Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 34—ሥነ - ሥርዓት

    አንድ ልጅ በመጀመሪያ ሊማራቸው ከሚገባው ትምህርቶች አንደኛው መታዘዝን ማወቅ ነው፡፡ ልጁ ከመብሰሉና ራሱ ማመዛዘን ከመቻሉ በፊት መታዘዝን መማር አለበት፡፡ ጨዋነት በተሞላበት፣ ጽናት በሚያይበት ጥረት ልማዱ ሊታነጽ ይገባዋል፡፡ ስለሆነም ወደኋላ ዘመኑ በልጁ ፍላጎትና ሥልጣን ባለው አካል መካከል የሚመጡ ግጭቶች ሊከላከልለት፣ ከወላጆችና ከመምህራን በጥላቻና በምሬት መራራቅን፣ ብዙ ጊዜም ባለሥልጣን ከሆነው ሁሉ ማለትም ከሰብዓዊና መለኮታዊውም ጭምር ከማፈንገጥ ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርግለታል፡፡EDA 323.1

    የሥነ - ሥርዓት ዓላማ ልጅ ራሱን በመግዛት እንዲሰለጥን ነው፡፡ በራስ መተማመንንና ራስን መቆጣጠርን መማር አለበት፡፡ በጥሩ ሁኔታ ማስተዋል እንደ ጀመረ ወዲያውኑ የማሰብና የማመዛዘን ችሎታው ከመታዘዝ አንፃር መሆን አለበት፡፡ ከርሱ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ሁሉ ታዛዥነትን፣ ቅንነትንና አመዛዛኝነትን ለማሳየት መሆን አለበት፡፡ ሁሉም ነገሮች ከሕግ ሥር መሆናቸውንና አለመታዘዝ ደግሞ በመጨረሻ ወደ ጥፋትና ስቃይ እንደሚያመራ ይመለከት ዘንድ አሳዩት፡፡ እግዚአብሔር ‹‹ይኸንን አታድርግ›› ሲል እኛን ከጉዳትና ከጥፋት ለማዳን አለመታዘዝ የሚያስከትለውን ውጤት በፍቅር ያስጠነቅቃል፡፡EDA 323.2

    ልጁ ወላጆችና መምህራን የእግዚአብሔር ወኪሎች መሆናቸውንና ከእርሱም ጋር በአንድነት በሚሠሩበት ጊዜ በቤታቸው ውስጥና በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉት ሕጎችም የርሱው መሆናቸውን እንዲያይ እርዱት፡፡ ልጁ ለወላጆቹና ለመምህራን ታዛዥ በመሆን ሲያገለግል እነርሱም ደግሞ በአፀፋው ለእግዚአብሔር በታዛዝነት ማገልገል አለባቸው፡፡EDA 323.3

    ልጁን ከአግባብ ውጪ በሆነ ቁጥጥር እድገቱን ያለማደናቀፍ መምራት የወላጆችና የመምህራን ጥረት መሆን አለበት፡፡ አመራሩን እጅግ ማጥበቅ እጅግ የማላላትን ያክል ጉዳት አለው፡፡ የልጁን ‹‹ፍላጎት ለመስበር›› ጥረት ማድረግ ትልቅና አሳዛኝ ስህተት ነው፡፡ አእምሮዎች በተለያዩ መንገዶች የተሠሩ ናቸው፡፡ ኃይል በምንጠቀምበት ጊዜ ለጊዜው በውጪ ተሸናፊነት ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ውጤቱ ብዙ ልጆች በልባቸው የበለጠ የቁርጠኝነት አመጽ ሊያድርባቸው ይችላል፡፡ ወላጅ ወይም መምህር ያ የፈለገው ዓይነት ቁጥጥር ቢሳካለትም እንኳ ውጤቱ በልጁ ላይ ያው የማይተናነስ ጉዳት ማድረሱ አይቀርም፡፡ ከሚያስተውልባቸው ዘመናት ላይ ሲደርስ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚወሰደው የሥነ - ሥርዓት እርምጃ አንድን ከብት ለማሰልጠን ከምንጠቀምበት ጋር መለየት አለበት፡፡ እንስሳው መማር የሚኖርበት ለጌታው መገዛትን ማወቅ ብቻ ነው፡፡ ጌታው ለእንስሳው እንደ አእምሮ፣ ዳኛና የእንስሳውን ፍላጎትና ፈቃድ ተቆጣጣሪ ነው፡፡ ይህ ዘዴ በሕፃናት ትምህርት ውስጥ ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ ከማሽን በትንሽ የሚለዩ ያስመስላቸዋል፡፡ አእምሮ፤ ፍላጎትና ሕሊና በሌላ ሰው ቁጥጥር ሥር ይሆናሉ፡፡ ማንኛውም አእምሮ በዚህ ዓይነት ተጽዕኖ እንዲደርስበት የእግዚአብሔር ዓላማ አይደለም፡፡ በዚህ ዓይነት ግላዊነትን የሚያዳክሙ ወይም የሚያጠፉ ሰዎች ውጤቱ ክፉ ብቻ የሆነ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በአንድ ኃላፊ ሥር በሚሆንበት ጊዜ ተማሪዎች በደንብ የተገራ ወታደር ይመሥላሉ፡፡ ነገር ግን ቁጥጥሩ ሲያበቃ እንደተለቀቁ ወዲያውኑ ባህሪያቸው ብርታትንና ጽናት ያጣል፡፡ ራስን መግዛት ሳይማር ከቀረ ወላጆቹ ወይም መምህራኑ ከሚፈልጉት ነገር ውጪ ምንም ገደብ የማያውቅ ይሆናል፡፡ እናም ይህ በሚነሳለት ጊዜ የራሱን ነፃነት እንዴት እንደሚጠቀምበት የማያውቅ ይሆናል፡፡EDA 324.1

    በተሸናፊነት ተንበርክኮ ፈቃድና ፍላጎትን ለሌላ ማስገዛት ለአንዳንድ ተማሪዎች ከሌሎች በተለየ ይበልጥ አስቸጋሪ ስለሚሆንባቸው መምህሩ የሚሰጣቸው ትዕዛዝ በተቻለ መጠን ቀላል እንዲሆንላቸው ማድረግ አለበት፡፡ ፈቃዳቸው መመራትና መቀረጽ እንድ ችላ ተብሎ መዘጋት ወይም መጨፍለቅ የለበትም፡፡ የፍላጎታቸውን ብርታት ይጠብቅላቸው፡፡ ምክንያቱም በሕይወት ጦርነት ውስጥ ተፈላጊ ነውና፡፡EDA 325.1

    እያንዳንዱ ልጅ የፍላጎትን አስገዳጅነት ማስተዋል አለበት፡፡ በዚህ ስጦታ ውስጥ የተካተተው ኃላፊነት ምን ያክል ታላቅ እንደሆነ እንዲያይ መመራት አለበት፡፡ ፍላጎት በሰው ተፈጥሮ ውስጥ ገዥ ኃይል፤ የመወሰን ወይም የመምረጥ ኃይል ነው፡፡ የማሰብና የማመዛዘን ኃይል ያለው እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ትክክለኛውን የመምረጥ ኃይል አለው፡፡ በእያንዳንዱ የሕይወት ገጠመኝ ውስጥ ለእኛ የእግዚአብሔር ቃል ‹‹የምታገለግሉትን ››› እነሆ ዛሬ ምረጡ›› የሚል ነው፡፡ ኢያሱ 24፡15 እያንዳንዱ ፍላጎቱን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጎን የሚያደርግ ሰው፤ ለርሱ መታዘዝን ሲመርጥ በዚህም ራሱን ከመለኮት ኃይሎች ጋር በማገናኘት ክፉ እንዲሠራ ማንም ሊያስገድደው ከማይችልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡ በእያንዳንዱ ወጣትና በእያንዳንዱ ልጅ ውስጥ በእግዚአብሔር እርዳታ የተረጋጋ ባህሪይ ለመቅረጽ የጠቃሚነት ሕይወት ለመኖር በውስጡ ኃይል አለው፡፡EDA 325.2

    በእንዲህ ዓይነት ትምህርት ልጁን ስለራስ መቆጣጠር የሚያስተምር ወላጅ ወይም መምህር እጅግ ጠቃሚና ለዘለቄታውም የሚሳካለት ይሆናል፡፡ ላይ ላዩን ብቻ ለሚመለከት ሰው የዚህ መምህር ወይም ወላጅ ሥራ እምብዛም ጠቃሚ ላይመስለው ይችላል፡፡ የልጁን አእምሮና ፍላጎት ሁሉ በሥልጣኑ ቁጥጥር ሥር እንዳዋለው ሰው ከፍተኛ ግምት አይሰጠው ይሆናል፡፡ ከአመታት በኋላ ግን መራራው የአሰለጣጠን ወይም የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ውጤቱ ይታያል፡፡EDA 325.3

    ጠቢቡ አስተማሪ ለተማሪዎቹ በሚኖረው አያያዝ እምነት እንዲያድርባቸው ማደፋፈር የክብር ስሜት እንዲኖራቸው ማበረታታት ይፈልጋል፡፡ ልጆችና ወጣቶች ተአማኒ በመሆናቸው ይጠቀማሉ፡፡ ብዙዎች ሕፃናትም ቢሆኑ አንኳን ከፍተኛ የመከበር ስሜት አላቸው፡፡ ሁሉም እምነት እንዲጣልባቸውና በመከበር እንዲያዙ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ደግሞ መብታቸው ነው፡፡ ያለ ጥበቃ መውጣትና መግባት እንደማይችሉ ተደርጎ እስከሚሰማቸው ድረስ አመራር ሊሰጣቸው አይገባም፡፡ ጥርጣሬ፤ ሊከላከሉት የሚፈልጉትን ያንኑ ክፉ ውጤት በማስተከል ሞራልን ይገድላል፡፡ ክፉ ነገር እንደሚጠረጥር ሰው ያለማቋረጥ ከመጠበቅ ይልቅ ከተማሪዎቻቸው ጋር ግንኙነት የሚኖራቸው መምህራን ረፍት የለሽ የሆነው አእምሮ የሚሠራቸውን ነገሮች መለየት ይችላሉ፡፡ እናም የክፉው ተቃራኒ የሆነውን እንዲሠራ ያዘጋጁታል፡፡ ወጣቶች እምነት የሚጣልባቸው እንደሆኑ እንዲሰማቸው አድርጋችሁ ምሯቸው፡፡ ለተጣለባቸው እምነትም ብቁ መሆናቸውን ማስመስከር የማይችሉ ጥቂቶች ይኖራሉ፡፡EDA 326.1

    በተመሣሣይ መሠረተ ሐሳብ ደረቅ ትዕዛዝ ከመስጠት ይልቅ በትሕትና መጠየቅ የተሻለ ይሆናል፡፡ በዚህ ዓይነት ተጠያቂው ትክክለኛ ለሆኑ መሠረት ሐሳቦች ራሱን ታማኝ አድርጎ የማቅረብ እድል ይኖረዋል፡፡ ታዛዥነቱ የራሱ የምርጫ ጉዳይ እንጂ በግዴታ አይደለም፡፡EDA 326.2

    የመማሪያ ክፍሎች የሚገዙበት ሕግ በተቻለ መጠን የትምህርት ቤቱን ድምጽ መወከል መቻል አለበት፡፡ በውስጣቸው የተካተቱ መሠረታዊ ሐሳቦች ሁሉ አንድ በአንድ በተማሪው ፊት ቀርበው ምን ያክል ፍትሐዊ እንደሆኑ እንዲያምንባቸው ቢደረግ መልካም ነው፡፡ ምክንያቱም ጽኑ ተፈፃሚ ይሆኑ ዘንድ እሱም በድርሻው አስተዋጽኦ ያደረገባቸው ስለሚሆኑ ሕጎቹ መከበርና መፈፀመ እንዳለባቸው ኃላፊነቱ ይሰማዋል፡፡EDA 326.3

    ሕጎቹ ጥቂቶችና በሚገባ የተጤኑ መሆን አለባቸው፡፡ እናም አንድ ጊዜ ከተቀረፁ በኋላ በተግባር መተርጎም አለባቸው፡፡ ለመለወጥ አስቸጋሪ ሆኖ የተገኘውን ነገር ሁሉ አእምሮ ሲገነዘበውና ሊለማመደው ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ጥፋት የማዘንበል ሁኔታ ፍላጎትን ተስፋንና እርግጠኛ አለመሆንን ያስከትላል፡፡ ውጤታቸውም ረፍት የለሽነት ብስጩነትና ተገዥ አለመሆን ነው፡፡EDA 327.1

    የእግዚአብሔር መንግሥት ከክፋት ጋር መደራደር የማያውቅ መሆኑ ግልጽ መደረግ አለበት፡፡ አለመታዘዝ በቤትም ሆነ በትምህርት ቤት ውስጥ በቀላሉ መታለፍ የለበትም፡፡ ለልጆቹ አጠቃላይ ደህንነት ከልቡ ለሚያስብና ደህንነታቸውም በእጆቹ ውስጥ የሆነ ማንኛውም ወላጅ ሆነ መምህር ከትዕዛዝ ለማምለጥ ሲል በኃይለኛ የግል ፍላጎት የበላዩን በግልጽ የሚቃወም ወይም በብልጠት ማጭበርበርና በልመና ዓይነት የማታለል ዘዴ ከሚጠቀም ልጅ ጋር የሚደራደር አይሆንም፡፡ ክፉ ሥራን በቀልድ በዋዛ የሚፈጽም ወይም ትብብር ለማግኘት በማባበልና ጉቦ ዓይነት ነገር የሚያቀርብ በመጨረሻ በሚፈልገው ነገር ሌላ ምትክ የሚፈልግ ሰው ሁሉ የፍቅር ሣይሆን መንፈሰ ደካማ በመሆኑ የሚያደርገው ነው፡፡EDA 327.2

    ‹‹ሰነፍ በኃጢአት ያፌዛል፡፡›› ምሳ 14፡9 ኃጢአትን እንደ ቀላል ነገር ከመቁጠር መጠንቀቅ አለብን፡፡ በጥፋተኛው ሰው ላይ የሚኖራት ኃይል ከባድ ነውና፡፡ ‹‹ኃጢአንን ኃጢአቱ ታጠምደዋለች፡፡›› ምሳ 5፡22 በአንድ ሕፃን ልጅ ወይም በአንድ ወጣት ላይ የሚፈፀም እጅግ ትልቅ ስህተት በመጥፎ ልማድ በሱሰኝነት እስኪታሰር ዝም ብሎ መልቀቅ ነው፡፡EDA 327.3

    ወጣቶች አብሯቸው የሚወለድ ነፃ የመሆን ፍቅር በውስጣቸው አለ፡፡ ነፃነትን ይፈልጋሉ፡፡ እናም ከነዚህ ለግምት በሚያስቸግሩ በረከቶች ለመደሰት የሚቻለው የእግዚአብሔርን ሕግ ስንታዘዝ ብቻ መሆኑን ማስተዋል ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ ሕግ የእውነተኛ አርነትና ነፃነት ዐቃቢ ነው፡፡ የሚያዋርደውንና ባሪያ የሚያደርገውን ነገር ያመለክታል፡፡ ከእሱም ይከላከላል፡፡ እናም ታዛዥ ለሆነው ሰው ከክፉው ኃይል ይጠብቀዋል ይከላከልለታል፡፡EDA 328.1

    ባለመዝሙሩ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ትዕዛዝክን ፈልጌአለሁና አስፍቼ እሄዳለሁ፡፡›› ‹‹ምስክርህም ተድላየ ነው ሥርዓትህም መካሬ ነው፡፡›› መዝ 119፡ 24፣45EDA 328.2

    ክፉውን ለማስተካከል በምናደርገው ጥረት ስህተት ወይም ግድፈት ፈላጊ የመሆንን አዝማሚያ መከላከል አለብን፡፡ ዘወትር ጥፋትን ብቻ መከታተል የበለጠ ያሳስታል እንጅ አያቀናም፡፡ ብዙ ጊዜ እጅግ ድንቅ ሐሳብ ያላቸው በቀላሉ ስሜታዊ የሚሆኑ ሰዎች ጥረታቸው ሁሉ ርህራሄ በሌለው ትችት ላይ የመውደቅ ዕድል ያጋጥመዋል፡፡ አበቦች ለኃይለኛ አውሎ ነፋስ መጋለጥ አይችሉምና፡፡EDA 328.3

    በአንድ ዓይነት የተለየ ስህተት ላይ ብቻ ሁልጊዜ የእርምት እርምጃ የሚወሰድበት ልጅ ያችን ጥፋቱን እንደ ልዩ ባህሪይው ወይም ለማረም ጥረት ማድረግ ከንቱ ልፋት እንደሆነ በማስመሰል እንደሙያ አድርጎ ያስበዋል፡፡ በዚህም በገለልተኝነት ወይም በኃይለኝነት ሥር ዘወትር በመጨቆን ላይ ተስፋ መቁረጥና ተስፋ የለሽ መሆን ይፈጥርበታል፡፡EDA 328.4

    እውነተኛ የተግሳጽ ዓላማ የሚገኘው ስህተት ፈፃሚው ራሱ ጥፋቱን እንዲያይ ሲደረግና ፍላጎቱም ለእርምት ዝግጁ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ይኸንን ሲፈጽም የይቅርታና የኃይል ምንጭ ወደሆነው አመልክቱት፡፡ እርሱም የሚሰጠውን ራስ ማክበርን እንዲጠብቅና በድፍረት በተስፋ ይሞላ ዘንድ እሹ፡፡EDA 329.1

    ይህ ሥራ ለሰው ከተሰጠው ግዳጅ ከሁሉም የበለጠ የሚያምር እጅግ ከባድም ነው፡፡ እጅግ ድንቅ የሆነ የዋህነት ስለሰው ተፈጥሮ ባለው እውቀት ከሰማይ የመጣውን እውቀትና ትዕግሥት፤ ለማስተዋልና ለመጠበቅ እጅግ ውስብስብ የሆነ ዘዴ ይጠይቃል፡፡ ወደር የማይገኝለት አስፈላጊ ነገር ነው፡፡EDA 329.2

    ሌሎችን የመቆጣጠር ፍላጎት ያላቸው ሁሉ መጀመሪያ ራሳቸውን መቆጣጠር አለባቸው፡፡ አንድን ልጅ ወይም አንድን ወጣት በስሜት መቅረብ የልጁን ንዴት የሚቀሰቅስ ይሆናል፡፡ አንድ ወላጅ ወይም መምህር ትዕግሥቱ አልቆ ጥበብ የጎደለውን ንግግር ለመናገር በሚገደድበት ሰዓት ፀጥ ብሎ በዝምታ ያሳልፈው፡፡ በዝምታ ውስጥ አስገራሚ ታላቅ ኃይል አለ፡፡EDA 329.3

    መምህር የተጣመሙ ባሕሪያትና የተበላሹ ልቦች እንደሚያጋጥሙት መጠበቅ አለበት፡፡ ነገር ግን ከእነሱ ጋር በሚኖረው ግንኙነት የሥነ-ሥርዓት ርምጃ ሲያስፈልገው እርሱ ራሱ ልጅ እንደነበረ በፍፁም መርሳት የለበትም፡፡ ከዕድሜ፤ ከትምህርትና ከልምድ ካለው ከማንም የተሻለ እድል አንፃር እንኳ ሁልጊዜም ስህተት ያጋጥመዋል፡፡ እናም ምህረትና ታጋሽነት በእጅጉ ያስፈልገዋል፡፡ ወጣቶችን በሚያሰለጥንበት ጊዜ እርሱ ራሱ እንዳለው ሁሉ እነርሱም ወደክፉው የማዘንበል ስሜት ካላቸው ሰብዓዊ ፍጡራን ጋር መሆኑን ማሰብ አለበት፡፡ ሁሉን ነገር ገና መማር ያለባቸው ናቸው፡፡ እንደዚህም ሆኖ አንዳንዶቹ ከሌሎች በተለየ የመማር ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ ደደብ ተማሪ በሚያጋጥመው ወቅት በትዕግሥት መያዝ አለበት፡፡ የሚኖርበትን ማንኛውንም እድል ማሻሻል አለበት እንጂ፡፡ ስሜታዊና እጅግ ግልፍተኞች ከሆኑት ተማሪዎች ጋር የሚኖረው ግንኙነት በገርነት የተሞላ መሆን አለበት፡፡ የራሱ ፍፁም አለመሆን ከብዙ ችግሮች ጋር ለሚታገሉት አያያዙ ርህራሄንና ትዕግሥትን ያለማቋረጥ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡EDA 329.4

    የመድኅናችን ‹‹ሌሎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንት ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፡፡›› (ሉቃ 6፡31) የሚለው ሕግ ልጆቹንና ወጣቶችን የማሰልጠን ተግባር ላለባቸው ሁሉ ሕግ ሊሆንላቸው ይገባል፡፡ የጌታ ቤተሰብ ወጣት አባላት ናቸው፡፡ ከእኛ ጋር የሕይወት ፀጋ ወራሾች፡፡ በማይሙ፤ በወጣቱ፤ በጥፋተኛና በእምቢተኛው ዘንድ እንኳ በቅድስና መጠበቅ አለበት፡፡EDA 330.1

    ይህ ሕግ መምህሩን በተቻለው መጠን የተማሪውን ጥፋትና ስህተት ያለአግባብ ገሃድ ለማውጣት እንዳይቸኩል ይረዳዋል፡፡ ለጥፋተኛው ተማሪ በሌሎች ጓደኞቹ ፊት ተግሳጽ ወይም ቅጣት ከመስጠት ይቆጠባል፡፡ ጥፋተኛው ልጅ አሻሽሎ እንዲመለስ የተቻለውን ያክል ሁሉ ሳይሞክር ለማባረር አይፈልግም፡፡ ነገር ግን ልጁ በጥፋቱ እየቀጠለ ከሄደና ተማሪው በመቆየቱ እንደማይጠቀም ሲረጋገጥ የትምህርት ቤቱን መተዳደሪያ ሕግ የሚጋፋ መሆኑ ሲታወቅ የርሱ ፀባይ ሌሎቹንም የሚበክል ከሆነ መባረሩ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ይሁንና በሕዝብ ፊት የመባረሩ ሐፍረትም ብልሹና የጥፋት ነክ ነገር እንዲናገር ሊያደርገው ይችላል፡፡ ብዙ ጊዜ ከማባረር በስተቀር ሌላ ምርጫ የሌለው ሲሆን ጉዳዩ ገሃድ ባይወጣ መልካም ነው፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር በመመካከርና በመወያየት መምህሩ የመልቀቂያ መረጃዎችን ያሰባስብለት፡፡EDA 330.2

    ለወጣቱ በጣም አደገኛ በሆነበት በዚህ ልዩ ጊዜው ውስጥ፤ ዙሪያው በፈተና የተከበበ ጊዜ፤ ራስን ለመቆጣጠር በማይችልበት የመዋዥቅ ጊዜ፤ ሞገዱን ለመቋቋም እጅግ ከባድ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል፡፡ እያንዳንዱ ትምህርት ቤት በዚህ ዓይነት የሕይወት ፈተና ላይ ለወደቀ ወጣት ውድቀቱ ከትዕግሥትና በጥበብ የሚስተናገድበት ‹‹የጥገኞች ከተማ›› መሆን አለበት፡፡ ኃላፊነታቸውን የሚያስተውሉ መምህራን እንደዚህ ፈቃደኝነት የጎደለው እምቢተኛውን ወጣት በሚገባ ለመርዳት የሚከለክላቸውን ማንኛውንም ነገር ከልባቸውና ከራሳቸው ሕይወት ውስጥ አውጥተው ይጥላሉ፡፡ ፍቅርና ገርነት ትዕግሥትና ራስን መቆጣጠር ሁልጊዜም የንግግራቸው ሕግ ይሆናል፡፡ ምህረትና ርህራሄ ከፍርድ ጋር ይዋሃዳሉ፡፡ ተግሳጽ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሚጠቀሙባቸው ቃላት ትህትና የተሞላባቸው እንጅ በጣም የተጋነኑ መሆን የለባቸውም፡፡ ለጥፋተኛው ልጅ ስህተቱን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ቁልጭ እርገው ያስቀምጡለት፡፡ ራሱን እንዲያሻሽልም ይረዱታል፡፡ እያንዳንዱ እውነተኛ መምህር ስህተት ቢሠራ እንኳ በጭካኔ ሣይሆን ምህረት በማድረግ በኩል ቢሳሳት እንደሚሻል ይሰማዋል፡፡EDA 331.1

    ሊታረሙ የማይችሉ ብዙ ወጣቶች ከላይ መስለው የሚታዩትን ያክል ከልባቸው እንደዚያ አይደሉም፡፡ ብዙ ተስፋ የላቸውም ተብለው የነበሩ ልጆች ጥበብ በተሞላበት ሥነ-ሥርዓት ተመልሰዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እንደ እነዚህ ዓይነቶቹ በትህትና ሲቀርቧቸው ወከክ የሚሉ ናቸው፡፡ መምህሩ በሕይወት ፈተና ላይ የወደቀው ወጣት በርሱ ላይ ሙሉ እምነት የሚጥልበት ዓይነት መሆን አለበት፡፡ እናም መልካሙን ነገር ሁሉ በመገንዘብና በባህሪያው ውስጥ እንዲያድግበት በማድረግ በብዙ ሁኔታዎች ላይ ክፉውን ማረምና እሱም ራሱ ወደ ክፉው ሳያዘነብል ማስተካከል ይችላል፡፡EDA 331.2

    መለኮታዊው መምህር ስህተት የሚፈጽሙትን ሁሉ ይታገሳቸዋል፡፡ የርሱ ፍቅር አያረጅም፡፡ እነሱን ወደራሱ ለመመለስ ጥረቱ አያቋርጥም፡፡ እምቢተኛ ወይም ጥፋተኛና ከሃዲ ኃጢአተኛ እንኳ ቢሆንም ወደ እርሱ እስከሚመለስ ድረስ በተደደጋጋሚ አሁንም እጆቹን ዘርግቶ ይጠብቃል፡፡ በጭካኔአዊ አያያዝ ሥር ለወደቀ ረዳት ለሌለው ልጅ አሁንም ልቡዋ ያዝናል፡፡ የሰው ልጅ የስቃይ ጩኸት እሱ ጆሮ ዘንድ ከደረሰ በከንቱ አይቀርም፡፡ በርሱ አመለካከት ሁሉም ክቡር ቢሆኑም ለክፉውና ለጨካኙ ምላሰኛ የበለጠ ርህራሄና ፍቅር ያሳያል፡፡ ምክንያቱም ከመነሻው እስከ ውጤቱ ያለውን ይከታተላልና፡፡ በቀላሉ ወደፈተና የሚገባና በቀላሉ ስህተት ውስጥ ለሚወድቅም የርሱ ልባዊ የሆነ ልዩ ዓላማው ነው፡፡EDA 332.1

    እያንዳንዱ ወላጅና መምህር የሕሊና ጉዳት ለደረሰባቸው ለሚሰቃዩና ለሚፈተኑ ጉዳታቸውን እንደራሱ አድርጎ የሚያስብ መሆን አለበት፡፡ ‹‹… እርሱ ራሱ ፈግሞ ድካምን ስለሚለብስ ላልተማሩትና ለሚስቱት ሊራራላቸው ይችላል፡፡›› ዕብ 5፡2 የሱስ ለእኛ ከሚገባን በላይ ያደርግልናል፡፡ እኛም ሌሎችን እርሱ እንዳደረገልን አድርገን ልንይዛቸው ይገባናል፡፡ መድኅናችን ለተመሳሳይ ሁኔታ ከሚያሳየውና ከሚያደርገው በተለየ መንገድ የሚፈጽም ማንኛውም ወላጅ ወይም መምህር አድራጎቱ ትክክል አይደለም፡፡EDA 332.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents