዛዝ ተቀብያለሁ እርሱ ባርኮአል እመልሰውም ዘንድ አልችልም፡፡ በያዕቆብ ላይ ክፋትን አልተመለከተም በእስራኤልም ጠማማነትን አላየም አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነው የንጉሡም እልልታ በመካከላቸው አለ፡፡... በያዕቆብ ላይ አስማት የለም በእስራኤልም ላይ አስማት የለም በጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል እግዚአብሔር ምን አደረገ ይባላል፡፡»EDA 178.1

    «የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ ሁሉን የሚችል
    የአምላክን ራዕይ የሚያይ ያዕቆብ ሆይ ድንኳኖችህ
    እስራኤል ሆይ ማደሪያዎችህ ምንኛ ያምራሉ?
    እንደሸለቆዎች በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች
    እግዚአብሔር እንደተከለው እሬት በውሃም ዳር
    እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል፡፡»

    «የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ የልዑልንም እውቀት
    የሚያውቅ፡፡... አየዋለሁ አሁን ግን አይደለም
    እመለከተዋለሁ በቅርብ ግን አይደለም ከያዕቆብ ኮከብ
    ይወጣል ከእስራኤል በትር ይነሳል፡፡»

    «ከያዕቆብ የሚወጣ ገዥ ይሆናል፡፡» ዘሁል 23፡7-23 24፡4-6፣ 24፡16-19
    EDA 178.2

    የምስጋና መዝሙር የሰማይን አካባቢ ሁኔታ የሚመስል ድባብ ይፈጥራል፡፡ ሰማይ ደግሞ ከምድር ጋር ግንኙነት ሲፈጥር ሙዚቃና መዝሙር ይኖራል፡፡ «ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምጽ ይገኝበታል፡፡» ኢሳ 51፡3EDA 178.3

    በአዲስ መልክ ከተፈጠረችው መሬት በላይ ከሩቅ ንጣፍ የተኛው በእግዚአብሔር ፊት ያልተጐዳው ሰማይ «አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ» ኢዮብ 38፡7 ስለዚህም የሰው ልጅ ልቦች ከሰማይ ጋር ሲግባቡ በምስጋና መዝሙር ለእግዚአብሔር ቸርነት አፀፋውን ይመልሳሉ፡፡ ከሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አብዛኛዎቹ ድርጊቶች /ክንውኖች/ ከመዝሙር ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡EDA 178.4

    ከሰዎች ከንፈር ወጥተው ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ የተመዘገበ ጥንታዊ መዝሙር የእስራኤል ሕዝብ ከቀይ ባህር ማዶ ለእግዚአብሔር ምስጋና በመስጠት በአንድ ላይ ያስተጋቡት መዝሙር ነው፡፡EDA 179.1

    «በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፡፡
    ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ፡፡ ጉልበቴ
    ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፡፡ መድኃኒቴም ሆነልኝ፡፡
    ይህ አምላኬ ነው አመሰግነዋለሁ የአባቴ አምላክ ነው
    ከፍ ከፍም አደረገዋለሁ፡፡»

    «አቤቱ ቀኝህ በኃይል ከበረ አቤቱ ቀኝህ ጠላቱን
    አደቀቀ፡፡... አቤቱ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ
    ማን ነው?... በቅድስና የከበረ እንደ አንተ ያለ ማነው?
    ምስጋና የተፈራህ ድንቅንም የምታደርግ፡፡...

    «እግዚአብሔር ለዘለዓለሙ አስከፍፃሜ ይነግሣል፡፡
    ...በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና ለእግዚአብሔር ዘምሩ፡፡» ዘፀ 15፡1-2፣6-11፣18-21
    EDA 179.2

    ለእነዚህ የምስጋና መዝሙሮች ሰዎች በአፀፋው እጅግ ታላላቅ በረከቶች አግኝተውበታል፡፡ የበረሃውን ጉዞ የሚያስታውስ ጥቂት ቃላት መልካም ትምህርታዊ ሐሳብ ይሰጣል፡፡EDA 179.3

    «ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ ይኸውም እግዚአብሔር ሙሴን ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ፡፡» «ከዚያ በኋላም እስራኤል ይኸንን መዝሙር ዘመረ፡፡» «አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ እናነተ ዘምሩለት በበትረ መንግሥት በበትራቸውም የሕዝብ አዛውንቶች ያጐድጉዱት፡፡ አለቆችም የቆፈሩት ጉድጓድ፡፡» ዘሁ 21፡17-18EDA 179.4

    በመንፈሳዊ ኑሮ ውስጥ ይህ ታሪክ ምን ያክል ጊዜ ተደጋግሟል፡፡ በቅዱስ መዝሙሮች ቃላት በነፍስ ውስጥ የትዕግሥትን የእምነትን የተስፋ፣ የፍቅርና የደስታ ምንጮችን የከፈቱት ስንት ጊዜ ነውEDA 180.1

    በዮሳፋጥ አመራር የእስራኤል ጦር ታላቁን አገር የማዳን ግዳጅ የተወጣው ከምስጋና መዝሙሮች ጋር ነው፡፡ ለዮሳፋጥ የአስፈሪ ጦርነት ማዕበል መልዕክት ነበር የመጣለት «ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል» የሚል መልዕክት ነበር፡፡ «ሞአብና የአሞን ልጆች ከእነርሱም ጋር ሌሎች» «ዮሳፋጥም ፈራ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ፡፡ ይሁዳም እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ተከማቸ» ዮሳፋጥም በቤተመቅደሱ አደባባይ ላይ በሕዝቡ ፊት ቆመና የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ከልቡ ለመነ፡፡ አስራኤል ረዳት የሌላት መሆኑንም ገለፀ «አምላካችን ሆይ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይኸን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም» አለ «የምናደርገውንም አናውቅም ነገር ግን አይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው፡፡» 2ኛ ዜና 20፡2-1-3-4-12EDA 180.2

    በኋላም በየሕዝኤል በሌዋዊው «የእግዚአብሔር መንፈስ መጣ እንዲህም አለ ይሁዳ ሁሉ በእየሩሳሌምም የምትኖሩ አንተም ንጉሡ ኢዮሳፋጥ ስሙ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጅ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሳ አትፍሩ አትደንግጡም ... እናንተ በዚህ ሰልፍ የምትዋጉ አይደላችሁም....ዝም ብላችሁ ቁሙ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነውና፡፡» 2ኛ ዜና 20፡14-17EDA 180.3

    «ማለደውም ተነሱ ወደ ቴቄሔም ምድረ በዳ ወጡ» 2ኛ ዜና 20-20 ከጦሩ ፊትም መዘምራን ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይዘምሩ ነበር፡፡ ለገባ የተስፋ ቃል ያመሰግኑ ነበር፡፡EDA 180.4

    በአራተኛውም ቀን ጦሩ ወደ እየሩሳሌም ተመለስ የጠላቶቻቸውን ምርኮ ጭነው ለተገኘው ድል የምስጋና መዝሙር እያቀረቡ መጡ፡፡EDA 181.1

    ከብልጽግና ወደ ድህነት ባሽቆለቆለበት የለውም ሕይወት ውስጥ ዳዊት በመዝሙር ከሰማይ ጋር ይገናኝ ነበረ፡፡ እንደ አንድ ወጣት እረኛ የነበረው ሕይወት በእነዚህ ቃላት ምንኛ ጣፋጭ በሆነ መልኩ የእረኝነት ኑሮው ተንፀባርቋል፡፡EDA 181.2

    «እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤ የሚያሳጣኝም የለም
    በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፡፡ በዕረፍት ውሃ ዘንድ
    ይመራኛል... በሞት ጥላ መካከል እንኳብሔድ አንተ
    ከእኔ ጋር ነህና ክፉውን አልፈራም በትርህና መርኩዝህ
    እርሳቸው ያጽናኑኛል፡፡» መዝ 23፡1-4፡፡
    EDA 181.3

    በጐልማሳነቱ ጊዜም በስደት እየሸሸ በበረሃ ውስጥ መጠለያና መጠጊያ በየቋጥኙና በየዋሻው ለመደበቅ ሲሯሯጥ ሳለ እንደዚህ ብሎ ጻፈ፡፡EDA 181.4

    «አምላኬ ፣ አምላኬ፣ ወደ አንተ አገሠግሣለሁ፡፡ ነፍሴ»
    አንተን ተጠማች ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች፡፡
    እንጨትና ውሃ በሌለበት በምድረበዳ... ረዳቴ
    ሆነኸኛልና በክንፎችህም ጥላ ይለኛልና፡፡
    «ነፍሴ ሆይ ለምን ታዝኛለሽ ለምንስ ታውኪኛለሽ?
    የፊቴን መድሐኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ
    በእግዚአብሔር ታመኚ፡፡».... «እግዚአብሔር
    ብርሃኔና መደሃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው?
    እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያ
    ስደነግጠኝ ማነው?» መዝ 63፡1-7፣42፡11፡27-1
    EDA 181.5

    አቤሴሎም በአምጽ በተነሳበት ጊዜ ዳዊት ከዙፋኑ ወርዶ በግልበጣ ንጉሡ ዘውዱን ባጣ እና ከየሩሳሌም በወጣ ጊዜ በእነኛው ቃላት በመፃፍ እምነቱን ገልጿል፡፡ በሀዘንና በጨንቀት ከወገኑ ጋር ሆኖ ሲባረር እንደዋለ በዮርዳኖስ ደርቻ ደክሞት ለጥቂት ሰዓታት አረፈ፡፡ ወዲያውም ተነስቶ እንዲበርር በሸሽት እንዲያመልጥ ቀስቅሰው ነገሩት፡፡ በጨለማ ውስጥ በእርሱ ወገን የነበረው ሕዝብ ወንዶች ሴቶችና ሕፃናት ሁሉ በዚያ ጥልቀት ባለውና በፍጥነት የሚወርደውን ወነዝ ተሻግረው መሄድ ነበረባቸው፡፡ ምክንያቱም ከኋላቸው የመጣባቸው የጦር ኃይል የከሀዲው ልጅ ሠራዊት በጣም ከባድ ነበረ፡፡EDA 182.1

    በዚያ ጨለማ የፈተና ሰዓት ዳዊት እንዲህ ሲል ዘመረ፡፡EDA 182.2

    «በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ ከተቀደሰ
    ተራራውም ይሰማኛል፡፡ እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም
    እግዚአብሔር ደግፎኛልና ነቃሁ፡፡ ከሚከብቡኝ ከአእላፍ
    ሕዝብ አልፈራም፡፡» መዝ 3፡4-6
    EDA 182.3

    በደረሰበት ከባድ ስቃይና ጥልቅ ሐዘን ታላቅ ኃጢአት ከሠራ በኋላ ራሱን በመጥላትና በመፀፀት ላይ እያለ እንኳ አንደ አንድ ምርጥ ጓደኛው ወደ እግዚአብሔር ፊቱን መለሰ፡፡EDA 182.4

    «አቤቱ፣ አንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ
    ምህረትህም ብዛት መተላለፌን ደምሰስ ከበደሌ ፈጽሞ
    እጠበኝ ከኃጢአቴም አንፃኝ እኔ መተላለፌን
    አውቃለሁና ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና አንተን
    ብቻ በደልሁ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፡፡ በነገርህ
    ትፀድቅ ዘንድ በፍርድህም ንፁህ ትሆን ዘንድ ፡፡እነሆ
    በዓመፃ ተፀነስሁ እናቴም በኃጢአት ወለደች፡፡ እነሆ
    እውነትን ወደድህ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ፡፡ መዝ 51፡1-7
    EDA 182.5

    ዳዊት በረዥም የእድሜ ዘመኑ በምድር ላይ አንድም የእረፍት ቦታ አላገኘም፡፡ «አባቶቻችንም ሁሉ እንደነበሩ እኛ በፊትህ ስደተኞችና መፃተኞች ነን» አለ «ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ናት፡፡» 1ኛ ዜና 29፡15EDA 183.1

    «እግዚአብሔር አምላካችን መጠጊያችን ነው፡፡ ባገኘን
    በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው፡፡ ስለዚህ ምድር
    ብትነዋወጥ ተራሮችም ወደ ባህር ልብ ቢወስዱ አንፈራም፡፡
    የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ
    ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ፡፡ እግዚአብሔር በመካከልዋ
    ነው አትናወጥም፡፡ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል፡፡
    አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተመለሱ፡፡ እርሱ
    ቃሉን ሰጠ ምድርም ተንቀጠቀጠች፡፡ የሰራዊት ጌታ
    ከእኛ ጋር ነው፡፡ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን
    ነው፡፡» «ይህ አምላካችን ነው እርሱም ለዘላለም
    ይመራናል፡፡»
    EDA 183.2

    መዝ 46፡1-2፣ 46፡4-7፣48፡14፡፡EDA 183.3

    የሱስ በልጅነቱ ፈተና ሲያጋጥመው እየዘመረ ይጋፈጠው ነበር፡፡ ዘወትር ስለታማና በኃይል ዘልቀው ጠልቀው የሚገቡ ቃላትን ይናገር ነበር፡፡ የሚከብድና ሁኔታው የሚደብት ዝግ የሆነ ቀን ሲያጋጥመው፣ ቅር የሚያሰኝ የሚያሳዝን ወይም የሚያስፈራ ቀን በከበበው ጊዜ የእምነት መዝሙሩና ቅዱስ ዕልልትው ይሰማ ነበር፡፡EDA 183.4

    በዚያ የሐዘን ምሽት የጌታ እራት በተከናወነበት ሰዓት የሚሸጥበትና የሚሞትበት ሰዓት እየተቃረበ በሄደበት ሰዓት ድምጹ በመዝሙር ከፍ ብሎ ተሰማEDA 183.5

    «...የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ
    እስከ ዘለዓለም ድረስ የእግዚአብሔር ስም ብሩክ
    ይሁን፡፡ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው
    EDA 183.6

    ድረስ፡፡ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን፡፡›
    «እግዚአብሔር የልመናዬን ድምጽ ሰምቷልና
    ወደድሁት፡፡ ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና በዘመኔ
    ሁሉ እጠራዋለሁ፡፡ የሞት ጣር ያዘኝ የሲኦል ሕማም
    አገኘኝ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ፡፡ የእግዚአብሔርን
    ስምጠራሁ፤...አቤቱ ነፍሴን አድናት እግዚአብሔር
    መሐሪና ጻድቅ ነው፡፡ አምላካችን ይቅር ባይ ነው፡፡
    እግዚአብሔር ሕፃናትን ይጠብቃል ተቸገርሁ እርሱም
    አዳነኝ፡፡ ነፍሴ ሆይ ወደ እረፍትሽ ተመለሺ
    እግዚአብሔር መልካም አድርጐልኛልና፡፡ ነፍሴን ከሞት
    ዓይኔንም ከእንባ እግርንም ከመሰናክል
    አድኖአልና፡፡» መዝ 113፡2፡2፣116፡1-8
    EDA 184.1

    በምድር ላይ ሊኖር በሚችለው እጅግ ከፍተኛው የቀውስ ጥላና ጭለማ ውስጥ የእግዚአብሔር ብርሃን በኃይል ያበራል፡፡ የተስፋና የእምነት መዝሙርም እጅግ ግልጽ በሆነ ድምጽ ከፍ ብሎ ይሰማል፡፡EDA 184.2

    «በዚያ ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘመራል
    የፀናች ከተማ አለችን ለቅጥርና ለምሽግ መድኃኒትን
    ያኖርባታል እውነትን የሚጠብቅ ጻድቅ ሕዝብ ይገባ
    ዘንድ በሮችን ከፈቱ፡ በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ
    ለምትደገፍ ነፍስህ ፈጽመህ በሰላም ተጠብቃታለህ፡፡
    ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም አምባ ነውና ለዘለዓለም
    በእግዚአብሔር ትመኑ፡፡» ኢሳ 26፡1-4
    EDA 184.3

    «እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፡፡ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል ሐሴትንና ደሰታን ያገኛሉ፡፡ ሀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ፡፡» ኢሳ 35፡10፡፡EDA 184.4

    «በጽዮንም ተራራ እልል ይላሉ ወደ እግዚአብሔርም በጐነት ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ... ይሰበሰባሉ ነፍሳቸውም እንደረካች ገነት ትሆናለች ከእንግዲህ ወዲህ አያዝኑም፡፡» ኤር 31፡12EDA 185.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents