Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 25—ፍቅርና ወሲብ በሰብአዊ ልምምድ ውስጥ

    ማስታወሻ፡-ኤለን ኋይት የኖረችውና የሰራችው ዘመን ስለ ወሲብና በባሎችና በሚስቶች መካከል ስላለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሕዝብ ፊት ለመናገርም ሆነ ለመጻፍ ከፍተኛ እቀባ (ገደብ) የሚደረግበት ዘመን ነበር።{1MCP 218.1}1MCPAmh 177.1

    እየወሰደች የነበረው እርምጃ ትክክል መሆኑን በጸሎት አማካይነት ካረጋገጠች በኋላ ነሃሴ 30 ቀን 1846 ዓ.ም ጄምስ ኋይትን አገባች። ለሃያ ወራት ከእግዚአብሔር ራዕይ ስትቀበል ስለነበረች በአገልግሎቷ ደህና እንደነበረች ልብ ማለት ያስፈልጋል። ከጄምስ ኋይት ጋር ከነበራት የጋብቻ ጥምረት አራት ልጆችን የወለደች ሲሆን ልጆቹ የተወለዱት በ1847፣ 1849፣ 1854 እና 1860 ዓ.ም ነበር። {1MCP 218.2}1MCPAmh 177.2

    ኤለን ጂ ኋይት ከወሲብ ጋር ግንኙነት ስላላቸው ነገሮች ውይይት ማድረግ የጀመረችው በ1860ዎቹ ውስጥ፣ ሁለት መሰረታዊ የሆኑ የጤና ተሃድሶ ራዕዮችን በተቀበለችበት አስር አመታት (ሰኔ 6፣ 1863 እና ታህሳስ 25፣ 1865 ዓ.ም.) ውስጥ ነበር። በኋለኞቹ ዓመታት የተሰጡ መግለጫዎች አንዳንድ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል። በጋብቻ ውስጥ የሚደረገውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት ስትጠቅስ ‹‹የጋብቻ ግንኙነት ልዩ ጥቅም፣›› ‹‹የቤተሰብ ግንኙነት ልዩ ጥቅም፣ ›› ‹‹የግብረ ሥጋ ግንኙነት ልዩ ጥቅሞች፣›› የሚሉ ስያሜዎችን ተጠቅማለች። {1MCP 218.3}1MCPAmh 177.3

    በዚህ አስደሳች የትምህርት ዘርፍ ትክክለኛና ሚዛናዊ የሆነ የኤለን ኋይትን አስተሳሰብ ለማግኘት መግለጫ ከመግለጫ ጋር መቀመጥ አለበት። በአብዛኞቹ መግለጫዎች ውስጥ የተገለጠው ሚዛናዊነት መጠበቅ አለበት። በጥቅም ላይ የዋሉ ቃላትን ትርጉም በተመለከተ ጥንቃቄ የተሞላበት ማስታወሻ መወሰድ አለበት። {1MCP 218.4}1MCPAmh 177.4

    አንዳንድ ጊዜ ‹‹የፍቅር ስሜት›› እና ‹‹የተፈጥሮ ዝንባሌ›› የሚሉ ስያሜዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። እነዚህን ስያሜዎች ለማጉላት ተራና ርካሽ፣ የእንስሳ፣ ፍትወተኛ፣ ሕገ-ወጥ (ነውረኛ)፣ ሥነ-ምግባር የጎደለው የሚሉ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል። ይህ ጠንካራ ቋንቋ አንዳንድ አንባቢዎችን ሁሉም የፍቅር ስሜት የተወገዘ እንደሆነ እና ሁሉም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ክፉ እንደሆነ አድርገው እንዲገምቱ ሊመራቸው ይችላል። የሚከተሉት ጥቅሶች ይህን ሀሳብ አይደግፉም፡- {1MCP 218.5}1MCPAmh 177.5

    እግዚአብሔር የሚፈልገው ሀሳባችሁን ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ስሜቶቻችሁንና ፍቅራችሁንም ጭምር ነው…። ስሜትና ፍቅር ኃይለኛ ወኪሎች ናቸው…። ሀሳቦቻችሁን፣ ስሜቶቻችሁንና ፍቅራችሁን አዎንታዊ በሆነ ሁኔታ ጠብቁ። ፍትወትን ለማገልገል እነዚህን ነገሮች ዝቅ አታድርጉ። ልታነጹአቸውና ለእግዚአብሔር ቀድሳችሁ ልትሰጡአቸው [ስሜቶቻችሁንና ፍቅራችሁን] ከፍ አድርጉአቸው። --2T 561, 564 (1870). {1MCP 218.6}1MCPAmh 177.6

    ሁሉም የተፈጥሮ የእንስሳ ፍላጎቶች ከፍ ላሉ የነፍስ ኃይሎች መገዛት አለባቸው።--Ms 1, 1888. (AH 128.) {1MCP 219.1}1MCPAmh 178.1

    ከላይ የተጠቀሱት አንዳንድ ጠንካራ ስያሜዎች ጥቅም ላይ ከዋሉበት አውድ ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ የፍቅር ስሜቶች እሷ ‹‹ከፍ ያሉ፣ የከበሩ ኃይሎች፣›› ‹‹የማሰብ ችሎታ፣›› ‹‹የግብረገብ እገዳ፣›› እና ‹‹የግብረ-ገብ ኃይሎች›› ብላ በምትጠራቸው ነገሮች ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ታደፋፍራለች። መሻትን ስለ መግዛት፣ በልክ ስለመኖርና ከመጠን ያለፈ ነገርን ከማድረግ ስለመራቅ ትጽፋለች። በጋብቻ ውስጥ እነዚህ በሁሉም ሰብአዊ ፍጡር ውስጥ ያሉ የተለመዱ የፍቅር ስሜቶች በቁጥጥር ሥር መሆን አለባቸው፣ መገዛት አለባቸው። በድጋሚ የሚከተለውን ልብ ይበሉ፡- {1MCP 219.2}1MCPAmh 178.2

    የጋብቻ ግንኙነት እግዚአብሔር ከሰጣቸው ቅዱስ ሥርዓቶች መካከል አንዱ እንደሆነ አድርገው የሚመለከቱ ሰዎች፣ በእርሱ ቅዱስ ቃል ተጠብቀው፣ የማሰብ ችሎታ በሚሰጠው ትዕዛዝ ቁጥጥር ሥር ይሆናሉ። --HL, No. 2, p. 48. {1MCP 219.3}1MCPAmh 178.3

    የፍቅር ስሜቶቻቸውን መቆጣጠር ኃይማኖታዊ ተግባራቸው እንደሆነ የሚሰማቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው…። የጋብቻ ቃል ኪዳን እጅግ የጠቆረውን ኃጢአት ይሸፍናል…። ተራ በሆነ የፍቅር ስሜት መሰዊያ ላይ ጤንነትና ሕይወት መስዋዕት እየተደረጉ ናቸው። ከፍ ያሉና የከበሩ ኃይሎች ለእንስሳዊ የተፈጥሮ ዝንባሌዎች ተገዥ እየሆኑ ናቸው…። ፍቅር ንጹህና ቅዱስ መርህ ነው፤ ነገር ግን ፍትወተኛ የሆነ የፍቅር ስሜት ገደብን ስለማይቀበል የማሰብ ችሎታ አያዘውም ወይም አይቆጣጠረውም።--2T 472, 473 (1870). {1MCP 219.4}1MCPAmh 178.4

    የጋብቻ ግንኙነት ‹‹ሊጣመም›› የሚችል ‹‹የተቀደሰ ተቋም›› እንደሆነ ጽፋለች። ‹‹ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ስለ ዋሉ›› ‹‹የግብረ ሥጋ ልዩ መብቶች›› ተናግራለች። እየተወገዘ ያለው የፍቅር ስሜት ሳይሆን ‹‹ተራ የሆነ›› እና ‹‹ፍትወተኛ›› የሆነ የፍቅር ስሜት ነው። ኤለን ኋይት በጋብቻ ውስጥ ያለውን ቅርርብ እንደ ‹‹ልዩ መብት/ጥቅም›› አድርጋ ማሳየቷን መመልከት ተገቢ ነው። ምንም እንኳን በጋብቻ ውስጥ ስለሚታይ ያልታረመ የወሲብ ባሕርይ ብታስጠነቅቅም ተገቢው ቁጥጥር የተደረገባቸው የፍቅር ስሜቶች ‹‹ነፃ›› ሊሆኑ ስለሚችሉበት ጊዜ ጽፋለች። ሌላ በቅርበት መመርመርን የሚፈልግና ጥሩ ማብራሪያ የሚሰጥ መግለጫን ልብ ይበሉ ።{1MCP 219.5}1MCPAmh 178.5

    ጋብቻን በተመለከተ የእግዚአብሔርን ቃል አንብቡ እላለሁ። የዚህ ዓለም ታሪክ የመጨረሻዎቹ ቀናት በሆኑበት በዚህ ጊዜ እንኳን በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች መካከል ጋብቻዎች ይፈጸማሉ…። ጋብቻው ሁለቱንም ተጋቢዎች ለችግር የሚያጋልጥ ስለመሆኑ ግልጽ የሆኑ ምክንያቶች ከሌሉን በስተቀር እኛ እንደ ሕዝብ ጋብቻን በፍጹም ከልክለን አናውቅም። በእንደዚህ ዓይነት ጊዜም ቢሆን እኛ ያደረግነው ምክርና አስተያየት መስጠት ብቻ ነው። --Lt 60, 1900. {1MCP 219.6}1MCPAmh 179.1

    እሷና ባለቤቷ ተሰማርተውበት ከነበረው ሥራ ጥያቄ የተነሣ ግማሽ አህጉር በለያቸው ጊዜ ለጄምስ በደብዳቤ እንዲህ በማለት ምስጢር ነገረችው፡- {1MCP 219.7}1MCPAmh 179.2

    በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ጋር የበለጠ ቅዱስ ቅርበት የመፍጠር ልባዊ ፍላጎት ይሰማናል። ስተኛም፣ በሌሊት ስነቃም፣ በማለዳ ከመኝታዬ ስነሳም፣ አምላኬ ወደ አንተ እቀርባለሁ፣ ወደ አንተ እቀርባለሁ የሚለው ጸሎቴ ነው።… {1MCP 219.8}1MCPAmh 179.3

    የምተኛው ብቻዬን ነው። ይህ የማርያምና የእኔም ምርጫ ይመስላል። ለማሰላሰልና ለጸሎት የተሻለ ዕድል ይኖረኛል። አንተ ከሌለህ በቀር መላው አካሌን ለራሴ አደርገዋለሁ። አልጋዬን መጋራት የምፈልገው ከአንተ ጋር ብቻ ነው። --Lt 6, 1876. {1MCP 220.1}1MCPAmh 179.4

    እሷ አንድም ጊዜ ቢሆን በጋብቻ ውስጥ ጥልቅ የሆነ የወንድምና የእህት ዓይነት ግንኙነት እንዲኖር ጥሪ በሚያደርጉ አስተምህሮች ላይ ተሳትፋ ወይም የዚህን ዓይነት ትምህርት ፈቅዳ አታውቅም። ኤለን ኋይት የዚህ ዓይነት ባሕርይ ያላቸውን ትምህርቶች ሰዎች እንዲቀበሉ ከሚገፋፉት ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ስትነጋገር ከዚህ ዓይነት አመለካከቶች እንዲርቁ መክራለች። ስለ እነርሱ ብዙ ማሰብ በሀሳብ ውስጥ ከንጽህና ይልቅ እርኩሰት እንዲከሰት ሰይጣን እንዲሰራ መንገድ ከፍቷል በማለት ጽፋለች።--LT 103, 1894. {1MCP 220.2}1MCPAmh 179.5

    ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር ለሰጠው ሕጋዊ የሆነ ልዩ መብት ሰይጣን ያንኑ የሚመስል የውሸት ሀሳብ አለው። ቅዱስና ንጹህ ሀሳቦችን በረከሱ ሀሳቦች ለመተካት ያስባል። በጋብቻ ውስጥ ባለው የፍቅር ቅድስና ቦታ ከመጠን ያለፈ ነጻነትን፣ ታማኝ አለመሆንን፣ ከልክ ማለፍን፣ ጤናማ ያልሆነ የወሲብ ፍላጎትን፤ ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን፣ ዝሙትን፣ በጋብቻ ውስጥም ሆነ ከጋብቻ ውጭ እንስሳዊነትን እና ግብረ ሶዶምን ይተካል። እነዚህ ሁሉ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ተጠቅሰዋል።--አሰባሳቢዎች። {1MCP 220.3}1MCPAmh 179.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents