Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 5—አክራሪ አእምሮ

  አክራሪዎችና አክራሪነት ወደ ፊት ይቀጥላሉ።---በአማኞችና አማኞች ባልሆኑ ሰዎች መካከል እያንዳንዱ የአክራሪነት ገጽታ ወደ ፊት በሚቀጥልበት ጊዜ ውስጥ በመኖር ላይ እንገኛለን። ሰይጣን በግብዝነት ውሸትን በመናገር ይመጣል። ወንዶችንና ሴቶችን ለማሳሳት ሊፈለስፍ የሚችለው እያንዳንዱ ነገር ይቀርባል። --Lt 121, 1901. (MM 114.) {1MCP 38.1}1MCPAmh 34.1

  ይህን ነገር ሰይጣን እንዴት እንደሚሰራ።---ከልምምዳችን እንዳገኘነው ሰይጣን ነፍሳትን በግድየለሽነት በረዶ ውስጥ ሊያስራቸው ካልቻለ በአክራሪነት እሳት ውስጥ ሊገፋቸው ይሞክራል። የእግዚአብሔር መንፈስ በሕዝቡ መካከል ሲመጣ ጠላት ደግሞ በተለዩ አእምሮዎች ውስጥ ሊሰራና የራሳቸውን ልዩ ባሕርያት ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር እንዲቀላቅሉ ሊመራቸው አጋጣሚውን ይጠቀማል። ስለዚህ የራሳቸውን መንፈስ ከሥራው ጋር በመቀላቀል ጥበብ የጎደለው እንቅስቃሴ የማድረግ አደጋ ሁል ጊዜም አለ። ብዙዎች እግዚአብሔር እንዲሰራ ያላዘዘውን ግን ራሳቸው የቀየሱትን ሥራ ይሰራሉ። --Lt 34, 1889. (Similar to 5T 644.) {1MCP 38.2}1MCPAmh 34.2

  እንከን (ጉድለት) ያለባቸውን ዝንባሌዎች የመንከባከብ ውጤት።---አንዳንድ የማይሰሙ ሰዎች አሉ። ለረዥም ጊዜ የራሳቸውን መንገድና የራሳቸውን ጥበብ ለመከተል ስለመረጡ፣ ለረዥም ጊዜ በውርስ ያገኙትንም ሆነ እራሳቸው ያጎለበቱአቸውን ጉድለት ያለባቸውን የባሕርይ ዝንባሌዎች ከመንከባከባቸው የተነሣ ስለታወሩ አርቀው ማየት አይችሉም። በእነርሱ መርሆዎች ተዛብተዋል፣ የውሸት መስፈርቶች ተቀምጠዋል፣ የሰማይ ማህተም ያላረፈባቸው ፈተናዎች ተዘጋጅተዋል።…ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ጽድቅ እንደሰራና የአምላካቸውን ትዕዛዛት እንዳልተወ ሕዝብ ይኩራራሉ። --MS 138, 1902. {1MCP 38.3}1MCPAmh 34.3

  ጤናማ የሆነ የአእምሮ አመለካከት እጦት።---በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ የተያዙ ሰዎች ጤናማ ወደ ሆነ የአእምሮ አመለካከት አልደረሱም። በትክክል ማሰብ አይችሉም፣ ለራሳቸው ከፍተኛ ቦታ ይሰጣሉ፣ በራሳቸው ብቃት ይተማመናሉ። ኦ፣ እንደዚህ ያሉትን ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት ባለ ሀዘኔታ ይመለከታቸው ይሆን፣ ታላቅ የሆኑና ያበጡ የከንቱነት ቃላቶቻቸውንም እንዴት ባለ ሀዘኔታ ይሰማ ይሆን። እነርሱ በኩራት የተነፉ ናቸው። ጠላት እንዲህ በቀላሉ በመማረካቸው በመደነቅ እየተመለከታቸው ነው። --Lt. 126, 1906. {1MCP 39.1}1MCPAmh 34.4

  የውሸት ራስን ዝቅ ማድረግ።---ክርስቲያኖች ነን በሚሉ ሰዎች መካከል ቀጣይነት የሌለው የውሸት ትህትና (ራስን ዝቅ ማድረግ) ይታያል። አንዳንዶች ራስን ለማሸነፍ ቁርጥ ሀሳብ ስላላቸው በተቻላቸው መጠን ራሳቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፤ ነገር ግን የሚሞክሩት በራሳቸው ብርታት ብቻ ስለሆነ ቀጥሎ የሚመጣው የምሥጋና ወይም የውሸት ሙገሳ ማዕበል ከዕይታ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል። ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ለማስገዛት ፈቃደኛ ካለመሆናቸው የተነሣ እርሱ በእነርሱ አማካይነት መሥራት አይችልም። {1MCP 39.2}1MCPAmh 35.1

  ምንም ቢሆን ክብሩን ለራስህ አትውሰድ።---በአንድ ጊዜ ራስህንና እግዚአብሔርን ለማገልገል እየሞከርክ በተከፋፈለ አእምሮ አትሥራ። ቃላቶችህ የደከሙትንና ሸክም የከበደባቸውን ርኅሩኅ አዳኝ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ ይምሩ። ለአገልግሎት ብርታት ሊሰጥህ ተዘጋጅቶ በቀኝ እጅህ በኩል ያለውን እርሱን እየተመለከትክ እንዳለህ ሆነህ ሥራ። ከአደጋ የምትጠበቀው ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ላይ በመደገፍህ ነው። --RH, May 11, 1897. {1MCP 39.3}1MCPAmh 35.2

  ከመጠን ያለፈ ደስታ ያለበት የስሜት በረራ።---አንዳንዶች ኃይለኛ የሆነ ደስታ ያለበትን ጊዜ ማሳልፍ ካልቻሉ በስተቀር በመሰብሰባቸው አይረኩም። ለዚህ ስለሚሰሩ የስሜት መነሳሳትን ይቀሰቅሳሉ። ነገር ግን እንደዚህ ያሉ ስብሰባዎች የሚያሳድሩት ተጽእኖ ጠቃሚ አይደለም። ያ ደስታ ያለበት የስሜት በረራው ሲያበቃ ደስታቸው ከትክክለኛው ምንጭ ስላልመጣ ከስብሰባው በፊት ከነበሩበት ሁኔታ ወደ ታች ይወርዳሉ (ይሰምጣሉ)። ለመንፈሳዊ እድገት እጅግ ትርፋማ የሆኑ ስብሰባዎች ጭምትነትና ጥልቅ የሆነ ልብን መመርመር የሚታይባቸው ስብሰባዎች ማለትም እያንዳንዱ ሰው ራሱን ለማወቅ በመፈለግ በእውነተኛ ልብና ጥልቅ በሆነ ራስን ዝቅ በማድረግ ከክርስቶስ ለመማር በመሻት የሚያሳልፍባቸው ስብሰባዎች ናቸው። --1T 412 (1864). {1MCP 39.4}1MCPAmh 35.3

  እንግዳ የሆኑ ተግባራት (ልምዶች)።---በቅርቡ በመካከላችን በካሊፎርኒያ ልዩ በሆኑ እንቅስቃሴዎችና አጋንንትን ለማውጣት ኃይል ተሰጥቶናል በማለት በታየው አክራሪነት ሰይጣን ቢቻለው የተመረጡትን እንኳን ሊያስታቸው በመሻት ላይ ይገኛል። እነዚህ ሰዎች፣ ለሕዝባችን የሚሆን የተለየ መልእክት እንዳላቸው በመናገር፣ ይህንና ያንን ክፉ መንፈስ ይዞሃል በማለት ይወነጅላሉ። በመቀጠልም ከእነዚህ ሰዎች ጋር አብረው ከጸለዩ በኋላ አጋንንቱ እንደወጣ ይናገራሉ። የሥራቸው ውጤት ስለ ባሕርዩ መሰከረ። በእነዚህ እንግዳ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እግዚአብሔር እንደሌለበት፣ ነገር ግን ሰዎች ማስጠንቀቂያ ካልተሰጣቸው በስተቀር እነዚህ የሚታዩ ነገሮች ነፍሳትን ለጥፋት ወደሚያደርስ መታለል ሊመሩ እንደሚችሉና ከዚህ የተነሣ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ሊዛባ እንደሚችል ለሕዝባችን እንድናገር ታዝዣለሁ። --Lt 12, 1909. {1MCP 40.1}1MCPAmh 35.4

  በተፈጥሮው ጦረኛ።---አንዳንዶች በተፈጥሮአቸው ጦረኞች ናቸው። ከወንድሞቻቸው ጋር ቢጣጣሙ ወይም ባይጣጣሙ ግድ የላቸውም። ተቃርኖ ውስጥ ይገባሉ፣ የራሳቸው ሀሳቦች ተቀባይነት እንዲያገኙ ለማድረግ ጦርነት ይገጥማሉ፤ ነገር ግን ይህ የክርስቲያን ፀጋዎችን ስለማያሳድግ ወደ ጎን መተው አለበት። ክርስቶስ እርሱ ከአባቱ ጋር አንድ እንደሆነ ደቀ መዛሙርቱም አንድ ይሆኑ ዘንድ ለጸለየው ጸሎት ምላሽ ትሰጡ ዘንድ ባላችሁ ኃይል ሁሉ ሥሩ።በየቀኑ ከክርስቶስ ገርነትንና ራስን ዝቅ ማድረግን ካልተማርን በስተቀር ከእኛ መካከል አንድም ነፍስ ከአደጋ ነጻ አይደለም። {1MCP 40.2}1MCPAmh 36.1

  በሥራህ አምባገነን፣ ጨካኝ፣ ሌሎችን ተቃዋሚ አትሁን። የክርስቶስን ፍቅር ስበክ፣ ይህ ልቦችን ያቀልጥና እንዲገዙ ያደርጋል። ከወንድሞቻችሁ ጋር አንድ ልብና አንድ አሳብ እንዲኖራችሁ ንግግራችሁም አንድ እንዲሆን እሹ። ለአንተ አእምሮ እንደመሰለህ ሁሉም አንድ አሳብ ስለሌላቸው ስለ መለያየት መናገር የእግዚአብሔር ሥራ ሳይሆን የጠላት ሥራ ነው። መስማማት ስለምትችሉበት ቀላል ስለሆነው እውነት ተናገሩ። ስለ አንድነት ተናገር፤ ጠባብና ከልክ ያለፈ ትዕቢተኛ አትሁን፤ አእምሮህን አስፋ። --MS 111, 1894. {1MCP 40.3}1MCPAmh 36.2

  በራስ የተመሰረቱ መርሆዎችን መከተል።---ብዙዎች በራሳቸው ጽድቅ እየታመኑ ናቸው። ለራሳቸው መስፈርትን ያስቀምጡና ለክርስቶስ ፈቃድ አይገዙም፣ እርሱ የራሱን የጽድቅ ቀሚስ እንዲያለብሳቸውም አይፈቅዱለትም። ባሕርያቸውን እንደ ራሳቸው ፈቃድና ደስ እንደሚያሰኛቸው ይመሰርታሉ። ሰይጣን በኃይማኖታቸው እጅግ ደስተኛ ነው። ለክርስቶስ ፍጹም ባሕርይ--ለጽድቅ--የተሳሳተ ገጽታ ይሰጣሉ። ራሳቸው ተታለው ሌሎችን ያታልላሉ። በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም።ሌሎች ነፍሳትን በውሸት መንገድ ለመምራት የተጋለጡ ናቸው። በመጨረሻ ከታላቁ አታላይ፣ ከሰይጣን፣ ጋር ዋጋቸውን ያገኛሉ። --MS 138, 1902. {1MCP 41.1}1MCPAmh 36.3

  አክራሪ የነበረ ሰው ያሳየው ባሕርይ።--- በካሊፎርኒያ ከሚገኘው ከሬድ ብላፍ የሆነ ኤን የሚባል ሰው መልእክቱን ለማስተላለፍ ወደ እኔ ከመጣ ጥቂት አመታት አልፈዋል።…እግዚአብሔር መሪ የነበሩ ሰራተኞችን ሁሉ አልፎአቸው ለእርሱ መልእክት እንደሰጠው አሰበ። እንደ ተሳሳተ ለማሳየት ጥረት አደረግኩ።…ስለ መሳሳቱ ምክንያቶቻችንን ነግረነው ጉዳዩን በፊቱ ስናቀርብለት ትልቅ ኃይል በላዩ ወረደና ታላቅ ጩኸት ጮኸ። ብዙ ተቸገርን፤ አእምሮው ሚዛኑን ሳተና አእምሮአቸውን የሳቱ ሰዎች በሚረዱበት ቦታ አስቀመጥነው። --Lt 16, 1893. (2SM 64.) {1MCP 41.2}1MCPAmh 36.4

  አክራሪዎችን መጋፈጥ።- እግዚአብሔር አገልጋዮቹ የእርሱን አእምሮና ፈቃድ እንዲያጠኑ ይጠራቸዋል። እንዲህ ሲሆን ሰዎች ራሳቸው ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ የፈለሰፉአቸውን መላምቶች ይዘው ሲመጡ ከእነርሱ ጋር ግጭት ውስጥ አትግባ፣ ነገር ግን የምታውቀውን ነገር አረጋግጥላቸው። ‹‹ተጽፏል›› የሚለው የእግዚአብሔር ቃል የጦር መሳሪያህ ይሁን። የራሳቸውን የውሸት መላምት ክሮችን መሸመን የሚሞክሩ ሰዎች አሉ። ከእግዚአብሔር የተማሩና እውነት ምን እንደሆነ የሚያውቁ ሰዎች ስላሉ እግዚአብሔርን አመስግን። --Lt 191, 1905. {1MCP 41.3}1MCPAmh 37.1

  የሀሳብ አገላለጻችሁንና አመለካከታችሁን ጠብቁ።---በጣም ነቅተን መጠበቅና የተሰራውን ሥራ ባሕርይ ከአደጋ መከላከል ያለብን ጊዜ አሁን ነው። አንዳንዶች የሀሰት መላምቶችን ለማስገባት በመፈለግ የውሸት መልእክቶችን ይዘው ይመጣሉ። በመካከላችን አክራሪነትን ለመፍጠር ሰይጣን ሰብአዊ አእምሮዎችን ያነሳሳል። የዚህ ዓይነቱን ነገር በ1908 ዓ.ም. አይተናል። እግዚአብሔር ሕዝቦቹ ንግግራቸውንና አመለካከታቸውን በመጠበቅ በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀሱ ይሻል። ሰይጣን መነሳሳትን ለመፍጠር እና ለማታለል በሰዎች አእምሮ ውስጥ ለመሥራት የአመለካከትና የድምፅ ልዩነትን ይጠቀማል።--Lt 12, 1909. {1MCP 41.4}1MCPAmh 37.2

  የሰው ፈጠራ መመዘኛዎችን አስወግዱ።- የእግዚአብሔርን ሕዝብ ወደ ውሸት መነሳሳት፣ ኃይማኖታዊ መነቃቃት እና አንድን ነገር ለማወቅ ወደ መፈለግ ሁኔታዎች ለመምራት አዲስና እንግዳ የሆኑ ነገሮች ያለማቋረጥ ይነሳሉ፤ ነገር ግን ሕዝባችን በማንኛውም መስመር ቢሆን ተቃርኖን ለሚፈጥር ለማንኛውም ሰብአዊ ፈጠራ ተገዥ መሆን የለበትም። --MS 167, 1897. {1MCP 42.1}1MCPAmh 37.3

  ‹‹አዲስ፣›› ‹‹ድንቅ፣›› ከፍ ያለ ብርሐን ከሚባል ነገር ተጠንቀቁ።…ከፊታችን ያለውን ነገር ስለማውቅ ነፍሴ ሸክም ይሰማታል። በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ጋር ሕያው ግንኙነት በሌላቸው ሰዎች ላይ እያንዳንዱ ሊታሰብ የሚችል ማታለያ ይመጣል። የሰይጣን መላእክት ክፉ ለመሥራት ጠቢብ ስለሆኑ አንዳንዶች ከፍ ያለ ብርሐን ነው የሚሉትን በመፍጠር አዲስና ድንቅ ነው በማለት ያውጃሉ፤ በአንዳንድ አቅጣጫዎች ሲታይ መልእክቱ እውነት ሊሆን ቢችልም ከሰው ፈጠራዎች ጋር በመቀላቀል የሰዎችን ትዕዛዛት እንደ አስተምህሮ ያስተምራሉ። እውነተኛ በሆነ ግለት መንቃትና መጸለይ ያለብን ጊዜ ቢኖር ያ ጊዜ አሁን ነው። {1MCP 42.2}1MCPAmh 37.4

  ብዙ ጥሩ የሚመስሉ ነገሮች በብዙ ጸሎትና በጥንቃቄ መታየት አለባቸው፤ እነዚህ ጥሩ የሚመስሉ ነገሮች ወደ እውነት መንገድ እጅግ ከመጠጋታቸው የተነሣ ከእውነት ለመለየት ስለሚከብድ ጠላት ነፍሳትን በስህተት መንገድ ላይ ለመምራት የሚጠቀምባቸው አሳሳች መሳሪያዎች ናቸው። ነገር ግን ምንም እንኳን ለማየት ከባድ ቢሆንም የእምነት ዓይን ከትክክለኛው መንገድ ያፈነገጠውን ነገር ለይቶ ያውቃል። በመጀመሪያ አዎንታዊ በሆነ መልኩ ትክክል እንደሆነ ሊታሰብ ይችላል፣ ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ቅድስናና ወደ ሰማይ ከሚወስደው መንገድ በስፋት ያፈነገጠ መሆኑ ይታያል። ወንድሞቼ ሆይ፣ ሽባዎች እንኳን እንዳይስቱት ለእግሮቻችሁ ቀጥ ያለ መንገድ እንድትሰሩ አስጠነቅቃችኋለሁ።--MS 82, 1894. {1MCP 42.3}1MCPAmh 38.1

  አክራሪነት ለማጥፋት ከባድ ነው።---አክራሪነት አንዴ ከተጀመረና ቁጥጥር ካልተደረገበት፣ በሕንጻ ላይ የተያያዘውን እሳት ለማጥፋት የሚከብደውን ያህል ለማጥፋት ከባድ ነው። ወደዚህ አክራሪነት የገቡና የደገፉ ሰዎች (ቅዱስ ሥጋ) በሚከተሉት ተለዋዋጭነት ባለው ድርጊታቸው እግዚአብሔርን እያዋረዱና የእርሱን ሕዝብ አደጋ ውስጥ እየጣሉ ስለሆነ ከዚህ ይልቅ በዓለማዊ ሥራ ላይ ቢሰማሩ እጅግ ይሻላል። የእግዚአብሔር ሥራ ከፍ ብሎ፣ ንጹህ ሆኖ፣ ከጥንቆላና ከአፈ-ታሪኮች ጋር ሳይበረዝ መቆም ባለበት በዚህ ወቅት ብዙ የዚህ ዓይነት እንቅስቃሴዎች ይነሳሉ። በሰይጣን መሳሪያዎች እንዳንጠመድ ከክርስቶስ ጋር ያለንን የቀረበ ግንኙነት ለማቆየት ራሳችንን መጠበቅ ያስፈልገናል።--GCB, Apr 23, 1901. (2SM 35.) {1MCP 43.1}1MCPAmh 38.2

  አእምሮን የሚሞሉ በጥንቃቄ የተዘጋጁ መላምቶች።-- ሰይጣን መልእክቱን መስበክ ያለባቸው ሰዎች አእምሮዎች በጣም አስፈላጊ በሚመስሉ በብልጠት በተዘጋጁ መላምቶች እንዲያዙና ሙሉ በሙሉ እንዲሞሉ ለማድረግ በብዙ መንገዶች እየሰራ ነው፤ በልምምዳቸው አስደናቂ እርምጃዎችን እየተራመዱ እንደሆኑ እያሰቡ ሳለ ጥቂት አሳቦችን ጣዖት በማድረጋቸው የሚያሳድሩት ተጽእኖ ስለሚጎዳ ተጽእኖአቸው ስለ ጌታ የሚናገረው በጣም ጥቂት ይሆናል።{1MCP 43.2}1MCPAmh 38.3

  እያንዳንዱ አገልጋይ የክርስቶስ አእምሮ ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ ልባዊ ጥረት ያድርግ። ከእግዚአብሔር ቃልና ከምስክሮች ውስጥ ከራሳቸው ሀሳቦች ጋር እንዲገጥሙ ተደርገው ትርጉም የተሰጣቸውን አንቀጾችንና አረፍተ ነገሮችን ነቅሰው እያወጡ እግዚአብሔር ሳይመራቸው በእነዚህ ሀሳቦች ላይ የሚያተኩሩና በራሳቸው አቋም ላይ ራሳቸውን የሚያንጹ ሰዎች አሉ። ይህ ሁሉ ጠላትን ያስደስተዋል። አስፈላጊ ያልሆኑ ልዩነቶችን ወይም ጠብን የሚፈጥረውን መንገድ መከተል የለብንም። ሰዎች የእኛን ሀሳብ የማይከተሉት አገልጋዮች ነገሮችን የመገንዘብ ችግር ስላለባቸው ነው የሚል ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ የለብንም።{1MCP 43.3}1MCPAmh 38.4

  በክርስቶስ ትምህርቶች ውስጥ መናገር የምትችልባቸውና አንተም ሆንክ አድማጮችህ ማስተዋልም ሆነ ማብራራት ስለማይችሏቸው የሚተውአቸው ጉዳዮችና ምስጢሮች በብዛት አሉ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንዲያስተምርህ ቦታ ስጥ፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ አማካይነት አስደናቂ የሆነውን የድነት እቅድ ለአእምሮህ እንዲከፍት ፍቀድለት። --MS 111, 1894. {1MCP 43.4}1MCPAmh 39.1

  ከአሉታዊ አቅጣጫ ተመለስ (ለአገልጋይ የተሰጠ ምክር)፡- ሁል ጊዜ አሉታዊ ጎንን የመያዝን ውጤት ማየት ብትችል ኖሮ፣ ይብዛም ይነስም ለዓመታት እንዳደረግከው፣ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 18 ላይ ተመዝግበው ያሉትን የአዳኙን ቃላት በተሻለ ሁኔታ ታስተውል ነበር። ደቀ መዛሙርቱ የሚከተለውን ጥያቄ ይዘው ወደ ኢየሱስ መጡ፡- ‹‹በእግዚአብሔር መንግስት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው? ኢየሱስም ትንሽ ልጅ ወደ እርሱ እንዲመጣ ጠርቶ በመካከላቸው አቆመና እንዲህ አላቸው፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ካልተለወጣችሁና እንደ ትንሽ ሕፃን ካልሆናችሁ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት አትገቡም። እንደዚህ ትንሽ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ እርሱ በሰማይ መንግስት ከሁሉ ይበልጣል። የዚህን ዓይነት ትንሽ ልጅ በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል። በእኔ ከሚያምኑ ከእነዚህ ከትናንሾቹ አንዱን የሚያስቀይም ማንም ቢኖር በአንገቱ የድንጋይ ወፍጮ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለዋል። ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፣ ነገር ግን በእርሱ ምክንያት ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት! ›› (ማቴ. 18፡ 1-7) ። {1MCP 44.1}1MCPAmh 39.2

  ወንድሜ ሆይ፣ ክፉ አሳብን ሁሉ አውጥተህ ጣል። በእግዚአብሔር ፊት ልብህን ትሁት አድርግ። ያኔ ዓይኖችህ ስለሚከፈቱ በአሉታዊ ወገን በፍጹም አትቆምም። ‹‹እጅህ ወይም እግርህ ቢያሰናክልህ ቁረጥና ጣል፡-ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከመጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጉንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል›› (ማቴ 18፡8) ። ይህን ማድረግ ለሰብአዊ ተፈጥሮ እጅግ የሚያም ቢሆንም ጉድለት ያለባቸውን ባሕርያትህን ቁረጣቸው። አንድን ነገር አይታ ለመተቸትም ሆነ ለመቃወም እጅግ የምትቸኩለው ‹‹ዓይንህ ብታሰናክልህ ከአንተ አውጥተህ ጣላት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።›› (ቁጥር 9) ። --Lt 93, 1901. {1MCP 44.2}1MCPAmh 39.3

  እምነት አሉታዊነትን ያሸንፋል።---የእግዚአብሔርን ሥራ አውቀን ለመሥራት ወስነን በእምነት ወደ ፊት ከተጓዝን ስኬትን እናገኛለን። እምነት የለሽ ሆነው በአሉታዊ ወገን ለመቆም የሚወዱ ሰዎች እንቅፋት እንዲሆኑብን መፍቀድ የለብንም። የእግዚአብሔር ሚስዮናዊ ሥራ ብዙ እምነት ባላቸው ሰዎች ወደ ፊት እየሄደ ባለማቋረጥ ኃይሉና ብቃቱ እየጨመረ መሄድ አለበት። --Lt 233, 1904. {1MCP 44.3}1MCPAmh 40.1

  በግል ጥገኛ ያለመሆን አደጋ: -በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለማቋረጥ በግላቸው ጥገኛ ወደ አለመሆን የሚያዘነብሉ ሰዎች ሁል ጊዜም ነበሩ። በመንፈስ ጥገኛ አለመሆን ሰብአዊ ወኪል ምክርን ከማክበርና ለወንድሞች ውሳኔ፣ በተለይም ሕዝቡን እንዲመሩ እግዚአብሔር በሀላፊነት ላይ ያስቀመጣቸው ሰዎች ለሚሰጡት ምክር፣ ከፍ ያለ ቦታ ከመስጠት ይልቅ ከመጠን በላይ በራሱ እንዲተማመንና የራሱን ውሳኔዎች እንዲያምናቸው እንደሚያደርገው መረዳት ያቃታቸው ይመስላል።ማንም ሰው ባያከብርና ቢንቅ ሊጸድቅ የማይችለውን ሥልጣንና ኃይል እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ ሰጥቶአል፣ የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣንና ኃይል የሚንቅ የእግዚአብሔርን ድምጽ ይንቃል። --AA 163, 164 (1911). {1MCP 45.1}1MCPAmh 40.2

  የዋህነትን በመንከባከብ የሚገኝ ሰላም።--ነፍስ እረፍት የምታገኘው የዋህነትንና የልብ ትህትናን በመንከባከብ ብቻ ነው። ራስ ወዳድነት በነገሰበት ቦታ የክርስቶስ ሰላም በፍጹም አይገኝም። ነፍስ ራስ ወዳድና ትዕቢተኛ ከሆነች በጸጋ ማደግ አትችልም። የክርስቶስ ሰላም በልብ ውስጥ እንዲኖር ኢየሱስ የሰውን ቦታ ወሰደ። ደቀ መዛሙርቱ ለመሆን ራሳቸውን ለክርስቶስ የሰጡ ሰዎች በየዕለቱ ራሳቸውን መካድ፣ መስቀልን ተሸክመው የኢየሱስን ዱካ መከተል አለባቸው። የእርሱ ምሳሌነት ወደሚመራቸው ቦታ መሄድ አለባቸው። --Lt 28, 1888. {1MCP 45.2}1MCPAmh 40.3

  የክርስቲያናዊ ትህትና መልካም ባሕርይ።-ጳውሎስ ለመርህ እንደ ዓለት ጽኑ ቢሆንም የትህትና ባሕርይን ሁል ጊዜ ያሳይ ነበር። ወሳኝ በሆኑ ነጥቦች ላይ ቀናተኛ ቢሆንም ከማህበራዊ ኑሮ አንጻር ጸጋንና ትህትናን የሚንቅ ሰው አልነበረም። የእግዚአብሔር ሰው ሰብአዊነትን አልሸፈነውም (አልዋጠውም)።--Lt 25, 1870. (HC 236.) {1MCP 45.3}1MCPAmh 40.4

  አንዳንድ ሰዎች የሌሎችን ስሜት በሚያቆስል መልኩ የጭካኔና ትህትና የጎደለውን ንግግር ከተናገሩ በኋላ ለንግግራቸው እንዲህ በማለት ምክንያት ይሰጣሉ፡- ‹‹ንግግሬ እንደዚህ ነው፤ ሁል ጊዜ ያሰብኩትን ነገር በግልጽ እናገራለሁ››፤ ይህን ክፉ የሆነ ባሕርይ እንደ መልካም ባሕርይ ከፍ ከፍ ያደርጉታል። ይህ ትህትና የጎደለው ባሕርያቸው በጽኑ መገሰጽ አለበት።--RH, Sept 1, 1885. (HC 229.) {1MCP 45.4}1MCPAmh 40.5

  የመጽሐፉ ደራሲ የአክራሪነትን እያንዳንዱን ክፍል እንድንጋፈጥ ጥሪ አቅርባለች።--በ1844 ዓ.ም አክራርነትን በሁሉም አቅጣጫ እንጋፈጥ ነበር፣ ነገር ግን ሁል ጊዜ ቃል ይመጣልኝ ነበር፡- ትልቅ የመነሳሳት ማዕበል ለሥራው ጉዳት የሚያስከትል ነው። እግሮቻችሁ የክርስቶስን ፈለግ ይከተሉ። እያንዳንዱን የአክራሪነት ማዕበል ደረጃ በደረጃ እንድንጋፈጥ መልእክት ተሰጥቶኝ ነበር። በዚህ የመነሳሳት ማዕበል ሥር እንግዳ የሆነ ሥራ እንደሚሰራ ለሕዝቡ እንድነግር መመሪያ ተሰጥቶኝ ነበር። ጥንቆላን ለማስገባት አጋጣሚውን የሚጠቀሙ ሰዎች አሉ። ከዚህ የተነሣ ትክክለኛ የሆነ አስተምህሮን ለማወጅ በሩ ተዘግቶ ነበር። --Lt 17, 1902. {1MCP 46.1}1MCPAmh 41.1

  የማይቀረው አደጋ።--መጨረሻው ሲቃረብ በመካከላችን አክራሪነትን ለማስገባት ጠላት ባለው ኃይሉ ሁሉ ይሰራል። ዓለም ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችን የአክራሪዎች ቡድን ናቸው ብሎ እስከሚጠራቸው ድረስ ወደ ጫፍ ወጥተው ሲያይ ደስ ይለዋል። ይህን አደጋ በተመለከተ አገልጋዮችንና ወንጌልን በፈቃዳቸው የሚሰሩ ሰዎችን እንዳስጠነቅቅ ታዝዣለሁ። የእኛ ሥራ ወንዶችና ሴቶች በእውነተኛ መሰረት ላይ እንዲገነቡ፣ እግሮቻቸውንም ግልጽ በሆነው ‹‹እግዚአብሔር እንዲህ ይላል›› በሚለው ቃል ላይ እንዲመሰርቱ ማስተማር ነው። --GW 316 (1915). {1MCP 46.2}1MCPAmh 41.2

  አእምሮን መቆጣጠር አንዱ የአክራሪነት ዓይነት።--አንድ ሰው ሌላ ሰው እንዲቆጣጠረው አእምሮውን ይተዋል የሚለውን አደገኛ ሳይንስ በተመለከተ በግልጽ ተናግሬያለሁ። ይህ ሳይንስ የራሱ የሰይጣን ሳይንስ ነው። {1MCP 46.3}1MCPAmh 41.3

  ይህ በ1845 ዓ.ም ያጋጠመን የአክራሪነት ባሕርይ ነው። በዚያን ጊዜ ምን ማለት እንደሆነ አላወቅኩም ነበር፣ ነገር ግን ማንኛውንም የዚህን ዓይነት ነገር በመቃወም ጽኑ የሆነ ምስክርነት እንዳስተላልፍ ተጠርቼ ነበር። --Lt 130 1/2, 1901. {1MCP 46.4}1MCPAmh 41.4

  ሚዛናዊ የሆነ አዎንታዊ አመለካከትን አሳድጉ።--ዓይኖቻችንን በስህተት ላይ ለመትከል፣ ለማዘንና ለማጉረምረም፣ እንዲሁም የሌሎችን ስህተቶች እያነሳን ለማላዘን ምክንያት የለም። ከዚህ ይልቅ ሚዛናዊ አመለካከትን በመያዝ ምን ያህል ነፍሳት በመክሊቶቻቸው (በሀብታቸውና በችሎታቸው) እግዚአብሔርን እያገለገሉ፣ ፈተናን እየተቋቋሙ፣ እርሱን እያከበሩና ከፍ ከፍ እያደረጉ እንደሆነ መመልከት እግዚአብሔርን የበለጠ አያስደስተውምን? ምስኪንና የተዋረዱ ኃጢአተኞችን፣ በግብረገብ ብክለት የተሞሉትን፣ ለውጦ በባሕርያቸው ክርስቶስን እንዲመስሉ የሚያደርገውን አስደናቂና ተአምር ሰሪ የሆነውን የእግዚአብሔርን ኃይል ከግምት ውስጥ ማስገባት አይሻልምን? --Lt 63, 1893. (HC 248.) {1MCP 46.5}1MCPAmh 41.5

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents