Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 18—የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢሮች

    «እግዚአብሔርን ፈልገህ
    ማግኘት ይቻልሃልን?»
    EDA 187.1

    የትኛውም ውስን የሆነ የእምሮ ወሰን የሌለበትን የእርሱን ባህሪይና ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ማስተዋል አይችልም፡፡ እኛ እግዚአብሔርን አፈላልገን ልናገኘው አንችልም፡፡ ለኃይለኛውና እጅግ ከፍተኛ ትምህርት ላገኘው አእምሮና እጅግ ደካማና መሃይም ለሆነውም እንዲሁ እኩል ያ ቅዱስ የሆነው አምላክ ምስጢርን እንደ ተላበሰ ይኖራል፡፡ ነገር ግን «ዳመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው» መዝ 97፡2፡፡ እርሱ ለእኛ ያለውን አያያዝ እጅግ በጣም ከፍተኛ ምህረት ወሰን ከሌለው ኃይሉ ጋር እንደተጣመረ ለይተን ማስተዋል እንችላለን፡፡ ከእርሱ ዓላማዎች ውስጥ የሚቻለንን ያክል እናስተውላለን፡፡ ከዙህ ወዲያ ላለው ደግሞ ዘለዓለማዊ ኃያል በሆነው ክንዱና በፍቅር በተሞላው ልቡ ላይ እምነታችን ማሳረፍ ብቻ ነው፡፡EDA 187.2

    የእግዚአብሔር ቃል እንደፈጣሪዋ ባሕሪይ ሁሉ ውሱን በሆኑ ፍጡሮች በከፊል ካልሆነ ሙሉ በሙሉ ፈጽሞ ሊስተዋሉ የማይችሉ ምስጢሮችን ታቀርባለች፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለእነዚህ መለኮታዊ ሥራዎች ሥልጣን በቅዱስ እግዚአብሔር ለእነዚህ መለኮታዊ ሥራዎች ሥልጣን በቅዱስ መጽሐፍት የርሱ ለመሆናቸው በቂ ማስረጃ አስቀምጧል፡፡ የራሱ ሕልውና የርሲ ባሕሪይ የቃሉ ሙሉ እውነተኛነት ህሊናችንን በሚነኩ የምስክር ቃሎች ተሞልተዋል፡፡ ይህ ምስክርነት ደግሞ እጅግ ብዙ ነው፡፡ በእርግጥ የመጠራጠር ችሎታን አላጠፋም፡፡ እምነት በማስረጃ ላይ ማረፍ አለበት፡፡ በመግለጫ አይደለም፡፡ መጠራጠር ለሚፈልጉ ደግሞ እድሉ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ነገር ግን እውነቱን ለማወቅ ለሚሹ ለእምነት የሚሆን ጥሩ መሠረት አላቸው፡፡EDA 187.3

    የእግዚአብሔርን ቃል ለመጠራጠር ምክንያት የለንም፡፡ ምክንያቱም የስጦታውን ምስጢሮች ልክ ማወቅ አንችልምና፡፡ በዚህ በተፈጥሮ ዓለም ውስጥ ልናስተውለው ከምንችለው በላይ በሆኑ አስገራሚ ነገሮች ዙሪያችን ተከበናል፡፡ ስለዚህ በመንፈሳዊዩ ዓለም ውስጥ ደግሞ የጥልቀቱን ልክ /ዲካ/ ልንደርስበት ሳንችል ብንቀር የሚያስደንቅ ይሆናል? ችግሩ ያለው በሰው ልጅ አእምሮ ደካማነትና ጠባብነት ብቻ ነው፡፡EDA 188.1

    የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢሮች በራሱ ላይ ክርክር የሚያስነሱ ከመሆን የራቁና የመለኮት የማነቃቂያ ማስረጃዎች ከሆኑት ማስረጃዎች መካከል እጅግ ጠንካራዎቹ ናቸው፡፡ ልናስተውለው የምንችለው ብቻ እንጅ ሌላ ስለ እግዚአብሐር የሚገልጽ ነገር ባይፃፍ ኖሮ ታላቅነቱና ግርማው ውስን በሆነ አእምሮ ውስጥ ሊጨበጥ የሚችል ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ አሁን የሆነውን ያክል የማያሳስተውን መለኮታዊ ባሕሪይዩን የሚገልጽ ማስረጃ መያዝ ባላስፈለገውም ነበር፡፡ የየክፍሎቹም ታላቅነት እንደ እግዚአብሔር ቃል እምነትን የሚያነቃቃ ነው፡፡EDA 188.2

    መጽሐፍ ቅዱስ እውነትን በቀላል መንገድና የሰው ልጅ ልቦና የሚያስፈልገውንና የሚመኘውን ሁሉ እጅግ ከፍተኛ እንክብካቤ ተደርጐለት የተማረውን አዕምሮም ያስደነቀና ያስደሰተ ዕውነትን ይገልፃል፡፡ ትሁትና ያልተማረ ለሆነው ደግሞ የሕይወትን ጐዳና ቀላልና ግልጽ ያደርግለታል፡፡ «በዚያ ጐዳናና መንገድ ይሆናል... ንፁሐንም ያልሆኑ አያልፉበትም፡፡» ኢሳ 35፡8 ሕፃንም የማይስተው መንገድ፡፡ ፍጹም ንፁህና ቅዱስ በሆነው ብርሃን አማካይነት በሚራመድበት ጊዜ የሚንቀጠቀጥ ለማኝ እንኳ አይወድቅም፡፡ ይሁንና እጅግ በቀላሉ ተብራርተው የተቀመጡ እውነቶች እጅግ ከፍ ብለውና እጅግ ርቀው የሰው ልጅ የማስተዋል ኃይል ሊደርስበት ከሚችለው በላይ ወሰን በሌለው ሁኔታ ጠልቀው የሚሄዱ በአንዳንድ ክፍሎች ውስጥ አሉ፡፡ የርሱን ክብር የሚደብቁ ምስጢሮች ለሚመራመረው አእምሮ ኃይልን የሚሞላለት በፍፁም ልብ ጥልቅና ልባዊ በሆነ ስብሃት እና እምነት የሚለምነውን ሰው የሚያንቃቁ ምስጢሮች ናቸው፡፡ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጠለቅ ብለን በተመራመርን ቁጥር የሕያው እግዚአብሔር ቃል መሆኑን ወዲያውኑ በጥልቀት እንረዳለን፡፡ የሰው ልጅ የማሰላሰል ችሎታም ወዲያውኑ በመለኮት የመገለጥ ግርማ ሥር ይንበረከካሉ፡፡EDA 188.3

    እግዚአብሔርን በንፁህ ልብ ለሚፈልገው ሰው የርሱ ቃል እውነትነት ሁልጊዜ እንዲገለጽለት እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ «የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው፡፡» ዘዳ 29፡29፡፡ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሊስተዋሉ ያለመቻላቸው ጉዳይ አነዳንድ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ክፍሎችን በቸልታ እንድናልፍ ወደሚያደርግ ሐሳብ ይምራል፡፡ ነገሩ መብራራት ያስፈልገዋል፡፡ ዘወትር መደጋገምም አለበት፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢሮች እግዚአብሔር ራሱ በእውነት ምስጢር እንዲሆን ፈልጐ ሳይሆን የራሳችን ድክመት ወይም ድንቁርና እውነትን እንዳናስተውል ወይም አብራርተን እንዳንረዳ ስለሚያደርገን ነው፡፡ ይህ ውሱንና እርሱ አስቦ ያደረገብን ሳይሆን የኛው የራሳችን ችሎታ ነው፡፡ ሊስተዋሉ አይቻሉም ተብለው ዘወትር ከሚታለፉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ አእምሮአችን መቀበል የሚችለውን ያክል እንድናስተውል የእግዚአብሔር ፍላጐት ነው፡፡ «መጽሐፍ ሁሉ በእግዚአብሔር መንፈስ ተፃፈ፡፡ «ለበጐ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀን እንሆን ዘንድ፡፡» 2ኛ ጢሞ 3፡16፡17EDA 189.1

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት እውነቶች ወይም የተስፋ ቃሎች አንዷን እንኳ አድቅቆ ወይም አብላልቶ ለማስተዋል ለሰው ልጅ አእምሮ የሚቻለው አይደለም፡፡ የእርሱን ክብር አንዱ ሰው ከአንድ አቅጣጫ ሌላው ደግሞ ከሌላ አቅጣጫ ይመለከተዋል፡፡ ያውም ለይተን የምንረዳው በጭላንጭል ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ በጥራት ለማስተዋል በእይታችን በላይ ነው፡፡EDA 190.1

    የእግዚአብሔርን ቃል ታላላቅ ነገሮች ስናስተውል ሳለን ከትኩረታችን ውስጥ ስፋትና ጥልቀት የሚሰጠውን ፏፏቴ እንመለከታለን፡፡ ሰፋቱን ጥልቀቱም ከእኛ ዕውቀት በላይ ያልፋል፡፡ አተኩረን ስንመለከት ሳለ የሚታየው ነገር እየሰፋ እዛው እፊታችን ላይ ስፋት እየጨመረ ወሰንና ድንበር የሌለው ባሕር እየሆነ ይሄዳል፡፡EDA 190.2

    እንዲህ ዓይነት ጥናት እርግጠኛ ኃይል ይሰጣል፡፡ አእምሮና ልብም ከአዲስ ኃይል ጋር ይተዋወቃሉ፡፡ አዲስ ሕይወትም ይጀመራል፡፡EDA 190.3

    እንዲህ ዓይነት ገጠመኝ መጽሐፍ ቅዱስ ከመለኮት የተሰጠው ኃይል እንዳለው ከፍተኛው ማረጋገጫ ነው፡፡ ምግብን ለአካላችን ጠቃሚ እንደ ሆነ አምነን እንድምንቀበለው ሁሉ የእግዚአብሔር ቃልም ለነፍሳችን ምግብ እንደሆነ አምነን እንቀበለዋለን፡፡ ምግብ ተፈጥሮአችን የሚፈልገውን ነገር ያቀርብልናል፡፡ ደም አጥንትና አእምሮአችንን እንደሚመግብ በልምድ እናውቃለን፡፡ ይኸንኑ ሙከራ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አውሉት፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት መርሆች በባሕሪያችን ውስጥ ተዋህደው ሲቀመሙ ውጤቱ ምን ይመስላል? በሕይወት ላይ ምን ዓይነት ለውጥ ይከተላል? «አሮጌው ነገር አልፏል፡፡ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል፡፡» 2ኛ ቆሮ 5፡17 በእርሱም ኃይል ብዙ ሴቶችና ወንዶች የኃጢአት ልማዶችን ሰንሰለት በጣጥተውበታል፡፡ ራስ ወደድነትን አውግዘውበታል፡፡ ዓለማዊው ፊሪሃ እግዚአብሔር አድሮበታል፡፡ ሰካራሙ ራሱን የሚቆጣጠር ሆኗል፡፡ ሀፍረትየለሽ ባለጌ የነበረው ንፁህ ሆኖበታል፡፡ ሰይጣን ሆነው ተወለዱ ወደ እግዚአብሐር ተምሳሌነት ተለውጠዋል፡፡ ይህ ለውጥ ራሱ የተዓምር ተዓምር ነው፡፡ በእርሱ ቃል የተቀረፀ ለውጥ እጅግ በጣም ጥልቅ ከሆኑት የርሱ ቃል ምስጢሮች አንዱ እና ዋናው ነው፡፡ ልናስተውለው አንችልም፡፡ በመጽሐፍት ውስጥ እንደ ተገለፀው ማመን ብቻ እንጅ፡፡ «የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው፡፡» ቆላ 1፡27EDA 190.4

    የዚህ ምስጢር ዕውቀት ከተገኘ ከአንዱ ቁልፍ ወደ ሌላው ያሸጋግራል፡፡ የፍጥረተ ዓለማትን መዝገብ ለነፍስ ይሰጣታል፡፡EDA 191.1

    ይህ እድገት የሚገኘው የእግዚአብሔርን ባህሪይና ክብር እንዲሁም የተፃፈው ቃል ምስጢር ያለማቋረጥ ሲገለጡልን ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ሙሉ ለሙሉ ማስተዋል የሚቻለን ቢሆን ኖሮ ከዚያ በላይ የሚበልጥ ትልቅ ዕውቀትም የለም፡፡ ከዚያ በላይ የሚበልጥ ትልቅ ዕውቀትም የለም፡፡ ከዚያ በላይ እድገትም አይኖርም ነበር፡፡ እግዚአብሔር የበላይ መሆኑንም እዚያው ላይ ያቆማል፡፡ የሰው ልጅ እድገትም ከዚያ በላይ መሄድ ስለማይችል እዚያው ላይ ያቆማል፡፡ እንደዚያ ባለመሆኑ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ እግዚአብሔር ወሰን የሌለበት በመሆኑ የጥበብ ሁሉ መዝገብም በርሱ ዘንድ ስለሆነ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ተመራማሪዎች ተማሪዎች እንድንሆንና እንደዚያም ሆኖ የጥበቡን ሐብት የርሱን ቸርነትና የርሱን ኃይል ዘልቀን ልንጨርሰው የማንችለው ነገር ነው፡፡EDA 191.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents