Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First

  ምዕራፍ 34—ህሊና

  ህሊና ተገቢ የሆነ ሥልጣኑን የሚያሳየውን ቦታ እስኪይዝ ድረስ ከፍ ከፍ አድርጉት።--እግዚአብሔር ለሰዎች ከተራ የእንስሳት ሕይወት የበለጠ ነገር ሰጥቶአል። እርሱ ‹‹በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲሆንለት እንጂ እንዳይጠፋ አንድያ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል።›› ይህን ያህል ታላቅ መስዋዕትነት የከፈለላቸው ሰዎች ክርስቶስ ያስቀመጠላቸውን ምሳሌ በመከተል፣ ከእርሱ ፈቃድ ጋር የተጣጣመ ሕይወትን በመኖር አድናቆታቸውን እንዲያሳዩ ይጠብቅባቸዋል። ለሌሎች መልካም እንዲሆን ራሳቸውን በመካድ እርሱ ለገለጸላቸው ፍቅር ምላሽ እንዲሰጡ ይጠብቅባቸዋል። በአገልግሎቱ ውስጥ የአእምሮና የአካል ኃይሎችን እንዲጠቀሙ ይጠብቅባቸዋል። የማፍቀር ስሜትን ስለሰጣቸው ይህን ውድ ስጦታ ለእርሱ ክብር እንዲጠቀሙ ይጠብቅባቸዋል። ህሊና ስለሰጣቸው ይህ ስጦታ በማንኛውም መንገድ ቢሆን ያለ አግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል ይከለክላል፤ ከዚህ ይልቅ እርሱ እስካስቀመጠለት የሥልጣን ቦታ እስኪደርስ ድረስ ከፍ ከፍ እንዲል ይፈልጋል። --SW, Mar 1, 1904. {1MCP 319.1}1MCPAmh 261.2

  ህሊናችሁን ተቆጣጥራችሁ ተወዳጅ የሆነ ባሕርይን አሳድጉ።--ሁላችንም ተወዳጅ የሆነ ጠባይን ማሳደግና ራሳችንን በህሊና ቁጥጥር ሥር ማድረግ አለብን። የእውነት መንፈስ እርሱን በልባቸው ውስጥ የሚቀበሉትን ሰዎች የተሻሉ ወንዶችና ሴቶች ያደርጋቸዋል። መላው ፍጡር ከመርሆዎቹ ጋር ወደ መስማማት እስኪደርስ ድረስ እንደ እርሾ ይሰራል። በንፉግነት የቀዘቀዘውን ልብ ይከፍታል፤ ለሰብአዊ ስቃይ ታጥፎ የቆየ እጅን እንዲዘረጋ ያደርጋል፤ በጎ ማድረግና ደግነት እንደ እርሱ ፍሬዎች ሆነው ይታያሉ። --4T 59 (1876). {1MCP 319.2}1MCPAmh 261.3

  ንጹህ ህሊናን ማግኘት አስደናቂ ግኝት ነው።--እግዚአብሔርንና ሰውን ከመበደል የጸዳ ህሊናን ማግኘት አስደናቂ ግኝት ነው። --MS 126, 1897. (HC 143.) {1MCP 320.1}1MCPAmh 262.1

  ህሊናን አለመቀበል አስፈሪ የሆነ አደጋ ነው።--ከቀን ወደ ቀን ሰዎች ዘላለማዊ መዳረሻቸውን እየወሰኑ ናቸው። ብዙዎች ትልቅ በሆነ አደጋ ውስጥ እንዳሉ እንዳይ ተደርጌያለሁ። ሰው ፍላጎቱን ለማሟላት ሲል ማንኛውንም ነገር ሲያደርግ ወይም ሲናገር ከእግዚአብሔር ኃይል በስተቀር ምንም ነገር ሊያድነው አይችልም። እግዚአብሔርንና ሰውን ከመበደል የጸዳ መልካም ህሊናን ከማግኘቱ በፊት ባሕርዩ መለወጥ አለበት። ራስ ሞቶ ክርስቶስ የነፍስን መቅደስ መቆጣጠር አለበት። ሰዎች እግዚአብሔር የሰጠውን ብርሐን ባለመቀበል ህሊናን ያለ አግባብ ሲጠቀሙና ሲረግጡ አስፈሪ በሆነ አደጋ ውስጥ ናቸው። የወደፊቱ ዘላለማዊ ደህንነት አደጋ ውስጥ ገብቶአል። --Lt 162, 1903. {1MCP 320.2}1MCPAmh 262.2

  ሰይጣን ህሊናን ለማስመጥ ይሞክራል።--ሰይጣን የእግዚአብሔርን ድምጽና የህሊናን ድምጽ ለማስመጥ ተጽእኖውን ስለሚጠቀም ዓለም የሚያደርገውን ነገር የሚያደርገው በእርሱ ቁጥጥር ሥር እንዳለ ሆኖ ነው። ሰዎች እርሱን መሪያቸው አድርገው መርጠውታል። በእርሱ ባንዲራ ሥር ቆመዋል። ሕይወት እንዲሆንላቸው ወደ ክርስቶስ አይመጡም። ለደስታና ለፈንጠዝያ በተዘጋጁ ዘዴዎች ፍቅር በመነደፍ ሲጠቀሙት የሚጠፋውን ነገር ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ናቸው። --MS 161, 1897. {1MCP 320.3}1MCPAmh 262.3

  አንድ የተሳሳተ እርምጃ ሕይወትን ይቀይራል።--አንድን የአደጋ መከላከያ ከህሊና ማስወገድ፣ እግዚአብሔር ከሌሎች የተለየ ስለመሆኑ ምልክት ያደረገበትን ነገር ማድረግ አለመቻል፣ በስህተት መርህ መንገድ ላይ አንድ እርምጃ መሄድ፣ ብዙ ጊዜ ወደ አጠቃላይ የሕይወትና የድርጊት ለውጥ ይመራል።…ከአደጋ ልንጠበቅ የምንችለው ክርስቶስ በሚመራው መንገድ ላይ ስንጓዝ ብቻ ነው። መንገዱ እስከ ሙሉ ቀን ድረስ እየጠራ፣ ብሩህነቱ እየጨመረ ይሄዳል። --Lt 71 1898. {1MCP 320.4}1MCPAmh 262.4

  የተጣሰ ህሊና የደከመ ነው።--አንዴ የተጣሰ ህሊና በከፍተኛ ደረጃ ይደክማል። ያለ ማቋረጥ ነቅቶ የመጠበቅንና ሳይታክቱ የመጸለይን ብርታት ይሻል። 2T 90, 91 (1868). {1MCP 321.1}1MCPAmh 262.5

  የተጣሰ ህሊና የማይታመን ይሆናል።--እውነትን ከሰማ በኋላ ይህን እውነት መቀበል በንግድ መስመሮች ያለውን ስኬት ዘገምተኛ ስለሚያደርግበት ከዚያ እውነት ፊቱን የሚመልስ ሰው ከእግዚአብሔርና ከብርሃን ፊቱን እያዞረ ነው። ነፍሱን በርካሽ ገበያ ላይ እየሸጠ ነው። ህሊናው ለዘላለም የማይታመን ይሆናል። ንጹህና ትክክለኛ ሆኖ ቢጠበቅ ኖሮ ከመላው ዓለም ይልቅ የበለጠ ዋጋ የሚኖረውን ህሊናውን ባለመታዘዝ ከሰይጣን ጋር እየተደራደረ ነው። ብርሃንን አልቀበል የሚል ሰው አዳምና ሄዋን በኤደን እንዳደረጉት ካለመታዘዝ ፍሬ ይጋራሉ። --MS 27, 1900. {1MCP 321.2}1MCPAmh 262.6

  ማስተዋል ያለበትን ታማኝነት ማጣት ጉልበትን ሽባ ያደርጋል።--ማስተዋል ያለበትን ታማኝነትህን ስታጣ ነፍስህ የሰይጣን ጦር ሜዳ ትሆናለች፤ ጉልበትህን ሽባ ሊያደርጉ የሚችሉ ጥርጣሬዎችና ፍርሃቶች ስላሉህ ወደ ተስፋ መቁረጥ ይገፉሃል። አንዳንዶቻችሁ የእግዚአብሔር ድጋፍ በተለያችሁ ጊዜ በዓለማዊ ፍንደቃና ከዓለማውያን ጋር በሚደረግ ሕብረት ውስጥ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆናችሁ መንፈስ ቅዱስ ስላልመሰከረላችሁ ቦታውን ለመተካትና ካሣ ለመሻት ሞክራችኋል። --Lt 14, 1885. {1MCP 321.3}1MCPAmh 263.1

  ያልታዘዙት ህሊና ጨካኝ ይሆናል።-- ሕሊና ካልታዘዙት በሌሎች ህሊናዎች ላይ ጨካኝ ይሆናል። --Lt 88, 1896. {1MCP 321.4}1MCPAmh 263.2

  ሰይጣን በአስካሪ መጠጥ የደነዘዘ ህሊናን ይቆጣጠራል።--ሰካራም የማገናዘብ ችሎታውን ለአንድ ሲኒ መርዝ ይሸጣል። ሰይጣን የማሰብ ችሎታውን፣ የፍቅር ስሜቱንና ህሊናውን ይቆጣጠራል። እንደዚህ ዓይነቱ ሰው የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እያፈረሰ ነው። ሻይን መጠጣት ይህንኑ የመሰለ ሥራ ለመስራት ይረዳል። ነገር ግን እነዚህን አውዳሚ ወኪሎች በምግብ ጠረጴዛዎቻቸው ላይ በማስቀመጠጥ መለኮታዊ ባህርያትን የሚያጠፉ ምንኛ ብዙ ናቸው። --MS 130, 1899. (Te 79, 80.) {1MCP 321.5}1MCPAmh 263.3

  አመጋገብ በህሊና ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል።--ያልታረመና አነቃቂ ምግብ ደምን ያፈላል፣ የነርቭ ሥርዓትን ይረብሻል፣ ብዙ ጊዜ የማሰብ ችሎታና ህሊና በፍትወት ስሜቶች እስኪሸነፉ ድረስ የግብረገብ እይታን ያደበዝዛል። --CTBH 134, 1890. (CD 243.) {1MCP 322.1}1MCPAmh 263.4

  ጤናና ህሊና።--ጤና ሊገመት የማይችል በረከት ሲሆን ብዙዎች ከሚገነዘቡት የበለጠ ከህሊናና ከኃይማኖት ጋር በቅርበት የተገናኘ ነው። ከአንድ ሰው ችሎታ ጋር የተገናኘ ብዙ ነገር አለው። እያንዳንዱ አገልጋይ የመንጋው ታማኝ ጠባቂ እንደመሆኑ ያሉትን ኃይሎች ሁሉ ከሁሉ የተሻለ አገልግሎት መስጠት በሚያስችለው ሁኔታ ማቆየት አለበት።--GW 175 (1893). (CH 566.) {1MCP 322.2}1MCPAmh 263.5

  ህሊና ጤናን ለመመለስ ፍቱን ወኪል ነው።--ሸክም ከብዶህ ደክሞህ ከሆነ በደረቀ ቅርንጫፍ ላይ ሆነው ጥቅልል እንደሚሉ ቅጠሎች መጠቅለል የለብህም። ደስተኛነትና የጠራ ህሊና ከመድሃኒት የተሻሉ ስለሆኑ ጤናችሁን በመመለስ ረገድ ውጤታማ የሆኑ ወኪሎች ናቸው።--HR, June, 1871. (ML 177.) {1MCP 322.3}1MCPAmh 263.6

  አእምሮ እያወቀ መሳሳት ይቻላል።--አንድ ሰው በአእምሮው ልክ ነው ብሎ የሚያምነውን ማንኛውንም ነገር መለማመድ ይችላል የሚል ሀሳብ በብዙዎች ዘንድ ይስተናገዳል። ነገር ግን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ቢኖር ሰውየው በደንብ የተማረ፣ ጥሩ ህሊና ያለው ነውን? ወይስ ያለ እውቀት አስቀድሞ ከተያዙ አመለካከቶች የተነሣ ሚዛናዊነት ያጣና የተጣመመ ነው? የሚለው ነው። ህሊና ‹‹እግዚአብሔር እንዲህ ይላል›› የሚለውን ቦታ መውሰድ የለበትም። ህሊናዎች ሁሉ የተጣጣሙና በተመሳሳይ ሁኔታ መገለጥ ያላቸው አይደሉም። አንዳንድ ህሊናዎች የሞቱ፣ በጋለ ብረት የተተኮሱ ናቸው። ሰዎች እያወቁ ሊሳሰቱ ወይም ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ። ጳውሎስ የናዝሬቱን ኢየሱስን የማያምን ስለነበር እግዚአብሔርን የሚያገለግል እየመሰለው ክርስቲያኖችን ከከተማ ወደ ከተማ እየዞረ ያድን ነበር። --Lt 4, 1889. {1MCP 322.4}1MCPAmh 264.1

  ሰብአዊ አመለካከቶች ቋሚ መመሪያዎች አይደሉም።--‹‹የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል። ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ ጨለማውስ እንዴት ይሆናል!›› (ማቴ. 6፡ 22)። {1MCP 322.5}1MCPAmh 264.2

  እነዚህ ቃላቶች የመጀመሪያና ሁለተኛ ፣ ቀጥተኛና ምሳሌያዊ ትርጉም አላቸው። ውጫዊ ነገሮችን የምንመለከትበትን አካላዊ ዓይንን በተመለከተ በእውነት የተሞሉ ናቸው። መልካምንና ክፉን የምንገምትበትን መንፈሳዊ ዓይን፣ ህሊናን በተመለከተም እውነት ናቸው። የነፍስ ዓይን የሆነው ህሊና በትክክል ጤናማ ከሆነ ነፍስ ትክክለኛ ትምህርት ማግኘት ይችላል። {1MCP 323.1}1MCPAmh 264.3

  ነገር ግን ህሊና በክርስቶስ ፀጋ ባልተሸነፈና ባልለሰለሰ ሰብአዊ አመለካከቶች የሚመራ ከሆነ አእምሮ ታማሚ ነው። ነገሮች በትክክለኛ ሁኔታቸው አይታዩም። አስተሳሰብ በዚያ አቅጣጫ ስለተቀረጸ የአእምሮ ዓይን ነገሮችን የሚመለከተው ስህተት በሆነና በተዛባ ብርሃን ነው። {1MCP 323.2}1MCPAmh 264.4

  ጥርት ያለ፣ ርኅራኄ ያለው እይታ ያስፈልግሃል። ህሊናህ ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፣ ደንድኖአልም፣ ነገር ግን ትክክለኛውን መንገድ ከተከተልክ ነገሮችን የምትመለከትበት ሁኔታ ይታደሳል።--Lt 45, 1904. {1MCP 323.3}1MCPAmh 264.5

  መቼ ህሊናን ማመን እንደምንችል።--አንድ ሰው ‹‹የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ባለመጠበቄ ህሊናዬ አይወቅሰኝም›› ይላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ መልካምና ክፉ ህሊናዎች እንዳሉ እናነባለን፤ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ባለመጠበቅህ ህሊናህ አለመውቀሱ በእርሱ እይታ ከኩነኔ ነጻ ስለመሆንህ ማረጋገጫ አይደለም። {1MCP 323.4}1MCPAmh 265.1

  ህሊናህን ወደ እግዚአብሔር ቃል ውሰድና ሕይወትህና ባህርይህ እግዚአብሔር እዚያ ከገለጠው የጽድቅ መስፈርት ጋር የሚስማማ መሆኑን ተመልከት። ከዚያ በኋላ እውቀት ያለበት እምነት እንዳለህና ህሊናህ ምን ዓይነት እንደሆነ መወሰን ትችላለህ። የሰው ህሊና በመለኮታዊ ፀጋ ተጽእኖ ሥር ካልሆነ በስተቀር ሊታመን አይችልም። ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል መካሪያቸው ስላላደረጉ ሰይጣን ያልተረዳ ህሊናን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሰዎችን ወደ ሁሉም ዓይነት ማታለያዎች ይመራቸዋል። ብዙዎች በእግዚአብሔር ሕግ ፈንታ የራሳቸውን ሕግ እንደተኩ ሁሉ የራሳቸውን ወንጌልም ፈልስፈዋል። --RH, Sept 3, 1901. {1MCP 323.5}1MCPAmh 265.2

  መስፈርቱ የእግዚአብሔር ቃል ነው።--ሰው የራሱን ህሊና ትዕዛዝ እስከተከተለ ድረስ ከአደጋ ነጻ ነው ብሎ ማሰብ በቂ አይደለም።…እልባት ማግኘት ያለበት ጥያቄ ህሊና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የተጣጣመ ነው ወይ? የሚለው ነው። እንዲህ ካልሆነ ስለሚያታልል ከአደጋ ነጻ በሆነ ሁኔታ መከተል አይቻልም። ህሊና በእግዚአብሔር መብራት አለበት። ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማጥናትና ለጸሎት ጊዜ መሰጠት አለበት። ያኔ አእምሮ ይመሰረታል፣ ይበረታል፣ ይረጋጋልም። --Lt 21, 1901. (HC 143.) {1MCP 324.1}1MCPAmh 265.3

  ህሊና ሕይወትህን እየለወጠ ነው ወይ? ህሊና ሊኖርህና ያ ህሊና ሊዘልፍህ (ጥፋተኛነትህን ሊያሳምን) ይችላል፣ ነገር ግን ጥያቄው ያ ዘለፋ የሚሰራ ወኪል ነው ወይ? ያ ዘለፋ ወደ ልብህ እና ወደ የውስጥ ሰው ሥራ የሚደርስ ነው ወይ? የነፍስን ቤተ መቅደስ ከእርኩሰት ማንጻት አለን? ጊዜው በእሥራኤል ልጆች ዘመን እንደነበረው ጊዜ ስለሆነ የምንፈልገው ያንን ነው፤ ምንም ዓይነት ኃጢአቶች ካሉብህ እስኪታረሙና እስኪወገዱ ድረስ ቁመህ አትጠብቅ። --MS 13, 1894. {1MCP 324.2}1MCPAmh 265.4

  እውነት በህሊናና በልብ ላይ ያለው ተጽእኖ።--ዘማሪው እንዲህ ይላል፣ ‹‹የቃልህ ፍቺ ያበራል፤ ሕጻናትንም አስተዋዮች ያደርጋል (መዝ. 119፡ 130)። እውነት በህሊና ላይ ብቻ ሲሰራ በጣም ምቾት ይነሳል፤ ነገር ግን እውነት ወደ ልብ እንዲገባ ሲደረግ መላው አካል ለኢየሱስ ክርስቶስ ምርኮኛ ይሆናል። የክርስቶስ አእምሮ የሚሰራው ፈቃድ ለእግዚአብሔር ፈቃድ አልፎ ሲሰጥ ስለሆነ ሀሳቦች እንኳን ይያዛሉ። ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን›› (ፊልጵስዩስ 2፡ 5)። ጌታ ነጻ ያደረገው እርሱ በርግጥ ነጻ ስለሆነ የኃጢአት አገልጋይ ባሪያ መሆን አይችልም። --MS 67, 1894. {1MCP 324.3}1MCPAmh 265.5

  በህሊና ብቻ የተያዘ እውነት አእምሮን ይቀሰቅሳል።--እያንዳንዱ ታማኝ አይሁድ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደነበረ በህሊናው እንዲያምን ተደርጓል፣ ነገር ግን ልብ ከኩራቱና አንድን ነገር ለማድረግ ካለው ፍላጎት የተነሣ አይሸነፍም። ለመቋቋምና ላለመቀበል የወሰኑትን የእውነት ብርሃን መቃወማቸውን ይቀጥላሉ። እውነት እንደ እውነት በሕሊና ብቻ ሲያዝ፣ ልብ ካልተቀሰቀሰና እንዲቀበል ካልተደረገ፣ እውነት አእምሮን ብቻ ይቀሰቅሳል። ነገር ግን እውነት እንደ እውነት በልብ ውስጥ ተቀባይነት ባገኘ ጊዜ በህሊና ውስጥ አልፎ በንጹህ መርሆዎቹ አማካይነት ነፍስን ይማርካል። የእርሱ የመለወጥ ኃይል በባህርይ ውስጥ መታየት እንዲችል ውበቱን በአእምሮ ውስጥ በሚቀርጽ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በልብ ውስጥ ይቀመጣል። --MS 130, 1897. {1MCP 324.4}1MCPAmh 266.1

  እግዚአብሔር ህሊናን አያስገድድም።--እግዚአብሔር ፈቃድን ወይም ህሊናን በፍጹም አያስገድድም፣ ነገር ግን የሰይጣን የማያቋርጥ አማራጭ--በሌላ መንገድ ሊያታልላቸው የማይችላቸውን መቆጣጠር እንዲችል--በጭካኔ ማስገደድ ነው። በፍርሃት ወይም በኃይል አማካይነት ህሊናን ለመግዛትና ለራሱ ተገዥ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል።--GC 591 (1888). {1MCP 325.1}1MCPAmh 266.2

  ህሊና እርግጠኛ መሪ ሲሆን።--ህሊናው እርግጠኛ መሪ የሆነ ሰው ከእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ሲበራበት ማሰብን አያቆምም። በሰብአዊ ምክር አይመራም። ዓለማዊ ንግድ በመታዘዝ መንገድ ላይ እንዲቆም አይፈቅድም። እያንዳንዱን የራስ ወዳድነት ፍላጎት በምርመራ በር ላይ በማስቀመጥ ዘላለማዊ ፍላጎቱ በሚዛን ላይ እንደተንጠለጠለ ሰው ወደ እግዚአብሔር ቃል ይቀርባል።--MS 27, 1900. {1MCP 325.2}1MCPAmh 266.3

  ስሜቶችና ፍላጎቶች ለማሰብ ችሎታና ለህሊና ሲገዙ።--ኃጢአትን መስራት ካልፈለግን የእርሱን ጅምር መሸሽ አለብን። እያንዳንዱ ስሜትና ፍላጎት ለማሰብ ችሎታና ለህሊና ተገዥ መሆን አለበት። እያንዳንዱን ቅዱስ ያልሆነ ሀሳብ ወዲያውኑ መቋቋም ያስፈልጋል። በእምነትና በሙሉ ልብ ጸልይ። ሰይጣን እግርህን ለማጥመድ ነቅቶ እየጠበቀህ ነው። ከእርሱ ወጥመዶች ለማምለጥ ከፈለግክ ከላይ እርዳታ ማግኘት አለብህ።-- 5T 177 (1882). {1MCP 325.3}1MCPAmh 266.4

  ነገር ግን እያንዳንዱን ስሜትና ፍላጎት ለማሰብ ችሎታና ለህሊና በእርጋታ በማስገዛት በቁጥጥርህ ሥር ማድረግ የአንተ ሀላፊነት ነው። ያኔ ሰይጣን አእምሮን የመቆጣጠር ኃይሉን ያጣል። --RH, June 14, 1892. (HC 87.) {1MCP 326.1}1MCPAmh 267.1

  ጠባሳዎች ለዘላለም ይኖራሉ።--ያ ታማኝ ያልሆነ ሰው በዓለማዊ ፖሊሲው ምን ትርፍ አገኘ? ለስኬቱ ምን ያህል ዋጋ ከፈለ? የከበረ ማንነቱን መስዋዕት በማድረግ የጠላት ሲሳይ ወደመሆን በሚወስድ መንገድ ላይ ጉዞ ጀምሮአል። ተለውጦ ሊሆን ይችላል፤ በመሰል ሰዎች ላይ የፈጸመውን የኢፍትሃዊነት ተግባር ክፋት ሊያይ እና በተቻለ መጠን ካሣ ሊከፍል ይችላል፤ ነገር ግን የቆሰለው ህሊና ቁስል ለዘላለም ይኖራል።--ST, Feb. 7, 1884. (3BC 1158.) {1MCP 326.2}1MCPAmh 267.2

  የበደለኝነት ስሜት ለሚሰማው ህሊና በቂ የሆነ የክርስቶስ ጸጋ።--ኃጢአት ልብን ለመቆጣጠር በሚታገልበት ጊዜ፣ የበደለኝነት ስሜት ነፍስን ሲጨቁንና ህሊናን ሲጫነው፣ አለማመን አእምሮን ሲያጨልም፣ ኃጢአትን ለማሸነፍና ጨለማን ለማጥፋት የክርስቶስ ጸጋ በቂ መሆኑን አስታውስ። ከአዳኝ ጋር ግንኙነት ስንፈጥር ወደ ሰላም ክልል እንገባለን። --MH 250 (1905). {1MCP 326.3}1MCPAmh 267.3

  ራስህን መሆን የምትፈልገውን እንድትሆን ማድረግ ትችላለህ።--የእያንዳንዱ ሰው ጉዳይ በሚወሰንበት በዚያ ቀን እነዚህን መስመሮች እንደሚገናኝ ሰው በድጋሚ አስጠነቅቅሃለሁ። ሳትዘገይ ራስህን ለክርስቶስ አሳልፈህ ስጥ፤ እርሱ ብቻ፣ በጸጋው ኃይል፣ ከጥፋት ሊያድንህ ይችላል። እርሱ ብቻ የግብረገብና የአእምሮ ኃይሎችህን ጤናማ ወደሆነ ሁኔታ ሊያመጣ ይችላል። ልብህ በእግዚአብሔር ፍቅር ሊሞቅ ይችላል ማስተዋልህም ጥርት ያለና የበሰለ ሊሆን ይችላል፤ ህሊናህ የበራ፣ የተነቃቃ እና ንጹህ ሊሆን ይችላል፤ ፈቃድህ የተስተካከለና የተቀደሰ፣ ለእግዚአብሔር መንፈስ ቁጥጥር የተገዛ ሊሆን ይችላል። ለመሆን የመረጥከውን መሆን ትችላለህ። አሁን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ፊትህን ብታዞር፣ ክፉ መስራትን ብትተውና መልካም ማድረግን ብትማር፣ በርግጥ ደስተኛ ትሆናለህ፤ በሕይወት ጦርነቶች የተሳካልህ ስለምትሆን ከዚህ በተሻለ ህይወት ወደ ክብርና ግርማ ከፍ ትላለህ። ‹‹የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ›› (ኢያሱ 24፡ 15)።--2T 564, 565 (1870). {1MCP 326.4}1MCPAmh 267.4

  በሌሎች ህሊናዎች ውስጥ ጣልቃ ላለመግባት።--ህሊና የእግዚአብሔርን ነገሮች በተመለከተ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር፣ የፈለገውን ያህል ሥልጣን ቢኖረው፣ ጣልቃ የመግባት መብት የሌለው የግለሰቡ ቅዱስ ሀብት ነው። ናቡከደነፆር ለእብራውያኑ ሌላ ዕድል ሰጥቶአቸው እምቢ ባሉ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ የሚነደው የእቶን እሳት በፊት ይነድ ከነበረው ሰባት እጥፍ እንዲነድ አዘዘ። ለምርኮኞቹ ወደ እቶን እሳት እንደሚጥላቸው ነገራቸው። በእምነትና በመታመን የተሞላ መልሳቸው እንዲህ የሚል ነበር፡- የምናመልከው አምላካችን ሊያድነን ይችላል፤ ሊያድነን ባይሻም እንኳን ግድ የለም፡-ራሳችንን ታማኝ በሆነው አምላክ እጅ አሳልፈን እንሰጣለን።--Lt 90, 1897. {1MCP 327.1}1MCPAmh 267.5

  ለሌሎች መስፈርት አይሆንም።--የአንተ ህሊና ለሌሎች መስፈርት እንዲሆን እግዚአብሔር አይፈልግም። መስራት ያለብህ ሥራ አለ። ያውም ራስህን ደስተኛ እንድታደርግና በዙሪያህ ያሉትን ሁሉ ደስተኛ ማድረግ ትልቁ ደስታህ እስኪሆን ድረስ በስሜቶችህ ውስጥ ራስን አለመውደድን እንድታሳድግ ነው። --4T 62 (1876). {1MCP 327.2}1MCPAmh 268.1

  ልጆች ንጹህ ህሊናን እንዲያቆዩ ወላጆች መርዳት አለባቸው።--ለወላጆች ይህን እንድል መመሪያ ተሰጥቶኛል፡- ልጆቻችሁ ንጹህና ያልጎደፈ ህሊና እንዲኖራቸው ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ። የእግዚአብሔርን ቃል እንዲመገቡ አስተምሩአቸው። የእግዚአብሔር ትንንሽ ልጆች እንደሆኑ አስተምሩአቸው። የእነርሱ አሳዳጊዎች እንድትሆኑ እንደ ሾማችሁ አትርሱ። ተገቢ የሆነ ምግብ ብትሰጡአቸውና ጤናማ በሆነ ሁኔታ ብታለብሱአቸው፣ ወደ ሰማያዊ አባታችን አብዝታችሁ እየጸለያችሁ የእግዚአብሔርን ቃል መስመር በመስመር፣ ጥቅስ በጥቅስ፣ እዚህ ጥቂት እና እዚያ ጥቂት ተግታችሁ ብታስተምሩአቸው ጥረቶቻችሁ ከፍተኛ ሽልማት ያስገኙላችኋል። --MS 4, 1905. {1MCP 327.3}1MCPAmh 268.2

  መንጻት ያለበት ህሊና።--ይብዛም ይነስም በነፍስ ቤተ መቅደስ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ክፍል ስለተበከለ መንጻት ያስፈልገዋል። የሸረሪት ድር ያደራ የህሊና ክፍል መገባት አለበት። የጽድቅ ፀሐይ ብሩህ ጮራዎች በነጻነት መግባት እንዲችሉ የነፍስ መስኮቶች ወደ ምድር መዘጋትና ወደ ሰማይ ደግሞ በሰፊው መከፈት አለባቸው። የማስታወስ ችሎታ በመጽሐፍ ቅዱስ መርሆዎች መታደስ አለበት። አእምሮ በመልካምና በክፉ መካከል መለየት እንዲችል ንጹህና ጽዱ ሆኖ መጠበቅ አለበት። ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ያስተማራውን ጸሎት ስትደግምና በየዕለቱ ሕይወት መልስ ለመስጠት ስትጥር ሳለ መንፈስ ቅዱስ አእምሮንና ልብን ያድስና ከፍ ያሉና ቅዱስ ተግባሮችን እንድትፈጽም ብርታት ይሰጥሃል። --MS 24, 1901. {1MCP 327.4}1MCPAmh 268.3

  የጠራ ህሊና ፍጹም ሰላምን ያመጣል።--የውስጥ ሰላምና እግዚአብሔርን ከመበደል ነጻ የሆነ ህሊና ለጋ በሆኑ ተክሎች ላይ እንደሚንቆረቆር ጤዛ አእምሮን በመቀስቀስ ያነቃቃል። ያኔ ፈቃድ በትክክል የተመራ፣ ቁጥጥር የተደረገበትና የበለጠውን ቁርጠኝነት ያለው ሆኖ ግን ምክንያታዊ ካለመሆን የጸዳ ይሆናል። ሀሳቦች የተቀደሱ ስለሚሆኑ አስደሳች ይሆናሉ። የምታገኘው የአእምሮ ሰላም ከአንተ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ይባርካል። ይህ ሰላምና እርጋታ በጊዜ ሂደት ተፈጥሮአዊ ይሆንና እንደገና በአንተ ላይ ተመልሶ ሊንጸባረቅ የከበሩ ጮራዎቹን በዙሪያህ ሁሉ ያንጸባርቃል። ይህን ሰማያዊ የሆነ የአእምሮ ሰላምና ፀጥታ በቀመስክ ቁጥር የበለጠውን እየጨመረ ይሄዳል። የሞራል ኃይሎችን ሁሉ እንዳይፈዙ የሚያደርግና እንቅስቃሴያቸው እንዲጨምር የሚያነቃ ተንቀሳቃሽና ሕያው ደስታ ነው። ፍጹም ሰላም መላእክት ያላቸው ሰማያዊ ጠባይ ነው። የዚህ ሰላም ባለቤት እንድትሆን እግዚአብሔር ይርዳህ። --2T 327 (1869). {1MCP 328.1}1MCPAmh 269.1