Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 9—አእምሮ፣ አካልን የሚጠብቅ ምሽግ

  የአካል መዲና።--እያንዳንዱ የአካል ክፍል የተፈጠረው ለአእምሮ ተገዥ እንዲሆን ነው። አእምሮ የአካል መዲና ነው። --3T 136 (1872). {1MCP 72.1}1MCPAmh 61.1

  አእምሮ መላውን ሰው ይቆጣጠራል። ድርጊቶቻችን በሙሉ፣ ጥሩም ቢሆኑ መጥፎ፣ ምንጫቸው አእምሮ ነው። እግዚአብሔርን የሚያመልከውና ከሰማያዊ ፍጡራን ጋር እንድንወዳጅ የሚያደርገን አእምሮ ነው። ሆኖም ብዙዎች ይህን ሀብት የያዘውን የእንቁ መያዣ በተመለከተ በቂ እውቀት ሳይኖራቸው ሕይወታቸውን በሙሉ ይጨርሳሉ።--SpTED 33, May 11, 1896. (FE 426.) {1MCP 72.2}1MCPAmh 61.2

  አእምሮ አካልን ይቆጣጠራል።--ልምምዳቸው ሊታመን እንደማይችል ማንም ሊያሳምናቸው ስለማይችል ዛሬ ታማሚ የሆኑና ለሁልጊዜም እንዲሁ ሆነው የሚቀጥሉ ሰዎች አሉ። አእምሮ የአካል መዲና፣ የመላው ነርቭ ኃይሎችና የአእምሮ ድርጊት መቀመጫ ነው። ከአእምሮ የሚወጡ ነርቮች አካልን ይቆጣጠራሉ። በአእምሮ ነርቮች አማካይነት በቴሌግራፍ ገመዶች እንደሚሆን በአእምሮ የተፈጠሩ መልእክቶች ወደ መላው የአካል ነርቮች ይተላለፉና የእያንዳንዱን የአካል ክፍል ዋና የሆነ ተግባር ይቆጣጠራሉ። ሁሉም ለእንቅስቃሴ የሚያገለግሉ የአካል ክፍሎች ከአእምሮ ለሚቀበሉት መልእክት ይገዛሉ።--3T 69 (1872). 73 {1MCP 72.3}1MCPAmh 61.3

  ከመላው የአካል ክፍሎች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩት የአእምሮ ነርቮች ሰማይ ከሰው ጋር ግንኙነት የሚፈጥርባቸውና ውስጣዊ ሕይወቱ ላይ ተጽእኖ የሚያሳድርበት ብቸኛው ማዕከል ናቸው። --2T 347 (1870). {1MCP 73.1}1MCPAmh 61.4

  ሰይጣን ጥቃት የሚያደርሰው ነገሮችን በሚገነዘቡ ክፍሎች ላይ ነው። [ምዕራፍ 35፣ ‹‹ነገሮችን የመገንዘብ ችሎታ ተጽእኖ›› የሚለውን ይመልከቱ]--ሰይጣን ወደ ክርስቶስ እንደመጣ ሁሉ ፈተናዎቹን ይዞ ወደ ሰው የሚመጣው በብርሃን መልአክ ተመስሎ ነው። እርሱ በፈተናዎቹ አማካይነት ሊያሸንፈውና በጥፋቱ ድሉን ሊያረጋግጥ ሰውን በአካልና በግብረገብ ደካማ እንዲሆን ለማድረግ ሲሰራ ቆይቷል። ውጤቱ ምንም ቢሆን ሰው የምግብ ፍላጎቱን እንዲያረካ በመፈተን ተሳክቶለታል። ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን የአካል ክፍሎች ካበላሸ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለመሰሎቹ ያለበትን ግዴታዎች መወጣት እንደማይችል ያውቃል። አእምሮ የአካል ርዕሰ ከተማ ነው። የሚያገናዝቡ የአካል ክፍሎች ከማንኛውም ዓይነት መሻትን አለመግዛት የተነሣ ከደነዘዙ ዘላለማዊ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አይቻልም። --RH, Sept 8, 1874. (MYP 236.) {1MCP 73.2}1MCPAmh 61.5

  የልማድ አምባገነንነት።--የአእምሮ ጥንካሬ ወይም ድክመት በዚህ ዓለም በሚኖረን ጠቃሚነታችን ላይም ሆነ በመጨረሻው ድነታችን ላይ የሚጫወተው ብዙ ሚና አለው። በአካላዊ ተፈጥሮአችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ሕግ በተመለከተ እየታየ ያለው ድንቁርና የሚያስጠላ ነው። ጅልነት አስከፊ በሆነ ደረጃ እየታየ ነው። ሰይጣን በላዩ እያለበሰ ካለው ብርሃን የተነሣ ኃጢአት ማራኪ ስለሚሆን የክርስቲያኑን ዓለም እንደ አህዛብ በልማድ አምባገነንነት ሥር በዕለታዊ ልማዶች መያዝ ሲችልና የምግብ ፍላጎት እንዲገዛቸው ሲፈቅድ በደንብ ይደሰታል። --RH, Sept 8, 1874. (MYP 237.) {1MCP 73.3}1MCPAmh 62.1

  ምሽጉን መጠበቅ።--ሁሉም ሁልጊዜ ነቅቶ በመጠበቅ የተደገፈ የግብረገብ ተፈጥሮን የመጠበቅ አስፈላጊነት ሊሰማቸው ይገባል። እንደ ታማኝ ዘቦች ጥበቃቸውን ለአፍታ እንኳን ማላላት እንዳለባቸው ሳይሰማቸው የነፍስን ምሽግ መጠበቅ አለባቸው። --SpTPH 65, 1879. (CH 411.) {1MCP 73.4}1MCPAmh 62.2

  በትክክል የሰለጠነ አእምሮ አያወላውልም።--የታማኝነት ልምዶችን በተመለከተ፣ ከዝንባሌና ከመደሰቻ በላይ ትክክለኛነትና ተግባር ስለሚጠይቁት ነገር ስሜት እንዲኖር አእምሮ በየዕለቱ በሚመጡ ፈተናዎች አማካይነት መሰልጠን አለበት። በዚህ መልክ የሰለጠኑ አእምሮዎች በውኃ ዳር ያለ ቄጠማ በንፋስ ወዲያና ወዲህ እንደሚወዛወዝ ትክክል በሆነውና ባልሆነው መካከል አያወላውሉም፤ ነገሮች በፊታቸው እንደቀረቡላቸው ወዲያውኑ መርሆዎችን የሚነካ መሆኑን ይለያሉ፣ እንዲሁም በጉዳዩ ለረዥም ጊዜ ሳይከራከሩ ትክክል የሆነውን ወዲያው ይመርጣሉ። ራሳቸውን ለታማኝነትና ለእውነት ልምዶች ስላሰለጠኑ ታማኝ ናቸው።-- 3T 22 (1872). {1MCP 74.1}1MCPAmh 62.3

  ጥበቃ ያልተደረገለት ምሽግ።--በመመልከት እንለወጣለን። ምንም እንኳን ሰው በፈጣሪው አምሳል ቢፈጠርም በአንድ ወቅት ይጠላው የነበረው ኃጢአት አስደሳች ነገር እንዲሆንለት አእምሮውን ማስተማር ይችላል። ነቅቶ መጠበቅንና መጸለይን ሲተው ምሽጉን ወይም ልቡን መጠበቁን ይተውና ኃጢአትንና ወንጀልን በመስራት ላይ ይሰማራል። አእምሮ ስለወረደ (ስለረከሰ) የግብረገብና የአእምሮ ኃይሎችን ለባርነትና ላልታረሙ ጥልቅ ስሜቶች ለማስገዛት እየተማረ ሳለ ከእርኩሰት ማንጻት የማይቻል ነገር ነው። ከሥጋዊ አእምሮ ጋር የማያቋርጥ ጦርነት መገጠም አለበት፤ በዚህ ጦርነት ላይ አእምሮን ወደ ላይ በሚስብና ንጹህና ቅዱስ በሆኑ ነገሮች ላይ እንዲያሰላስል በውስጡ በሚያድርና በሚያስተካክል በእግዚአብሔር ጸጋ ተጽእኖ መመራት አለብን። --2T 479 (1870). {1MCP 74.2}1MCPAmh 62.4

  የሕይወትና የሞት ጉዳዮች ምንጭ።--‹‹በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም›› (ቆላስያስ 3፡ 2)። ልብ የሰው ምሽግ ነው። ከእርሱ የህይወት ወይም የሞት ጉዳዮች ይወጣሉ። ልብ እስኪነጻ ድረስ አንድ ግለሰብ በቅዱሳን ሕብረት ውስጥ ምንም ዓይነት ድርሻ ሊኖረው ገጣሚ አይደለም። ልብን የሚመረምረው አምላክ በኃጢአት እየቆዩ ያሉት እነማን እንደሆኑ አያውቅምን? በእያንዳንዱ ግለሰብ ሕይወት ውስጥ እጅግ ምስጢር በሆነ ሁኔታ ሲካሄዱ ለነበሩ ነገሮች ምስክር አልነበረምን? {1MCP 74.3}1MCPAmh 62.5

  አንዳንድ ወንዶች ለአንዳንድ ሴቶችና ልጃገረዶች ሲናገሩ የነበሩ ቃላትን ለመስማት ተገድጄ ነበር--የማታለል ቃላት፣ የሚያሳስቱና በስድ ፍቅር እንዲያዙ የሚያደርጉ ቃላት። ሰይጣን ነፍሳትን ለማጥፋት እነዚህን ሁሉ መንገዶች ይጠቀማል። አንዳንዶቻችሁ የእርሱ ወኪሎች የነበራችሁ ልትሆኑ ትችላላችሁ፤ እንዲህ ከሆነ እነዚህን ነገሮች በፍርድ ቀን ትጋፈጣላችሁ።1MCPAmh 63.1

  ይህን ክፍል በተመለከተ መልአኩ እንዲህ አለ። ‹‹ልባቸው በፍጹም ለእግዚአብሔር ተሰጥቶ አያውቅም። ክርስቶስ በውስጣቸው የለም። በዚያ እውነት የለም። የእርሱን ቦታ ኃጢአት፣ ማታለል እና ውሸት ይዟል። የእግዚአብሔር ቃል አልታመነም፣ ሥራ ላይም አልዋለም። --5T 536, 537 (1889). {1MCP 74.4}1MCPAmh 63.2

  እፎይታ፣ የሚፈልጉትን ማድረግ፣ ደህንነት--ከሀዲዎች በግንብ (በቅጥር) ውስጥ።--እሥራኤላውያን ወደ ኃጢአት የተመሩት ውጫዊ የሆነ እፎይታና ደህንነት በነበረበት ሁኔታ ነበር። ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊታቸው ማድረግ አቃታቸው፣ ጸሎትን ችላ ብለው በራስ የመተማመንን መንፈስ ተንከባከቡ። እፍይታና የፈለጉትን ማድረግ የነፍስን ምሽግ ያለ ጥበቃ ስላስቀረው የወረዱ አሳቦች መግቢያ አገኙ። የመርህን ምሽግ ያፈረሱና እሥራኤልን ለሰይጣን ኃይል አሳልፈው የሰጡት በቅጥሮች ውስጥ የነበሩ ከሀዲዎች ነበሩ። {1MCP 75.1}1MCPAmh 63.3

  አሁንም ሰይጣን የነፍስን ጥፋት ለማምጣት የሚፈልገው በዚህ ሁኔታ ነው። ክርስቲያን ግልጽ የሆነ ኃጢአት ከመፈጸሙ በፊት ለዓለም ያልታወቀ ረዥም የዝግጅት ሂደት ይካሄዳል። አእምሮ ከንጽህናና ከቅድስና ወደ ሕገወጥነት፣ ወደ የሥነ-ምግባር ውድቀትና ወደ ወንጀል በአንድ ጊዜ አይወርድም። በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ወደ ጭካኔ ወይም ወደ ሳይጣናዊነት ደረጃ ዝቅ ለማድረግ ጊዜ ይጠይቃል። በመመልከት እንለወጣለን። ንጹህ ያልሆኑ አሳቦችን በማስተናገድ ሰው ከዚህ በፊት ይጠላው የነበረው ኃጢአት የሚያስደስተው እስኪሆን ድረስ አእምሮውን ያስተምራል።--PP 459 (1890). {1MCP 75.2}1MCPAmh 63.4

  ትንባሆ ስሜቶችን በድን ያደርጋል።--ትንባሆ በማንኛውም መልክ ጥቅም ላይ ከዋለ በአካል ላይ የሚታይ ለውጥ ያመጣል። ትንባሆ ቀስ ብሎ የሚገድል መርዝ ነው። አእምሮ መንፈሳዊ ነገሮችን፣ በተለይም ይህን ቆሻሻ ነገር መጠቀምን የማረም ዝንባሌ ያላቸውን እውነቶች አጥርቶ መለየት እንዳይችል አእምሮን ይጎዳና ስሜቶችን ያበድናል። {1MCP 75.3}1MCPAmh 63.5

  ትንባሆን በማንኛውም መልክ የሚጠቀሙ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ግልጽ አይደሉም። እንደዚህ ያለ ቆሻሻ ልምምድ እያላቸው የራሱ በሆኑት በአካልና በመንፈስ እግዚአብሔርን ማክበር የማይቻል ነገር ነው። ጤንነታቸውን እያቃወሱና የአእምሮ ክፍሎቻቸውን ዝቅ እያደረጉ በቀስታ ግን በእርግጠኝነት የሚጎዱ መርዞችን እየተጠቀሙ ሳለ እግዚአብሔር ሊረዳቸው አይችልም። ይህ መጥፎ ልምድ እያደረሰባቸው ያለውን ጉዳት ካለማወቃቸው የተነሣ እየፈጸሙት ከሆነ ሊምራቸው ይችላል፣ ነገር ግን ጉዳዩ በእውነተኛ ብርሃን ከፊታቸው ቀርቦላቸው ሳለ ይህን መጥፎ ፍላጎታቸውን መፈጸማቸውን ከቀጠሉ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ናቸው።--4SG 126 (1864). {1MCP 75.4}1MCPAmh 64.1

  የአስካሪ መጠጥና የአደንዛዥ እፆች ባሪያዎች።--ሰይጣን፣ በሁሉም አቅጣጫ፣ ወጣቶች የእርሱ ሲሳይ በሚሆኑበት መንገድ ሊመራቸው ይሻል፤ አንድ ጊዜ ብቻ እግሮቻቸው በዚያ መንገድ ላይ እንዲቆሙ ማድረግ ከቻለ ግዳዮቹን በቁልቁለት መንገድ እያጣደፋቸው፣ ከአንዱ ከንቱ ሕይወት ወደ ሌላው እየመራቸው፣ የህሊና ደግነትን በማጣት በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት እንዳይኖር ያደርጋል። ራስን የመቆጣጠር ልምምዳቸው አነስተኛ ነው። ወይንና አስካሪ መጠጥን፣ ትንባሆንና ኦፒየም የሚባል አደንዛዥ እፅን የመጠቀም ሱሰኞች ይሆኑና ከአንዱ የእርኩሰት መድረክ ወደ ሌላኛው ይሸጋገራሉ። የምግብ ፍላጎት ባሪያዎች ናቸው። ከዚህ በፊት ያከብሩት የነበረውን ምክር መናቅ ይማራሉ። የክፋትና የሥነ-ምግባር ብልሽት ባሪያዎች ሆነው ሳለ የመጀነን አየርን ይለብሱና ስለተሰጣቸው ነጻነት ይኩራራሉ። ለእነርሱ ነጻነት ማለት የራስ ወዳድነት ባርነት፣ የወረደ የምግብ ፍላጎት፣ እና ልቅ የሆነ የወሲብ ስሜት ናቸው። --ST, June 22, 1891. (Te 274.) {1MCP 76.1}1MCPAmh 64.2

  የሰይጣን የጦር መሣሪያዎች።--የሥጋ ፍትወትን መፈጸም ነፍስን ይዋጋል። ሐዋርያው እጅግ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ለክርስቲያኖች እንዲህ በማለት ይናገራል‹- ‹‹እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፣ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ›› (ሮሜ 12፡1)። አካል በአስካሪ መጠጥ የተሞላና በትንባሆ የተበከለ ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ቅዱስና ተቀባይነት ያለው አይደለም። ሰይጣን ይህ ሊሆን እንደማይችል ስለሚያውቅ፣ በሰዎች ላይ የምግብ ፍላጎት ፈተናን በማምጣት፣ የዚህ የተፈጥሮ ዝንባሌ ምርኮኛ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲጠፉ ይሰራል። --RH, Sept 8, 1874. {1MCP 76.2}1MCPAmh 64.3

  ጠንካራ ስሜትንና የምግብ ፍላጎትን በተመለከተ ወሳኙ ነገር።--የተማረ አእምሮ ያላቸው ወንዶችና ሴቶች፣ በማንኛውም ዓይነት መሻትን አለመግዛት የሞራል ኃይሎቻቸው ከደነዘዙ፣ በብዙ ልማዶቻቸው ከፍ ያሉ ቢሆንም ከአህዛብ አይሻሉም።1MCPAmh 65.1

  ሰይጣን የአካል፣ የአእምሮ፣ እና የሞራል ጤናን ሳይለይ ሰዎችን ሁልጊዜ ከሚያድን ብርሃን ወደ ወግና ፋሽን በመሳብ ላይ ይገኛል። የምግብ ፍላጎትና ጠንካራ ስሜት የበላይነት ባገኙበት ሁሉ የአካል ጤናና የአእምሮ ብርታት ራስን በማስደሰት መሰዊያ ላይ መስዋዕት እንደሚሆኑና ሰው በፍጥነት ወደ ጥፋት እንደሚመጣ ታላቁ ጠላት ያውቃል። የተማረ አእምሮ የእንስሳ ዝንባሌዎችን በመቆጣጠር ለግብረገብ ኃይሎች እንዲገዙ ለማድረግ ልጓሙን ከያዘ በፈተናዎቹ አማካይነት የማሸነፍ ኃይሉ እጅግ ትንሽ መሆኑን ሰይጣን በደንብ ያውቃል። --RH, Sept 8, 1874. (MYP 237.) {1MCP 76.3}1MCPAmh 65.2

  መሆን የነበረበት።--ባለፉት ትውልዶች የነበሩ ወላጆች በዓላማ ጽናት አካልን የአእምሮ አገልጋይ አድርው አቆይተው ቢሆንና የአእምሮ ማስተዋል ለእንስሳዊ ስሜቶች እንዲገዛ ባይፈቅዱ ኖሮ፣ በዚህ ዘመን በምድር ላይ የተለየ የፍጡራን ሥርዓት ይኖር ነበር። --HL (Part 2) 38, 1865. (2SM 431, 432.) {1MCP 77.1}1MCPAmh 65.3

  የአእምሮ ምርጫ ወይም የአካል ቁጥጥር።--እያንዳንዱ ተማሪ በተራ ኑሮና በከፍተኛ አስተሳሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት መረዳት ያስፈልገዋል። ሕይወታችን በአካል ወይም በአእምሮ ቁጥጥር እንዲሆን የመወሰኑ ጉዳይ በግል በእኛ ላይ ያርፋል። እያንዳንዱ ወጣት ሕይወቱን መልክ የሚያስይዘውን ምርጫ ለራሱ ማድረግ አለበት፤ ከምን ዓይነት ኃይሎች ጋር እንደሚሰራ ለማወቅና ባሕርይንና የመጨረሻ መዳረሻን የሚቀርጹ ኃይሎችን ለመረዳት ማድረግ የሚችለውን ሁሉ ማድረግ አለበት። --Ed 202 (1903). {1MCP 77.2}1MCPAmh 65.4

  ሕዝብን አስተምሩ።--የምግብ ፍላጎትን የመቋቋም አስፈላጊነትን ለሕዝብ አስተምሩ። ብዙዎች እየወደቁ ያሉት በዚህ ነጥብ ላይ ነው። አካልና አእምሮ ምን ያህል በቅርበት የተገናኙ እንደሆኑ አስረዱአቸውና ሁለቱንም በጥሩ ሁኔታ የመጠበቅን አስፈላጊነት አሳዩአቸው። --Circular Lt to Physicians and Evangelists, 1910. (CH 543.) {1MCP 77.3}1MCPAmh 65.5

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents