Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 2—የኤደን ትምህርት ቤት

    «ጥበብን የሚፈልግ ደስተኛ ነው፡፡»EDA 16.1

    በዓለም መጀመሪያ ላይ የተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ከዚያ በኋላም ለሰው ልጅ የዘለዓለም ናሙና እንዲሆን ተደርጐ የተዘጋጀ ነበር፡፡ የመርሆቹ መግለጫ ይሆን ዘንድ የማሳያ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ወላጆቻችን መኖሪያ ቤት በነበረው በኤደን ተቋቋመ፡፡ የኤደን ገነት የአትክልት ቦታ ራሱ ትምህርት ቤት ነበረ፡፡ ተፈጥሮ እንደ ትምህርት መጽሐፍ፣ ፈጣሪ ራሱ ደግሞ ታላቁ መምህር ሲሆን የሰው ዘር ወላጆች ደግሞ ተማሪዎች ነበሩ፡፡EDA 16.2

    «በእግዚአብሔር ተምሳሌትና ክብር፡» 1ኛ ቆሮ 11፡7 እንደ መረጣቸው አዳምና ሄዋን ለዘላቂ ግባቸው ብቁ የሚያደርጓቸው ችሎታዎች ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ እኩልና ትክክል የሆነ ግርማ ሞገስ ያለው ቁመና፣ የተሟላና የሚያምር ደልዳላ ቅርጽ የነበራቸው ሲሆን ፀዳላቸውም ጤናማነታቸውን የሚያንፀባርቅ የደስታና የተስፋ ብርሃን ያበራል፡፡ መልካቸውም የፈጣሪአቸውን ተምሳሌት ይዟል፡፡ ይህ ተምሳሌነታቸው ደግሞ በአካላቸው ላይ ብቻ የነበረ አይደለም፡፡ የአእምሮና የነፍስ ልዩ ተሰጥኦዎቻቸው ሁሉ የፈጣሪን ክብር የሚያንፀባርቁ ነበሩ፡፡ ከፍተኛ የሕሊናና መንፈሳዊ ተሰጥኦ ታድሏቸው ስለ ነበረ «ከመላዕክት ትንሽ ዝቅ ብለው» ዕብ 2፡7 የሚታየውን ፍጥረተ ዓለም ትንግርት አስተውለው መመልከት እንዲችሉ ብቻ ሳይሆን የሞራል ኃላፊነትና ግዴታዎችንም እንዲገነዘቡ ሆነው ነው የተፈጠሩት፡፡EDA 16.3

    «እግዚአብሔር አምላክ በምሥራቅ ኤደን ገነትን ተከለ፡፡ የፈጠረውንም ሰው እዚያ አኖረው፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፡፡ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ መልካምና ክፉውን የምታስታውቀውን ዛፍ አበቀለ፡፡» (ዘፍ 2፡8-9) የመጀመሪያ ወላጆቻችን በዚህ ኃጢአት ባልነካው እጅግ በተዋበው ተፈጥሮ መካከል ይማሩ ነበር፡፡EDA 17.1

    ለልጆቹ ባለው ፍቅር የሰማዩ አባታችን ለነሱ የሚሰጠውን ትምህርት ራሱ ይመራው ነበር፡፡ አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔር መልዕክተኞች በሆኑት ቅዱስ መላዕክቱ ዘወትር ይጐበኙ ነበር፡፡ ከእነርሱም ምክርና ትምህርት ይቀበሉ ነበር፡፡ ሁልጊዜ በቀዝቃዛ ሰዓት በዚያ ያትክልት ስፍራ ውስጥ በሚዘዋወሩ ጊዜ የእግዚአብሔርን ድምጽ ይሰሙ ነበር፡፡ ከዘለዓለማዊዩ ጌታ ጋር ፊት ለፊት ግንኙነት ነበራቸው፡፡ እርሱ ለነሱ የሚያስብላቸው «የሰላም ሐሳብ እንጅ የክፋት አይደለም፡፡» (ኤር 29፡11)፡፡ የርሱ ዓላማዎች ሁሉ ለነርሱ እጅግ በከፍተኛ ደረጃ መልካም ነበሩ፡፡EDA 17.2

    የኤደን ገነት ያትክልት ቦታ አዳምና ሄዋን ይንከባከቡር ዘንድ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ «ያበጁትና ይጠብቁት ዘንድ፡፡» (ዘፍ 2፡15)፡፡ ምንም እንኳን የፍጥረተ ዓለም ባለቤት የሆነው አምላክ ሁሉን አትረፍርፎ ቢያቀርብላቸውም ያለሥራ እንዲቀመጡ አልነበረም፡፡ አካላቸው እንዲጠነክር፣ አእምሮአቸው እንዲሰፋ ባሕሪያቸውም ይዳብር ዘንድ ሥራ እንደበረከት ተመርጦላቸው ነበር፡፡EDA 17.3

    እንደ መጽሐፍት ሕያው የሆነውን ትምህርቷን ከነርሱ በፊት ቀድሞ ታሰራጭ የነበረችው ተፈጥሮ፣ ድካም የሌለበት ትምህርትና ደስታ ታቀርብላቸው ነበር፡፡ በእያንዳንዱ የጫካው ቅጠል ላይ፣ በእያንዳንዱ የተራራው ድንጋይ ላይ፤ በእያንዳንዱ የሚያበራ ኮከብ ላይ፣ በመሬት፣ በባህር ውስጥና በሰማይ ላይ የእግዚአብሔር ስም ተጽፎ ነበር፡፡ ሕይወት ያለውና የሌለውም ተፈጥሮ ሁሉ ቅጠሎች፣ አበቦችና ዛፎች ሕይወት ካለው ፍጥረት ጋር፤ በውሃ ውስጥ ካለው ግዙፍ እንስሳ አንስቶ በፀሐይ ጨረር ብቻ እስከሚታዩት ብናኞች ድረስ በኤደን ውስጥ የነበሩ ፍጥረቶች ሁሉ ከየራሳቸው የሕይወት ምስጢር የተሰባሰበውን ትምህርት ባንድላይ ይናገሩ ነበር፡፡ በሰማያት የእግዚአብሔር ክብር፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዓለማት በየምህዋራቸው «የደመናዎችን ሚዛን የሚጠብቅ» (ኢዮ 37፡16) የብርሃንና የድምጽን፣ የቀንና የሌሊት ምስጥር ሁሉ በመጀመሪያው የምድራችን ት/ቤት ተማሪዎች ዘንድ ዋና የትምህርት ዓይነቶች ሆነው ይቀርቡ ነበር፡፡EDA 17.4

    የተፈጥሮ ሕጐችና መስተጋብሮች፣ መንፈሳዊዩን ዓለም የሚገዙ ታላላቅ የዕውነት መሠረተ ሀሳቦች፣ ወሰን በሌለበት የፍጥረት ዓለም ሁሉ የበላይ ደራሲ በሆነው አምላክ አማካይነት ተገልጦላቸው ነበር፡፡ «በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን ዕውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ ፣ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና፡፡» (2ኛ ቆሮ 4፡6) የሕሊናቸውና የመንፈሳቸው ኃይል አደገ፡፡ የተቀደሰውን የሕልውናቸውን ከፍተኛ ደስታ አስተዋሉ፡፡EDA 18.1

    በፈጣሪ እጅ የተሠራ እንደመሆኑ የኤደን ገነት የአትክልት ሥፍራ ብቻ ሳይሆን መላው አለምም እጅግ ተውቦ ነበር የተሠራው፡፡ አንዳችም የሀጢአት ብከላ ወይም የሞት ጥላ፣ ውብ የነበረውን ተፈጥሮ አላበላሸውም ነበር፡፡ የእግዚአብሔር «ክብሩ ሰማያትን ከድኗልና ምስጋናውም ምድርን ሞልቷልና» «አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፡፡» (እን 3፡3 ኢዮ 38፡7) «ባለብዙ ቸርነትና እውነት» (ዘፀ 34፡6) የሆነውን የአምላክ ትክክለኛ የእጅ ሥራ ውጤት መሆኗን ከመግለጿም ሌላ በርሱ አምሳል ለተፈጠሩትም ጥሩ የጥናት መስክ ሆናላቸው ነበር፡፡ የኤደን ገነት የአትክልት ቦታ እግዚአብሔር መላዋ ዓለምም ምን እንድትመስል እንደሚፈልግ የምታስረዳ መግለጫ ነበረች፡፡ የሰው ልጆች እየበዙ በሄዱ መጠን እርሱ እንደ ሰጣቸው፣ እንደ ኤደን ገነት ዓይነት መማሪያና መኖሪያ ስፍራዎች ይኖራቸው ዘንድ ዓላማው ነበር፡፡ በጊዜ ሂደትም መላው ዓለም የርሱ ቃልና ሥራዎች ጥናት በሚካሄድባቸው ቤቶችና ትምህርት ቤቶች ትሞላ ዘንድ፣ ተማሪውም ለዘለዓለም ማብቂያ በሌላቸው ዘመናት የእርሱን ክብር በማወቅ፣ የሚገኘውን ብርሃን ይበልጥ ያንፀባርቅ ዘንድ ነው፡፡EDA 18.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents