Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጳውሎስ ደስተኛው አገልጋይ

    ከእምነትና ከተካበተ ልምድ ጋር ገሊላዊያን ሐዋሪያት እሳት በተላበሰ ጥንካሬ እና በየሩሳሌም ረቢ የእውቀት ብርታት ከእየሱስ ጋር በወንጌል ሥራ አንድ ሆኑ፡፡ ዜግነቱ ሮማዊ ርጋታ በተሞላበት ከተማ ተወልዶ ዘሩ ይሁዳዊ ሲሆን ከጥንት ተያይዞ በወረደለት ብቻ ሳይሆን በእድሜልክ ስልጠና የአርበኝነት መንፈስ እና ሃይማኖታዊ እምነት በየሩሳሌም የረቢ ዋነኛ ተከታዮች አማካኝነት የተማረ በአባቶች ሕግጋትና ወግ የተገራ የጠርሴሱ ሳውል የርሱ ወገን የሆነው ሕዝብ ካገኘው ክብርና ድንቅ ግምት እሱም በድርሻው ሙሉውን አግኘቷል፡፡ ገና ወጣት ሰው ሆኖ እያለ የሰነሃድሪን የተከበረ አባል ሆነ፡፡ ተስፋ የሚጣልበት ሰው ሆኖ ታየ፡፡ ለጥንታዊዩ እምነት ቅናት የተሞላበት ታጋይ ነበር፡፡EDA 69.1

    በይሁዳ የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት የእግዚአብሔር ቃል ወደጐን ገለል ተደርጐ በሰብዓዊ የግምት አሰተሳሰብ ሳቢያ በረቢያዊያን አተረጓጐምና ልማድ ኃይሉን ተነጥቆ ነበር፡፡ የግል ሐብት በማጋበስ በበላይነት ስሜት መኩራራት ቀናተኛነት የጭንቀት ኩራት በግል ሐሳብ ግትር መሆን የእነንህን መምህራን ፍላጐቶች የሚገዙ ስሜቶች ነበሩ፡፡EDA 69.2

    ረቢያዊያን በበላይነታቸው ተኮፍሰው ለሌላ ወገን ሰዎች ብቻ ሳይሆን በራሳቸውም ሕዝብ ላይ ተኩራርተው ነበር፡፡ በረማዊያን ጨቋኞቻቸው ላይ በነበራቸው ክፉ ጥላቻ ብሔራዊ የበላይነታቸውን በጦር ኃይለ ለማስመለስ ወሰኑ፡፡ የየሱስ ተከታዬች የነበሩ ረቢያዊያን ካሰቡትና ካለሙት ተፃራሪ የሆነ የሰላም መልዕክት ስለነበር እጅግ ጠሉት፡፡ ይህንን አስተሳሰብም ገደሉት፡፡ በዚህ የማሳደድ ሥራ ውስጥ ዋናው በቁርጠኝነት አምርሮ ይታገል የነበረው ተዋናይ ሳውል ነበር፡፡EDA 69.3

    በግብጽ የወታደራዊ ት/ቤቶች ውስጥ ሙሴ የኃይል አጠቃቀምን ሕግ ተምሮ ነበር፡፡ ይህ ትምህርትም በባህሪው ውስጥ ክፉኛ ተቀርጾበት ስለነበረ እሰራኤልን በፍቅር ሕግ የሚመራ ሰው ለመሆን ከእግዚአብሔርና ከተፈጥሮ ጋር ፀጥታ በሞላበት ግንኙነት በማድረግ አርባ ዓመታት የቆይታ ጊዜ አስፈልጐታል፡፡ ያንኑ ትምህርት ጳውሎስም መማር ነበረበት፡፡EDA 70.1

    በደማስቆ በር ላይ የተሰቀለውን ጌታ በራዕይ በማየቱ በሁለንተናዊ ሕይወቱ ላይ ለውጥ አመጣ፡፡ አሳዳጁ ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ አስተማሪ የነበረው ተማሪ ሆነ፡፡ በደማስቆ በብቸኝነት ያስለፋቸው ቀናት በሕይወቱ ውስጥ እንደ ዓመታት የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡ በአዕምሮው ውስጥ ያከማቿቸው የብሉይ ኪዳነ ጽሁፎች የጥናት ትኩረቶቹ ቤቱ ሆኖለት ነበር፡፡ ስለ እግዚአብሔርና ስለ መጽሐፍት ለማጥናት ወደ አረቢያ በረሃ ሄደ፡፡ በዚያም ሕይወቱን የቀረፀለትን ያልተሟላ ዕውቀትና የልማድ ሕጐች አራገፈና የእውነት ምንጭ ከሆነው መመሪያዎችን ተቀበለ፡፡EDA 70.2

    የእሱ ወደኋላ የነበሩ ዘመኖቹን ራስን መስዋዕት በማድረግና በፍቅር አገልግሎት መሠረታዊ ሐሳቦች የተነቃቁ ነበሩ፡፡ «ታውቁ ዘድ እወዳለሁ፡፡ ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩ በጥበበኞች ለማያስተውሉ እዳ አለብኝ፡፡» «...የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና» ሮሜ 1፡12 2ኛ ቆሮ 5፡14EDA 70.3

    ከሰው ልጆች መምህራን ሁሉ ታላቁ መምህር ጳውሎስ፣ ከትንሻ አስከ መጨረሻው ታላቅ ድረስ ያለውን ኃላፊነት ተቀብሏል፡፡ የእጅና የአእምሮን ሥራ አስፈላጊነት ተገነዘበ፡፡ በመሆኑም በእጅ ሥራ ድንኳን እየሰራ ለኑሮው መደጐሚያ የሚሆን ያገኝ ነበር፡፡ ለድንኳን መሥሪያ የሚሆን ክር እያዘጋጀ ራሱን ሲረዳ በታላላቅ የሥልጣኔ ማዕከላት ውስጥም በየቀኑ ወንጌልን ይሰብክ ነበር፡፡ «እነዚህ እጆች» አለ በኤፌሶን ሽማግሌዎችን ሲለይ «እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ለእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናነተ ታውቃላችሁ፡፡» የሐዋ ሥራ 20፡34EDA 70.4

    ከፍተኛ ያስተሳሰብ ችሎታ የታደለ ሰው ሲሆን የጳውሎስ ሕይወት ከስንት አንድ ሰዎች የሚያገኙት ልዩ የጥበብ ኃይል አንደነበረው ተገለጧል፡፡ እጅግ ታላቅ በጣም ጥልቀት ያላቸው መሠረታዊ ሐሳቦችን እጅግ ታላቅ አእምሮ አላቸው የሚባሉ የዛሬ ጊዜ ሊቃውንት ያላወቋቸው መሠረታዊ ሐሳቦች እሱ ባስተማራቸው ትምህርቶች ውስጥና በራሱ ሕይወትም ገለጧቸዋል፡፡ ብሩህና ቀልጣፋ የሚያደርገውንና ልብን የሚያራራ ሰውን ከሰዎች የሚያግባባ በዚህም ድንቅ የተፈጥሮ ተሎታቸውን ማነሳሳት ወደተሻለ ከፍተኛ የሕይወት ደረጃ እንዲደርሱ ለመቀስቀስ የሚረዳው ከሁሉም የሚበልጥ ታላቅ ጥበብ ነበረው፡፡EDA 71.1

    በአረመኔ ሊያስትሪያን ፊት የተናገረውን ቃል ስሙ፡፡ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔርን ሲያመለክታቸው እንዲህ ብሏል፡፡ «ከሰማይ ዝናብን የሚሰጠን ልባችንም በምግብና በደስታ የሚሞላ ዘመን፡፡» የሐዋ ሥራ 14፡17EDA 71.2

    በፊሊጲስዩስ በሰናጐግ በነበረ ጊዜ ይታያችሁ፡፡ አካላቱ እንደዚያ በስቃይ ተጐድቶ እያለ እኩለሌሊት ላይ የምስጋና መዝሙር ድምጹ የውድቀቱን ፀጥታ ሰንጥቆ ሲወጣ ይሰማ ነበር፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ በእስር ቤቱን በሮች ከከፈተው በኋላ ለወህኒ ቤት ጠባቂው በደስታ እልልታ ሲናገር ድምጹ እንደገና ተሰማ፡፡ «ራስህን እንደትገድል እኛ ሁላችን እዚህ አለን፡፡» የሐዋ ሥራ 16፡28 ሰው ሁሉ በዚያው በየቦታው ነበረ፡፡ ሁሉም በአንድ እስረኛ ጓደኛቸው ተጽናነተው ተቆጥበው ተቀመጡ፡፡ የእስር ቤቱ ጠባቂ ወታደርም ለጳውሎስ ብርታት የሆነው እምነት እውነተኛና ትክክለኛ መሆኑን አመነ፡፡ የደህንነትን መንገድም ከነቤተሰቡና ከተሰደዱት ደቀ መዛሙርት ጋር ጠየቀ፡፡EDA 71.3

    ጳውሎስን እስቲ እንደገና በአቴና በኤሮፓገስ ምክር ቤት ሳይንስን በሳይንስ ሎጅክን በሎጅክ፣ ፍልስፍናን በፍልስፍና ሲሞግታቸው ተመልከቱ፡፡ ከእግዚአብሔር በፈለቀ በፍቅር ዘዴ አቭን ‹የማይታወቀው አምላክ› በማለት ያዳምጡት የነበሩ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ያመልኩት እንደነበረና ራሳቸውም ይቀኙለት ከነበረው ግጥም አንዱን በመጥቀስ ያ የተቀኙለት አምላክ የእነሱ አባት እንደሆነና እነርሱም ልጆቹ አንደሆኑ ያመለከታቸው ነበር፡፡ ያዳምጡትም ነበር፡፡ በዚያ በሕዝብ መካከል የተወሰትን በንቀት የማግለል እርኩስ ዘመን የሰው ልጅ እነደሰው መብቶቹ የማይከበረበት ጊዜ እሱ ግነ የሰው ልጅን ወንድማማችነት፤ እግዚአብሔር «የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ፡፡» በማለት ያስተምር ነበር፡፡ ይህን በግልጽ እንደአዋጅ ይናገር ነበር፡፡ ከዚያ በኋላም እግዚአብሔር በሰው ጋር በሚኖረባቸው ቦታዎች ሁሉ የፀጋውና የምህረቱ በሥራው እንደወርቅ ክር እንደሚገባ ያሳያል፡፡ «ለማይታወቅ አምላክ የሚል ጽህፈተ ያለበትን መሰወያ ደግሞ አግኝቻለሁ፡፡» እንግዲህ ይኸንን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ አነግራችኋለሁ፡፡ «እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፡፡ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም፡፡» የሐዋ ሥራ 17፡232627EDA 72.1

    በፊስጦስ አደባባይ ላይ ንጉሥ አግሪጳ የወንጌልን እምነት በመቀበል «ክርስቲያን ልታደረገኝ ምንም አልቀረህም፡፡» እስከ ማለት ሲደርስ ተመልከቱ፡፡ ጳውሎስም ወደ ታሠረበት ሰንሰለት እያመለከተ በታላቅ ርጋታ እንዲህ ሲል መለሰ፡፡ «ጳውሎስም በጥቂት ቢሆን በብዙ አንተ ብቻ አይደለህም ነገር ግን ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ ደግሞ ከዚህEDA 72.2

    እስራት በቀር እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እለምናለሁ፡፡ አለው፡፡» የሐዋ ሥራ 26፡2829EDA 73.1

    በእንዲህ ዓይነትም ሕይወቱ አለፈ፡፡ በራሱ አባባል እንደተገለፀው «ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁ በወንዝ ፍርሃት በወንበዴዎች ፍርሃት በምደረ በዳም ፍርሃት በባሕር ፍርሃት በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረኝ በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት በራብና በጥም ብዙ ጊዜ በመጦም በብርድና በራቁተነትም ነበርሁ፡፡» 2ኛ ቆሮ 11፡2627EDA 73.2

    «በመገለጽም» አለ «በገዛ እጃችን እየሰራን አንደክማለን፣ ሲሰድቡን እንመርቃለን፡፡ ሲያሳድዱን እንታገሳለን፣ ክፉ ሲናገሩና እንማለደለን እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል፡፡» «ሐዘነተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፡፡ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለጠጐች እናደርጋለን፣ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ሰው፡፡» 1ኛ ቆሮ 4፡12-13 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡10EDA 73.3

    በአገለግሎት ደስታውን አገኘ፡፡ እናም በሕይወቱ ማብቂያ ላይ በመከራ ያሰለፈው ትግልና ያገኘውን ድል ወደኋላ መለሰ ብሎ በመመልከት እንዲህ ለማለት ችሏል፡፡ «መልካሙን ገድል ተጋደለሁ» 2ኛ ጢሞ 4፡7EDA 73.4

    እነኝህ ታሪኮች በጣም ደስ የሚያሰኙ ናቸው፡፡ ለወጣቶች የሚሆኑትን ያክል ለሌላ ለማንም በጣም አስፈላጊ አይሆኑም፡፡ ሙሴ ያስበው ስለነበረው መንግሥት ግዛት ተናገረ፡፡ ጳውሎስ ደግሞ የራሱ ወገን በሆነው ሕዝብ መካከል ሐብትና ክብርን ለማግኘት ኋላ ደግሞ በእግዚአብሔር አገልግሎት ሸክም የመቀበል ሕይወት አሳለፈ፡፡ የእነኝህ ሰዎች ሕይወት ራስን የመካድና የመስዋዕተነት ሕይወት ነበር፡፡ አይደለምን? ሙሴ ወደ ክርስቶስ መቅረብ በግብጽ ከነረው ሐብት ሁሉ የሚበልጥ እንደሆነ አድርጐ ተመለከተ፡፡ እንደዚያ እንደሆ ቆጠረው፡፡ በእርግጥም እንደዚያ ነበረና፡፡ ጳውሎስም እንዲህ ሲል ተናገረ፡፡ «ነገር ግን ለኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቆጥሬአለሁና፡፡ አዎን በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ እየሱስ ስለጌታየ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ ስለእርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፡፡» ፊሊ. 3፡78 በምርጫውም ረክቶ ነበር፡፡EDA 73.5

    ሙሴ የፈርኦን ቤተ መንግሥትና የንጉሥ ዙፋን ተሰጥቶት ነበር፡፡ ነገር ግን ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲረሱ የሚያደርጋቸው ከሐጢአት የሚገኙ ደስታዎች በዚያ የጌቶች አደባባይ ላይ ነበሩ፡፡ ስለዚህ ምንጫው «ብልጽገናና ክብር ከኔ ዘንድ ነው፡፡ ብዙ ሐብትና ጽድቅም፡፡» ምሳሌ 8፡18 ራሱን በግብጽ ኃያልነት ጋር ከማያያዝ ይልቅ ሕይወቱን ከእግዚአብሔር ዓላማ ጋር ማስተሳሰርን መረጠ፡፡ ለግበጽ ከማውጣትና ከመስጠት ይልቅ በመለኮት ኃይልና መመሪያ የተዘጋጁ ሕጐችን ለመላው ዓለም አወጀ፡፡ ለቤተሰብና ለሕበረተሰብ ደህነነት የሚበጁ መርሆች በማበርከት የእግዚአብሔር መሣሪያ ሆነ፡፡ እነኝህ መሠረታዊ ሐሳቦች ለሕዝቦች ብልጽግና የማዕዘን ድንጋይ የሆኑ በዛሬዋ ዓለም ታላላቅ ሰዎች ዘንድ እንኳ ከሰው ልጅ መንግሥታት ጠቃሚ መሠረት እንደሆኑ የታወቁ ዋና ዋና ሀሳቦች ናቸው፡፡EDA 74.1

    የግብጽ ታላቅነት አሁን አቧራ ለብሷል፡፡ ኃይሏና ሥልጣኔዋ አለፏል፡፡ የሙሴ ሥራ ግን ምን ጊዜም ሊጠፉ አይችሉም፡፡ እርሱ በሕይወቱ ያቋቋማቸውና የኖረባቸው ተላላቅ የጽድቅ መሠረታዊ ሀሳቦች ዘለዓለማዊ ናቸው፡፡EDA 74.2

    የሙሴ የልፋትና የድካም ሕይወትና ለሰዎች በመጨነቅ የተሰበረው ልቡ «ከሸዎች መካከል አለቃ በሆነው» «በሙሉ ተወዳጅ በሆነው» 5፡1016 ሰው መምጣት ታደሰ፡፡ ከክርስቶስ ጋር በበረሃ በመንከራተት ከክርስቶስ ጋር በአስደናቂ ግርማ ሞገስ ባላቸው ተራሮች ከክርስቶስ ጋር በሰማይ አደባባዮች የእሱ ሕይወት በመሬት የተበረከና ለሌሎችም በረከት የነበረ ሲሆን በሰማይ ደግሞ የተከበረ ለመሆን በቅቷል፡፡EDA 75.1

    ጳውሎስም ደግሞ ሁለገብ በሆነው ሥራው አበርታች ኃይል በሆነው በእርሱ ይታገዝ ነበር፡፡ «ሁሉንም አደረጋለሁ፡፡» አለ ጳውሎስ «በክርስቶስ በርታት በሆነኝ፡፡» «ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡» «ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናለ? መከራ ወይስ ጭንቀት ወይስ ስደት ወይስ ረሀብ ወይስ ራቁትነት ወይስ ፍርሃት ወይስ ሰይፍ ነውን? ሞት ቢሆን ሕይወት ቢሆንም መላእክትም ቢሆኑ ግዛትም ቢሆን ክቅታም ቢሆን ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ እየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንደይችል ተረድቻለሁ፡፡» ፊሊጵ 4፡13 ሮሜ 8፡35-39EDA 75.2

    ይሁንና ጳውሎስ አሻግሮ ወደፊት የተመለከተው ደስታ ነበር፡፡ የሥራው ውጤት ዋጋ ያ ክርስቶስ መስቀሉን በመሸከም የተሰቃየበትና በዚያም ያላፈረበት ተግባር የሥራውን ፍሬ በማየት የተደሰተበት፡፡ «ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይም ትምክህታችን አክሊል ማነው? በጌታችን በየሱስ ፊት በመምጣቱ እናነተ አይደላችሁምን? እናንተ ክብራችንም ደስታችንም ናችሁና፡፡» 1ኛ ተሰሎ 2፡1920EDA 75.3

    በጳውሎስ የሕይወት ሥራ ዓለም የተገኙት ወጣቶች በመስፈርት መለካት የሚችለው ማነው? ከዚያ ሁሉ የመሳብ ኃይል ስቃዩን ያስታገሱ ያዘኑትን ልቦች ያጽናኑ ከክፉ ሥራ ጥፋት ያዳኑ፤ ራስን ከውደድና ስሜታዊ ከመሆን ሕይወት ያወጡ እናም በማይሞተ ተስፋ ነፍስን ያከበሩ ለጳውሎስና ለተከታዮቹ የሥራ ዋጋ ሊከፈላቸው የሚገባው ምን ያክል ነው? የእግዚአብሔር ልጅ በወንጌል እንደተገለፀው ሁሉ እነርሱም ከእስያ እስከ አውሮፖ የባህር ዳርቻዎች ድረስ ያልታወቀ ጉዞ ያደረጉትስ? EDA 75.4

    እንዲህ ዓይነት የበረከት ሥራ በመትከል የእግዚአብሔር መሣሪያ የሆነ ማንኛውም ሕይወት በሰማይ ምን ያክል ዋጋ ይኖረዋል? በዘለዓለማዊው ቤት ዘንድ ለእንዲህ ዓይነቱ የሕይወት ሥራ ውጤት ማስረጃ ምስክር የሚሆነው ዋጋ ምንድን ነው? EDA 76.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents