Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First

  ምዕራፍ 36—አንድን ነገር ለማድረግ የመፈለግ መርሆዎች

  ስኬት ዓላማን ይሻል።--በማንኛውም ዘርፍ ቢሆን ስኬት ግልጽ የሆነ ዓላማን ይሻል። በሕይወቱ እውነተኛ ስኬትን ማግኘት የሚፈልግ ሰው የሚያደርገው ጥረት ከዓላማው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ያለው መሆኑን ያለማቋረጥ በዕይታው ውስጥ ማድረግ አለበት። በዛሬዎቹ ወጣቶች ፊት የዚህ ዓይነት ዓላማ ተቀምጦአል።--Ed 262 (1903). {1MCP 341.1}1MCPAmh 277.2

  እስከሚቻል ድረስ ከፍ አድርጎ ማለም ያስፈልጋል።--በሕይወት ውስጥ የተመደበልን የተለየ ቦታ የሚወሰነው በችሎታዎቻችን ነው። ሁሉም ተመሳሳይ የእድገት ደረጃ ላይ መድረስ ወይም ተመሳሳይ የሆነ ሥራን እኩል በሆነ ብቃት መሥራት አይችሉም። እግዚአብሔር የሒሶጵ ተክል የሊባኖስን ዛፍ ያህል እንዲያድግ ወይም ወይራ የግዙፉን የዘንባባ ዛፍ ከፍታ እንዲደርስ አይጠብቅበትም። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ሰብአዊ ፍጡር ከመለኮት ጋር ሕብረት ሲፈጥር እንዲደርስ ከሚያስችለው ከፍታ ላይ ለመድረስ ያልም። --Ed 267 (1903). {1MCP 341.2}1MCPAmh 277.3

  ተማሪዎች እርግጠኛ የሆነ ዓላማ ሊኖራቸው ይገባል።--ተማሪዎች በዚህ ዓለም ከሁሉ የበለጠ መልካም ነገር ማድረግ እንዲችሉ እግዚአብሔር የሰጣቸውን መክሊቶች እጅግ ከፍ ላለና ቅዱስ ዓላማ እንዲጠቀሙ አስተምሩአቸው። ተማሪዎች በሕይወት እርግጠኛ የሆነ ዓላማ ባለቤት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና እውነተኛ ትምህርት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከፍ ያለ መረዳት እንዲኖራቸው መማር ያስፈልጋቸዋል። --SpT Series B, No. 11, p 16, Nov 14, 1905. {1MCP 341.3}1MCPAmh 277.4

  ክርስቶስ ከፍ ያሉ ዓላማዎችን ያደፋፍራል።--እርሱ እጅግ ከፍ ላሉ ዓላማዎቻችን ማበረታቻን፣ እጅግ ምርጥ ለሆነው ሀብታችን ደህንነትን ይሰጣል። --COL 374 (1900). {1MCP 342.1}1MCPAmh 278.1

  አንድ ሰው ያለውን አቅም መገንዘብ አለመቻል።--ብዙዎች መሆን ያለባቸውን የማይሆኑበት ምክንያት በውስጣቸው ያለውን ኃይል ሥራ ላይ ስለማያውሉት ነው። መለኮታዊ ብርታትን መያዝ የሚገባቸውን ያህል አጥብቀው አይይዙም። ብዙዎች ወደ እውነተኛው ስኬት ከሚደርሱበት መስመር ወጥተዋል። ከፍ ያለ ክብርን ወይም የበለጠውን የሚያስደስት ሥራ በመፈለግ እነርሱ ገጣሚ ያልሆኑለትን ነገር ለማድረግ ይሞክራሉ። {1MCP 342.2}1MCPAmh 278.2

  መክሊቶቻቸው ለሌላ ጥሪ ገጣሚ የሆኑ ብዙ ሰዎች ገጣሚ ወደማይሆኑበት ሥራ ለመግባት ጉጉት አላቸው፤ገበሬ፣ የዕደ ጥበብ ሰራተኛ ወይም ነርስ ቢሆን ኖሮ የተሳካለት መሆን የሚችል ሰው በቂ ባልሆነ ሁኔታ የአገልጋይን፣ የጠበቃን ወይም የሐኪምን ቦታ ይይዛል። ሌሎች ደግሞ ኃላፊነትን የሚጠይቅ ክፍተትን መሙላት የሚችሉ ሆነው ሳለ ጉልበትን፣ ተግባራዊነትን ወይም ትዕግስትን ስላጡ ቀለል ያለ ቦታን በመያዛቸው ረክተው የሚቀመጡ አሉ።--Ed 267 (1903). {1MCP 342.3}1MCPAmh 278.3

  በሕይወት ውስጥ ያሉ ታላላቅ አጋጣሚዎች።--የሕይወት አጋጣሚዎችን በተመለከተ ምን ትልቅ እንደሆነና ምን ትንሽ እንደሆነ መወሰን የሚችል ማን ነው? ዓለምን ለመባረክ ወኪሎችን በማስቀመጥ በሕይወት ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ በመስራት ነገስታትን ሊያስቀኑ የሚችሉ ውጤቶችን ያገኙ ሰዎች ምንኛ ብዙ ናቸው! --Ed 266 (1903). {1MCP 342.4}1MCPAmh 278.4

  “የተሻለ ነገር”--የእውነተኛ ኑሮ ሕግ።--‹‹የተሻለ ነገር›› የሚለው አባባል የትምህርት መሪ ቃል፣ የሁሉም እውነተኛ ሕይወት ሕግ ነው። ክርስቶስ ማንኛውንም ነገር እንድንክድ ሲጠይቀን በእርሱ ፈንታ የተሻለ ነገር ይሰጠናል። {1MCP 342.5}1MCPAmh 278.5

  ብዙ ጊዜ ወጣቶች ክፉ መስለው የማይታዩ ነገር ግን ከፍተኛ ከሆነ የመልካምነት መስፈርት የሚጎድሉ ዓላማዎችን፣ ፍላጎቶችንና ደስታዎችን ይንከባከባሉ። ሕይወትን ከከበረ ዓላማ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይመልሱታል። የዘፈቀደ እርምጃዎች ወይም ቀጥተኛ ትችት ወጣቶች እንደ ውድ ነገር አድርገው የያዙትን ነገር ወደመተው ላይመራቸው ይችላል። ከታይታ፣ ከፍላጎት ወይም የራስን ፍላጎት ከማሟላት ወደ ተሻለ ነገር ይመሩ። ከእውነተኛ ውበት፣ እጅግ ከፍ ካሉ መርሆዎችና የከበረ ሕይወት ጋር አገናኙአቸው። ‹‹ሙሉ በሙሉ አስደሳች›› የሆነውን እንዲመለከቱ ምሩአቸው። {1MCP 342.6}1MCPAmh 278.6

  አንዴ እይታ በእርሱ ላይ ካተኮረ ሕይወት ማዕከሉን ያገኛል። የወጣቶች አንድን ነገር የማድረግ ኃይለኛ ፍላጎት፣ ልግስና ያለበት መሰጠት፣ ስሜት ያለበት ግለት በዚህ ቦታ እውነተኛ ዓላማቸውን ያገኛሉ። ክርስቶስን ማክበር፣ እንደ እርሱ መሆን፣ ለእርሱ መስራት፣ የሕይወት ከፍተኛው ፍላጎትና ትልቅ ደስታ ነው።--Ed 296, 297 (1903). {1MCP 343.1}1MCPAmh 279.1

  እድገት ለማሳየት እጅግ ከፍ ያሉ ማነሳሻዎችን ፍጠሩ።--ነርሶችና ሀኪሞች ለመሆን እየሰለጠኑ ያሉ ሰዎች እድገት ለማሳየት ከፍተኛ ማነሳሻ የሚፈጥሩትን ትምህርቶች በየዕለቱ ማግኘት አለባቸው። በኮሌጆቻችንና በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶቻችን መማር አለባቸው፤ በእነዚህ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ መምህራን ከተማሪዎች ጋር አብሮ የመስራትና የመጸለይ ሀላፊነት እንዳለባቸው መገንዘብ አለባቸው። በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከወንጌል አገልግሎት ጋር በጽኑ የተሳሰሩ እውነተኛ የሕክምና ሚስዮናውያን ለመሆን መማር አለባቸው። --SpT Series B, No. 11, p 12, Nov 14, 1905. {1MCP 343.2}1MCPAmh 279.2

  የሞኙ ሀብታም ሰው ራስ ወዳድ ዓላማ ቢስነት።--የዚህ ሰው ዓላማዎች ከሚጠፉ እንስሳት ዓላማዎች ከፍ ያሉ አይደሉም። የኖረው እግዚአብሔርና ሰማይ፣ የወደፊት ሕይወት እንደሌለ አድርጎ ነው፤ የነበረው ነገር ሁሉ የራሱ እንደሆነና ለእግዚአብሔር ወይም ለሰው መመለስ ያለበት ምንም እዳ እንደሌለበት አድርጎ ኖረ። ባለመዝሙሩ ይህን ሀብታም ሰው እንደሚከተለው በመጻፍ ገልፆታል፡- ‹‹ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል።›› --COL 257, 258 (1900). {1MCP 343.3}1MCPAmh 279.3

  ዓላማ የሌለው ሕይወት መኖር በሕይወት መሞት ነው።--ዓላማ የሌለው ሕይወት መኖር በሕይወት እያሉ መሞት ነው። አእምሮ ከዘላለማዊ ፍላጎቶች ጋር ግንኙነት ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማረፍ አለበት። ይህ ለአካልና ለአእምሮ ጤና ተስማሚ ይሆናል። --RH, July 29, 1884. (CH 51.) {1MCP 343.4}1MCPAmh 279.4

  በዓላማ ቢስነት ላይ ሻጋታ (ፈንገስ) ይበቅልበታል። ከአእምሮ ብቃት ማነስና ከግብረገብ ድክመት ዋና መንስኤዎች አንዱ ውጤታቸው ጥሩ በሆኑ ነገሮች ላይ ትኩረት ማጣት ነው። ስነ-ጽሁፍ በሰፊው በመሰራጨቱ እንኩራራለን፤ ነገር ግን የመጽሐፍት መባዛት፣ በራሳቸው ጎጂ ያልሆኑ መጻሕፍት እንኳን ቢሆኑ፣ አዎንታዊ ክፋት ሊሆኑ ይችላሉ።. . . {1MCP 343.5}1MCPAmh 279.5

  እንደ ግብጽ እንቁራርቶች በምድሪቱ እየተሰራጩ ካሉ ወቅታዊ መጽሔቶችና መጻሕፍት መካከል አብዛኞቹ ተራ፣ መሰረተ ቢስ፣ እና አድካሚ ብቻ ሳይሆኑ እርኩስና የሚያዋርዱ ናቸው። ውጤታቸውም አእምሮን ማስከርና ማበላሸት ብቻ ሳይሆን ነፍስን ማበላሸትና ማጥፋትም ነው። {1MCP 344.1}1MCPAmh 280.1

  ሰነፍና ዓላማ ቢስ የሆነ አእምሮ፣ ልብ፣ በቀላሉ የክፉ ሲሳይ ይሆናል። ሻጋታ የሚያድገው በታመሙ፣ ሕይወት በሌላቸው እንስሳትና እጽዋት ላይ ነው። ሥራ ፈት አእምሮ የሰይጣን የሥራ ቦታ ነው። አእምሮ እንዲሆን ወደሚፈለግበት ከፍ ወዳሉና ቅዱስ ነገሮች ከተመራ፣ ሕይወት የከበረና የሚመስጥ ዓላማ ካለው፣ ክፋት መቆሚያ ያጣል። --Ed 189, 190 (1903). {1MCP 344.2}1MCPAmh 280.2

  ዓላማ ቢስነት መሻትን ላለመግዛት የሚያጋልጥ ነገር ነው።--መሻትን ያለመግዛት መንስኤ ምን እንደሆነ መድረስ ከፈለግን አስካሪ መጠጥ ከመጠጣት ወይም ትንባሆ ከመጠቀም ጠለቅ ብለን መሄድ አለብን። ሥራ ፈትነት፣ ዓላማ ቢስነት፣ ወይም ክፉ ግንኙነቶች ለዚህ የሚያጋልጡ ነገሮች ናቸው። --Ed 202, 203 (1903). {1MCP 344.3}1MCPAmh 280.3

  ጥቂት ክፋቶች እጅግ መፈራት አለባቸው።-- ከስንፍናና ከዓላማ ቢስነት ይልቅ ጥቂት ክፋቶች በጣም መፈራት አለባቸው። ሆኖም በልባቸው የወጣቶች ደህንነት ላላቸው ሰዎች የአብዛኞቹ የአትሌቲክስ እስፖርቶች ዝንባሌ የሚያስጨንቅ ሀሳብ ነው።--የደስታንና የፍንደቃን ስሜት ስለሚቀሰቅሱ ጠቃሚ ለሆነ ሥራ ፍላጎት ማጣትንና ተግባራዊ የሆኑ ሥራዎችንና ሀላፊነቶችን መሸሽን ያስከትላሉ። ለከበሩ የሕይወት እውነታዎች ያለውን ፍላጎት ወደማጥፋት ያዘነብላሉ። ከዚህ የተነሣ ከንቱ ለሆነ ሕይወትና ለህገ-ወጥነት አስከፊ ከሆኑ ውጤቶቻቸው ጋር በር ይከፈታል። --Ed 210, 211 (1903). {1MCP 344.4}1MCPAmh 280.4

  ማንም ዓላማ ቢስ ሕይወት መኖር የለበትም።--እያንዳንዱ ነፍስ መመስከር አለበት። ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ መስራት እንዲችል በመንፈስ ቅዱስ መቀደስና የአካል፣ የግብረገብና የአእምሮ ኃይሎችን መጠቀም አለበት። ሁሉም በንቃትና ባለመቆጠብ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ራሳቸውን ቀድሰው መስጠት አለባቸው። ሌሎችን በመርዳት ታላቅ ሥራ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መተባበር አለባቸው። ክርስቶስ የሞተው ለእያንዳንዱ ሰው ነው። ሕይወቱን በመስቀል ላይ አሳልፎ በመስጠት እያንዳንዱን ሰው ዋጅቶአል። ይህን ያደረገው ሰው ዓላማ የለሽና ራስ ወዳድ የሆነ ኑሮን በመተው ለድነቱ ለሞተለት ለኢየሱስ ክርስቶስ እንዲኖር ነው። ሁሉም ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ባይጠሩም ማገልገል አለባቸው። ማንኛውም ሰው ቢሆን ራስን የማገልገል ሕይወት ሲመርጥ የእግዚአብሔርን ቅዱስ መንፈስ መሳደብ ነው። --Lt 10, 1897. (4BC 1159.) {1MCP 344.5}1MCPAmh 280.5

  አንድን ነገር የማድረግ ትክክለኛ ፍላጎቶችን ማሳደግ ያስፈልጋል። እውነተኛ የሆኑ የአገልግሎት ምክንያቶች በሽማግሌዎችና በወጣቶች ፊት መቀመጥ አለባቸው። ተማሪዎች ጠቃሚ ወደ ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ማደግ በሚችሉበት መንገድ መማር አለባቸው። እነርሱን ከፍ ያሉና የከበሩ እንዲሆኑ የሚያደርግ እያንዳንዱ ዘዴ ጥቅም ላይ መዋል አለበት። ኃይሎቻቸውን በተሻለ ሁኔታ መጠቀም እንዲችሉ መማር አለባቸው። የአካልና የአእምሮ ኃይሎች እኩል በሥራ መጠመድ አለባቸው። የሥርዓትና የእርምት ልማዶች ማደግ አለባቸው። በንጹህና እውነተኛ ሕይወት ሥራ ላይ የዋለ ኃይል በተማሪዎች ፊት መቀመጥ አለበት። ይህ ጠቃሚ ለሆነ አገልግሎት በሚያደርጉት ዝግጅት ይረዳቸዋል። በየቀኑ ንጹህና ብርቱ ሆነው፣ ክፉን ለመቃወም ከፍተኛ ጥረት ለማድረግ በደንብ ተዘጋጅተው፣ በእርሱ ጸጋና በቃሉ ጥናት ያድጋሉ። --RH, Aug 22, 1912. (FE 543.) {1MCP 345.1}1MCPAmh 281.1

  ተግባሮች አንድን ነገር የማድረግ ማነሳሻዎችን ይገልጣሉ።--ተግባሮች መርሆዎችንና አንድን ነገር የማድረግ ምክንያቶችን ይገልጣሉ። በእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ ውስጥ ያሉ ተክሎች እንደሆኑ የሚናገሩ ሰዎች የሚያፈሩት ፍሬ እሾክና አሜካላ እንደሆነ ያሳያል። አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባላት የሚሄዱበትን የስህተት መንገድ ትክክል እንደሆነ መላው ቤተ ክርስቲያን ሊያጸድቅ ይችላል፣ ነገር ግን ይህ ማረጋገጫ ስህተት ትክክል እንደሆነ አያረጋግጥም። የእሾህን ፍሬዎች የወይን ማድረግ አይችልም።--5T 103 (1882). {1MCP 345.2}1MCPAmh 281.2

  የሚፈረደው ውጫዊው እይታ ሳይሆን አንድን ነገር ለማድረግ ያነሳሳው ነገር ነው።-- ሁሉም ከእለት ወደ እለት ጠቅለል ያለ ባሕርያቸውን እና ድርጊታቸውን ካነሳሱ ምክንያቶች ጋር መተዋወቅ አስፈላጊ ሥራ ነው። ልዩ የሆኑ ተግባሮችን ከሚያነሳሱ የተለዩ ምክንያቶችች ጋር መተዋወቅ አለባቸው። እያንዳንዱ የህይወታቸው ድርጊት የሚፈረደው በውጫዊ እይታ ሳይሆን ያን ድርጊት እንዲፈጸም ባደረገው ማነሳሻ ነው። --3T 507 (1875). {1MCP 345.3}1MCPAmh 281.3

  የክርስቶስ ተከታዮች አዲስ ማነሳሻዎን ያገኛሉ።--በተማሪዎች ሕይወት የእግዚአብሔርን ባህርይ ከሚያሳድግ ሳይንስ ጋር ማንኛውም ሳይንስ ሊስተካከል አይችልም። የክርስቶስ ተከታዮች የሚሆኑ ሰዎች አዳዲስ የተግባር ማነሳሻዎች እንደሚሰጡ፣ አዳዲስ አስተሳሰቦች እንደሚነሱ፣ እና አዳዲስ ተግባሮች መፈተን እንዳለባቸው ያውቃሉ። ነገር ግን ነፍስ እንድትጠራጠርና ኃጢአት እንድትሰራ ለማድረግ ፈተናዎችን በማቅረብ ሁል ጊዜ የሚታገላቸው ጠላት ስላለ ወደ ፊት መጓዝ የሚችሉት በተቃርኖ ውስጥ ብቻ ነው። መሸነፍ ያለባቸው በውርስ የተገኙና ያሳደግናቸው የክፉ ዝንባሌዎች አሉ። የምግብ ፍላጎትና የፍቅር ስሜት በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር መሆን አለበት። ከዘላለም በዚህኛው ወገን ለሚደረገው ጦርነት መጨረሻ የለውም። ነገር ግን ያለማቋረጥ መዋጋት የሚያስፈልጉ ጦርነቶች ቢኖሩም መገኘት ያለባቸው የከበሩ ድሎችም አሉ፤ በራስና በኃጢአት ላይ የሚገኝ ድል አእምሮ ማሰብ ከሚችለው በላይ ትልቅ ዋጋ አለው። --CT 20 (1913). {1MCP 346.1}1MCPAmh 281.4

  ሁለት እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ የማነሳሻ ኃይሎች።--መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ ገላጭ ነው። ጥቅስ ከጥቅስ ጋር መነጻጸር አለበት። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ቃሉን እንደ አንድ ሙሉ ነገር ለመመልከትና ክፍሎቹ ከእርስ በርስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማየት መማር አለበት። ስለ ቃሉ የተከበረ ማዕከላዊ መልእክት፣ እግዚአብሔር ለዓለም ስላለው የመጀመሪያ ዓላማ፣ ስለ ታላቁ ተጋድሎ መነሳት እና ስለ መበዤት ሥራ እውቀት ማግኘት አለበት። የበላይነትን ለማግኘት እየተፎካከሩ ያሉ የሁለቱን መርሆዎች ባህርይ ማስተዋልና እስከ ታላቁ ፍጻሜ ድረስ የእነርሱን አሰራር በታሪክና በትንቢት አማካይነት ማፈላለግን መማር አለበት። ይህ ተጋድሎ ወደ እያንዳንዱ ሰብአዊ ልምምድ ምዕራፍ እንዴት እንደሚገባ፣ በእያንዳንዱ የህይወት ተግባር እርሱ ራሱ ከሁለቱ የማይስማሙ ምክንያቶች መካከል አንዱን ወይም ሁለቱንም እንዴት እንደሚያሳይ፣ እና ፈቃደኛ ቢሆንም ባይሆንም በተጋድሎው በየትኛው ወገን እንደሚገኝ እንዴት አሁን እየወሰነ እንደሆነ ማየት አለበት።--Ed 190 (1903).{1MCP 346.2}1MCPAmh 282.1

  እያንዳንዱ ተግባር መንታ ባሕርይ አለው።--እያንዳንዱ የተግባር መንገድ መንታ ባህርይና ጠቀሜታ አለው። እንደሚያነሳሳው ማነሳሻ ምክንያት መልካም ወይም በተንኮል የተሞላ፣ ትክክል ወይም ስህተት ሊሆን ይችላል። የስህተት ተግባር፣ ቶሎ ቶሎ ሲደጋገም፣ በተዋንያኑ አእምሮና በማንኛውም መንገድ፣ መንፈሳዊ ቢሆን ወይም ዓለማዊ፣ ከእርሱ ጋር ግንኙነት ካላቸው ሰዎች አእምሮዎች ላይ ቋሚ የሆነ አሻራ ይተዋል። ትክክል ላልሆኑ ትናንሽ ተግባሮች ትኩረት የማይሰጡ ወላጆች ወይም መምህራን እነዚያን ልማዶች በወጣቶች ውስጥ ይመሰርታሉ።--RH, May 17, 1898. (CG 201.) {1MCP 347.1}1MCPAmh 282.2

  ተግባር ጥሩነትን ከማነሳሻ ያገኛል።--እያንዳንዱ ተግባር ከሚገፋፋው ማነሳሻ ችሎታን ስለሚያገኝ ማነሳሻዎቹ ከፍ ያሉ፣ ንጹህና ራስ ወዳድነት የሌለባቸው ካልሆኑ በስተቀር አእምሮና ባህርይ በፍጹም ሚዛናቸውን የጠበቁ አይሆኑም።--YI, Apr 7, 1898. (SD 171.) {1MCP 347.2}1MCPAmh 282.3

  ማነሳሻዎች ለተግባሮቻችን ባህርይ ይሰጣሉ።--በላያቸው አሳፋሪ የሆነ ነገርን ወይም ከፍ ያለ የግብረገብ ብቃትን በማተም ለተግባሮቻችን ባሕርይ የሚያላብሰው የአንድ ነገር ማነሳሻ ነው። እያንዳንዱ ዓይን የሚያያቸውንና እያንዳንዱ ምላስ የሚያወድሳቸውን ታላላቅ ነገሮች እግዚአብሔር እጅግ እንደከበሩ ነገሮች አይቆጥራቸውም። በደስታ የሚሰሩ ትናንሽ ተግባሮች፣ ታይታ የሌለባቸው ትናንሽ ስጦታዎች እና ለሰብአዊ አእምሮ ዋጋ ቢስ የሚመስሉ ነገሮች ብዙ ጊዜ በእርሱ ፊት ከፍ ብለው ይታያሉ። ለእግዚአብሔር የእምነትና የፍቅር ልብ እጅግ ውድ ከሆነ ስጦታ ይልቅ የከበረ ነው። ደሃዋ ባልቴት ማድረግ የቻለችውን ትንሽ ነገር ለማድረግ መተዳደሪያዋን ሁሉ ሰጠች። እነዚያን ሁለት ሳንቲሞች ለወደደችው ሥራ ለመስጠት ለራስዋ ምግብ ነፈገች። ሰማያዊ አባትዋ ታላቁን ፍላጎቷን ችላ እንደማይል በማመን በእምነት አደረገች። የአዳኙን ሙገሳ ያተረፈው ይህ ራስ ወዳድነት የሌለው መንፈስና የልጅ መሰል እምነት ነው። --DA 615 (1898). {1MCP 347.3}1MCPAmh 283.1

  እግዚአብሔር አንድን ነገር የምናደርግበትን ምክንያቶች ይገልጣል።--እግዚአብሔር ደረጃ በደረጃ ሕዝቡን ወደ ፊት ይመራል። የልባቸውን ሀሳቦች እንዲገልጡ ወደተሰሉ ቦታዎች ያመጣቸዋል። አንዳንዶች በአንዱ ነጥብ ይታገሱና በሌላኛው ነጥብ ላይ ይወድቃሉ። እያንዳንዱ እርምጃ ወደ ፊት በሄደ ቁጥር ልብ ትንሽ ቀረብ በማለት ይፈተናል። ማናቸውም ቢሆኑ ልባቸው ቀጥተኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሥራ የሚቃረን ሆኖ ካገኙት ያንን በማሸነፍ የሚሰሩት ሥራ እንዳለ ወይም በመጨረሻ በጌታ ተቀባይነትን እንደሚያጡ ሊያሳምናቸው ይገባል። -RH, Apr 8, 1880. (HC 162.) {1MCP 347.4}1MCPAmh 283.2

  የምስጢር ማነሳሻዎቻችን መዳረሻችንን ይወስናሉ።--ተግባሮቻችን፣ ቃላቶቻችን፣ እጅግ ምስጢራዊ የሆኑ ማነሳሻ ምክንያቶቻችንም ቢሆኑ፣ መዳረሻችንን ለደስታ ወይም ለዋይታ በመወሰን ሂደት ሁላቸውም የየራሳቸው ክብደት አላቸው። ምንም እንኳን በእኛ ቢረሱም ለጽድቅ ወይም ለኩነኔ ምስክርነታቸውን ያስተላልፋሉ። --GC 486, 487 (1911). {1MCP 348.1}1MCPAmh 283.3

  እግዚአብሔር ሰዎችን የሚገምተው አንድን ነገር እንዲያደርጉ ያነሳሳቸው ነገር ባለው ንጽህና ነው።--እግዚአብሔር ሰዎችን የሚገምተው በሀብታቸው፣ በትምህርታቸው ወይም በስልጣናቸው አይደለም። እርሱ የሚገምተው አንድን ነገር እንዲያደርጉ ባነሳሳቸው ምክንያት ንጽህና እና በባህርይ ውበታቸው ነው። መንፈስ ቅዱስ ምን ያህል እንዳላቸውና ሕይወታቸው ምን ያህል የእርሱን ምሳሌ እንደሚያሳይ ለማየት ይፈልጋል። በእግዚአብሔር መንግስት ትልቅ መሆን ራስን ዝቅ በማድረግ፣ በእምነት ትህትና፣ በፍቅር ንጽህና እንደ ትንሽ ህጻን መሆን ነው።--MH 477, 478 (1905). {1MCP 348.2}1MCPAmh 283.4

  እግዚአብሔር አንድን ነገር እንድናደርግ ባነሳሱን ምክንያቶች ይፈርድብናል።--በአገልጋይ ባህርይ ውስጥ ሊያሻሽል የሚችለው ብዙ ነገር አለ። ብዙዎች ጉድለታቸውን ያያሉ ይሰማቸውማል፣ ነገር ግን በሌሎች ላይ ስለሚያሳድሩት ተጽእኖ እውቀት የሌላቸው ይመስላሉ። በሚፈጽሙአቸው ሰዓት ተግባሮቻቸውን ያውቃሉ፣ ነገር ግን ከአእምሮአቸው እንዲጠፉ ስለሚያደርጉአቸው አይታደሱም። {1MCP 348.3}1MCPAmh 284.1

  አገልጋዮች ከራሳቸው የሕይወት ልማዶች ጋር መተዋወቅን ዓላማቸው አድርገው የእያንዳንዱን ቀን ድርጊቶች በጥንቃቄ ቢያስቡበትና ሆን ብለው ቢከልሱት ኖሮ ራሳቸውን በተሻለ ሁኔታ ያውቁ ነበር። በሁሉም ሁኔታዎች ዕለታዊ ሕይወታቸውን በደንብ በመመርመር የራሳቸውን የድርጊት ማነሳሻዎችና የሚያነሳሱአቸውን መርሆዎች ያውቃሉ። ህሊና እንደሚያረጋግጥ ወይም እንደሚኮንን ለማየት የሚደረገው ይህ ዕለታዊ የተግባሮቻችን ክለሳ ወደ ክርስቲያን የባሕርይ ፍጽምና ለመድረስ ለሚመኙ ሁሉ አስፈላጊ ነው። {1MCP 348.4}1MCPAmh 284.2

  ለመልካም ሥራ የሚተላለፉ ድንጋጌዎች፣ የልግስና ተግባራትም ቢሆኑ፣ በቅርበት ሲመረመሩ፣ በስህተት ምክንያት የተነሳሱ መሆናቸው ይታወቃል። ብዙዎች በሌሉአቸው መልካም ጠባያት አድናቆትን ይቀበላሉ። የልብ መርማሪ የሆነው አንድ ነገር የተደረገበትን ምክንያት ስለሚመረምር ብዙ ጊዜ በሰዎች ከፍተኛ አድናቆት የተቸራቸው ተግባሮች ከራስ ወዳድነት ማነሳሻና ተራ ከሆነ ግብዝነት የመነጩ መሆናቸው በእርሱ ተመዝግቦአል። እያንዳንዱ የህይወታችን ተግባር፣ ከሁሉ የላቀና ምስጋና የሚገባው ቢሆን ወይም ነቀፌታ የሚገባው ቢሆን ልብን የሚመረምረው ያ ድርጊት እንዲፈጸም ባነሳሱት ምክንያቶች ይፈርዳል። --2T 511, 512 (1870). {1MCP 348.5}1MCPAmh 284.3

  የአንድን ድርጊት ማነሳሻዎች ማወቅ አንዳንድ ጊዜ ከባድ ነው።--ሥራ በበዛበት የሕይወት ጭንቀት መካከል አንዳንድ ጊዜ የራሳችንን ማነሳሻዎች ማወቅ ከባድ ነው፣ ነገር ግን በየዕለቱ ለክፉ ወይም ለመልካም ለውጥ እየተደረገ ነው።--5T 420 (1889). {1MCP 349.1}1MCPAmh 284.4

  እውነተኛ መለወጥ አንድን ነገር የማድረግ ማነሳሻዎችን ይለውጣል።--እውነተኛ መለወጥ ቆራጥ የሆነ የስሜቶችና የማነሳሻዎች ለውጥ ነው፤ እውነተኛ የሆነ ከዓለማዊ ግንኙነቶች መለየት፣ ከመንፈሳዊ ከባቢ አየር በፍጥነት መውጣት፣ ከእነርሱ አስተሳሰቦች፣ አመለካከቶችና ተጽእኖዎች የመቆጣጠር ኃይል መውጣት ነው። --5T 82, 83 (1889). {1MCP 349.2}1MCPAmh 284.5

  ትልቆቹ የነፍስ ማነሳሻ ኃይሎች።--ነፍስን የሚያነሳሱ ታላላቅ ኃይሎች እምነት፣ ተስፋና ፍቅር ናቸው፤ በትክክል ከተከተልን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይግባኝ የሚለው ወደ እነዚህ ነገሮች ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ውጫዊ ውበት፣ የምስል ከሳች ቃላትና ገለጻዎች ውበት ከዚህ በፊት እንደነበረው ሁሉ እውነተኛ ለሆነው ሀብት--ለቅድስና ውበት--መነሻ ቦታ ናቸው። ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ስለተጓዙ መዝግቦ በያዘው ውስጥ የእርሱን ክብር ጨረፍታ እናያለን። ‹‹በአጠቃላይ ተወዳጅ›› በሚለው ሀረግ ውስጥ በምድርና በሰማይ ያለው ውበት ሁሉ ደብዛዛ ነጻብራቅ የሆኑለትን እርሱን እናያለን። እርሱ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እኔ ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ (ዮሐ. 12፡ 32)።--Ed 192 (1903). {1MCP 349.3}1MCPAmh 285.1