Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እውነተኛና ቅን ሰዎች

    በጥበባቸውና በፍርድ ችሎታቸው በንጽህናና በየቀኑ የደግነት ሕይወታቸው ለህዝብ ፍላጐት ባላቸው ልባዊ ስሜት፣ በጣኦት አምላኪዎች ፊት ዮሴፍና ዳንኤል በልጅነታቸው የተማሩአቸው ዋና መሠረታዊ ሐሳቦች ትክክለኛ ወኪል ለሆኑለት አምላክም ፍፁም እውነተኛ መሆናቸውን አስመሰከሩ፡፡ እነኚህን ሰዎች በግብጽና በባቢሎን ውስጥ ሕዝብ በሙሉ አክብሯቸዋል፡፡ በእነሱም አማካይነት ሃይማኖት የሌላው አረመኔ ሕዝብና በየጊዜው በየምክንያቱ የተገናኙአቸውን ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ስለ እግዚአብሔር በረከትና ቸርነት ትምህርት ሊሰጧቸው ችለዋል፡፡ ይህም የክርስቶስ ፍቅር መግለጫ ትምህርት ነው፡፡EDA 59.1

    እነኝህ የተቀደሱ እብራዊያን ምንኛ የሚያስደንቅ የሕይወት ሥራ ነው የሠሩት! የልጅነት ቤታቸውን ተሰናብተው ሲሄዱ ስለዚህ ታላቅና ከፍተኛ ተልዕኮአቸው የሚያውቁትና ያለሙት ምንም ዓይነት ነገር አልነበረም፡፡ በጽንአት የሚያምኑ ስለነበሩ እግዚአብሔር በእነሱ አማካይነት ዓላማዉን ያስፈጽም ዘንድ ራሳቸውን ለመለኮት አመራር አስገዙ፡፡EDA 60.1

    በእነኝሁ ሰዎች አማካይነት የተገለፁ እጅግ ታላላቅ እውነቶች በዛሬ ወጣቶችና ልጆች እንዲገለጡ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ የዮሴፍና የዳንኤል ታሪክ የሚያስረዳን ነገር ቢኖር ራሳቸውን ለእርሱ የሚያስገዙ የእርሱን ሐሳብ ለማከናወነ ከልባቸው ለሚነሱ ሰዎች እርሱ ምን እንደሚያደርግላቸው ነው፡፡EDA 60.2

    ዓላማችን አሁን የምትፈልገው ነገር ቢኖር ሰዎችን ማግኘት ነው፡፡ የማይሸጡና የማይለዋወጡ ሰዎችን ከውስጥ ከለባቸው እውነተኛና ቀና የሆኑ ሰዎች ኃጢአትን በትክክለኛ ስሙ ለመጥራት የማይፈሩ ሰዎች አዕመሮአቸው አንደ ኮምፓስና እንደ አመልካቿ ቀስት በእውነት ለሥራ ብቻ የሚቆሙ ሰዎችን ነው የምትፈልገው፡፡EDA 60.3

    ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ባህሪይ በአጋጣሚ የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ በልዩ አስተያየትና ችሮታ የሚሰጠን ነገርም አይደለም፡፡ ክቡር የሆነ ባህሪይ ራስን ለሥነ-ሥርዓት በማስገዛት የሚመጣ ነው፡፡ የበታች የሆነው ፍጡር የበላይ ለሆነው ራሱን ለእግዚአብሔርና ለሰዎች ፍቅር አገልግሎት በመስጠት የሚገኝ ነው፡፡EDA 60.4

    ወጣቶች የተሰጧቸው ክህሎቶች በራሳቸው ያገኛቸው እንዳልሆኑ ሊረዱ ይገባል፡፡ ብርታት እድሜ ብልህነት በብድር የሚገኙ ነብረቶች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር የግሉ ናቸው፡፡ ስለዚህም እያንዳንዱ ወጣት ከፍተኛ ጠቀሜታ ላይ ሊያውላቸው ይገባል፡፡ ወጣቱ እግዚአብሔር ፍሬ የሚሰበስብበት ቅርንጫፍ ነው፡፡ አስተናጋጅ አሳላፊ ነብረቱ እንዲጨምርለት የዓለምንነ ጨለማ ያስወግድ ዘንድ ቀንዲል እንዲሆን ያስፈልገዋል፡፡EDA 61.1

    እያንደንዱ ወጣት እያንዳንዱ ልጅ ለእግዚአብሔር ክብር እና ለሰው ልጅ እድገት የሚሰራው ሥራ አለው፡፡EDA 61.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents