Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 28—ራስን ማክበር

  የራስ አክብሮትን ማሳደግ።--ለነፍሳት መልካም ለማድረግ ከተመኘን በእነዚህ ነፍሳት ላይ የሚኖረን ስኬት የሚለካው እኛ በእነርሱ ላይ ስላለን እምነትና አድናቆት እነርሱ በሚኖራቸው እምነትና አድናቆት ልክ ነው። ሰው ያጣውን የራስ ክብር የመመለሻ እርግጠኛው መንገድ እየታገለ ላለው ሰብአዊ ነፍስ አክብሮት ማሳየት ነው። ሰው ሊሆን ስለሚችለው ነገር እየጨመሩ ያሉ ሀሳቦቻችን እኛ ራሳችን ሙሉ በሙሉ ልናደንቅ የማንችላቸው ናቸው። --Lt 50, 1893. (FE 281.) {1MCP 255.1}1MCPAmh 209.1

  የሰውን ስብዕና እንደ ሰው ማክበር።--በመርህ ላይ ድርድር በሌለበት ሁሉ ሌሎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት ተቀባይነት ካገኙ ወጎች ጋር ወደ መስማማት ይመራል፤ ነገር ግን እውነተኛ ገርነት ተቀባይነት ላላቸው ልማዶች መርህን መስዋዕት ማድረግን አይጠይቅም። ሕብረተሰብን በተለያየ መደብ መከፋፈልን አይቀበልም። ራስን ማክበርን፣ እንደ ሰው የሰው ስብዕናን ማክበርን፣ በታላቁ ሰብአዊ ወንድማማችነት ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ አባል አክብሮት መስጠትን ያስተምራል።--Ed 240 (1903). {1MCP 255.2}1MCPAmh 209.2

  የራስ ክብርን ጠብቁ።--አንዳንድ የምትገናኙአቸው ሰዎች ሥርዓተ አልበኞችና ትህትና የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ፣ ከዚህ የተነሣ እናንተም ትህትና የጎደላችሁ መሆን የለባችሁም። ራሱን አክብሮ መኖርን ማቆየት የሚፈልግ ሰው ሌሎች ለራሳቸው ያላቸውን አክብሮት አስፈላጊ ባልሆነ ሁኔታ እንዳይጎዳ መጠንቀቅ አለበት። ይህ ደንብ እጅግ ዘገምተኛ ለሆኑና እጅግ ስህተት ለሰሩ ሰዎችም በቅድስና መጠበቅ አለበት። በግልጽ ተስፋ በማይጣልባቸው በእነዚህ ሰዎች አማካይነት እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንደሚፈልግ አታውቁም። ከዚህ በፊት ብዙ ተስፋ የማይጣልባቸውን ወይም ቀልብን የማይስቡትን ለእርሱ ትልቅ ሥራ እንዲሰሩ ተቀብሎአል። የእርሱ መንፈስ በልብ ውስጥ በመንቀሳቀስ እያንዳንዱ የአካል ክፍል ተግቶ እንዲሰራ አነሳስቶአል። በእነዚህ ሸካራ በሆኑና ባልተጠረቡ ድንጋዮች ውስጥ የማዕበልን፣ የሙቀትንና የአየር ግፊትን ፈተና መቋቋም የሚችል የከበራ ነገር አየ። እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ አያይም። ፊትን በማየት አይፈርድም፣ ነገር ግን ልብን በመመርመር በጽድቅ ይፈርዳል።--GW 122, 123 (1915). {1MCP 255.3}1MCPAmh 209.3

  ተግባርን ወይም ግዴታን በደንብ ለመወጣት አለመፈለግ የራስ አክብሮትን አደጋ ላይ ይጥላል።--በመርህ የሚመሩ ሰዎች የቁልፍ ጋኖችና የመክፈቻ ቁልፎች ቁጥጥር አያስፈልጋቸውም፤ ነቅቶ የሚከታተልና የሚጠብቅ ሰው አያስፈልጋቸውም። ብቻቸውን፣ የሚመለከታቸው ማንም ሳይኖር፣ በሰዎች ፊትም ቢሆን፣ ሁል ጊዜ በእውነትና በክብር ይሰራሉ። ከፍተኛ ትርፍ ለማግኘት ብለው ወይም ለራስ ጥቅም ሲሉ በነፍሶቻቸው ላይ እንከን አያመጡም። ክፉ ተግባርን ይንቃሉ። ይህን ተግባር ማንም ሰው ባያውቀውም ለራሳቸው ያላቸውን አክብሮት እንደሚያጠፋባቸው እነርሱ ራሳቸው ያውቃሉ። በትናንሽ ነገሮች ለህሊና የማይገዙና ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች ሕጎች፣ ዕቀባዎችና ቅጣቶች በቦታቸው ቢኖሩም አይታረሙም። --SpTPH 62, 1879. (CH 410.) {1MCP 256.1}1MCPAmh 209.4

  የራስ አክብሮት በጥብቅ ዋጋ ማግኘት አለበት።--የሞራል ንጽህናን፣ ራስን ማክበርን እና ጠንካራ የሆነ የመቋቋም ኃይልን በጽናትና ባለማቋረጥ መንከባከብ አለብን። ለአንዴ እንኳን ከቁጥብነት መለየት የለብንም። አንዲት እውቅናን የማግኘት ተግባር፣ አንዲት የጥንቃቄ ጉድለት፣ ለፈተና በር በመክፈትና የመቋቋም ኃይልን በማዳከም ነፍስን አደጋ ላይ ልትጥል ትችላለች።--HPMMW 26, 1885. (CH 295.) {1MCP 256.2}1MCPAmh 210.1

  ለሌሎች ያለን አክብሮት የሚለካው ለራሳችን ባለን አክብሮት ነው።--ኃጢአትን በመስራት የራስ አክብሮት ይጠፋል፤ ይህ ሆኖ ሲያልፍ ለሌሎች ያለው አክብሮት ይቀንሳል፤ እኛ ቅዱስ እንዳልሆንን ሁሉ ሌሎችም ቅዱስ እንዳልሆኑ እናስባለን።--6T 53 (1900). {1MCP 256.3}1MCPAmh 210.2

  በተሳሳቱ ልማዶች ተማሪው የራስ ክብርን ያጠፋል።--ከስህተት ልማዶች የተነሳ ራሱን የማድነቅ ኃይሉን ያጣል። ራሱን መቆጣጠር ያቅተዋል። እጅግ በሚመለከቱት ጉዳዮች ላይ በትክክል ማገናዘብ አይችልም። አካሉንና አእምሮን በሚይዝበት ሁኔታ ግድ የለሽና ማሰብ የማይችል ይሆናል። በስህተት ልማዶች ራሱን ከጥቅም ውጭ/በሽተኛ ያደርጋል። ንጹህና ጤናማ መርሆዎችን ለማሳደግ ችላ ማለቱ ሰላሙን በሚያጠፉ ልማዶች ቁጥጥር ሥር ስለሚያደርገው ደስታ ሊያገኝ አይችልም። ራሱን ስላበላሸ ልፋት የነበረባቸው የትምህርት ዓመታት በከንቱ ጠፍተዋል። የአካልና የአእምሮ ኃይሎችን ያለ አግባብ ስለተጠቀመ የአካል ቤተ መቅደስ ፈርሶአል። ለዚህ ሕይወትም ሆነ ለሚመጣው የማይጠቅም ሆኗል። ምድራዊ እውቀትን በማግኘት ሀብትን ለማግኘት አስቦ ነበር፣ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሱን ወደ ጎን በመተው ሁሉንም ነገር መሆን የሚችለውን ሀብት መስዋዕት አደረገ። --COL 108, 109 (1900). {1MCP 257.1}1MCPAmh 210.3

  ትዕግስት የሌላቸው ቃላት የራስ አክብሮትን ይጎዳሉ።--እንደዚህ ዓይነቱን ቋንቋ የሚጠቀሙ ሰዎች [ትዕግስት የለሽ ቃላት] ኃፍረትን፣ የራስ አክብሮት ማጣትን፣ በራስ መተማመን ማጣትን ይለማመዳሉ፤ ራሳቸውን ባለመቆጣጠራቸውና በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በመናገራቸው መራር ፀፀትና ቁጭት ያጋጥማቸዋል። የዚህ ዓይነት ባህርይ ያላቸው ቃለት በፍጹም ባይነገሩ ምን ያህል መልካም ነበር። በልብ ውስጥ የጸጋ ዘይት መኖር፣ ትንኮሳዎችን ሁሉ ማለፍ መቻል፣ እና ሁሉንም ነገር ክርስቶስን በሚመስል የዋህነትና ትዕግስት መሸከም ምን ያህል ይሻል ነበር።-- RH, Feb 27, 1913. (MYP 327.) {1MCP 257.2}1MCPAmh 210.4

  ወላጆች ማገናዘብ በጎደላቸው ቃላት ለራስ ያላቸውን ክብር በፍጹም ማጣት የለባቸውም።--አንድም ደስታ የጎደለው፣ የጭካኔ፣ ወይም በስሜት የተነሳሳ ቃል ከከናፍራችሁ አይውጣ። የክርስቶስ ጸጋ የእናንተን ጥያቄ ይጠብቃል። የእርሱ መንፈስ ቃላቶቻችሁንና ተግባሮቻችሁን በመጠበቅ ልባችሁንና ህሊናችሁን ይቆጣጠራል። በችኮላና ሳይታሰብ በሚነገሩ ቃላት ለራሳችሁ ያላችሁን አክብሮት አትጡ። ቃላቶቻችሁ ንጹህ መሆናቸውንና ንግግራችሁም ቅዱስ መሆኑን ተመልከቱ። ልጆቻችሁ እንዲሆኑ ስለምትፈልጉት ነገር እናንተ ምሳሌ ሁኑአቸው…። ሰላም፣ አስደሳች ቃላትና በደስታ የተሞላ ፊት ይኑራችሁ።--Lt 28, 1890. (CG 219.) {1MCP 257.3}1MCPAmh 211.1

  ሴጋ የራስ አክብሮትን ያጠፋል። [ቻይልድ ጋይዳንስ በሚል መጽሐፍ ገጽ 439-468ን ይመልከቱ]--የዚህ ዓይነት ወራዳ የሆኑ ልማዶች ተጽእኖ በሁሉም አእምሮ ላይ እኩል አይደለም። የሞራል ኃይላቸው በአብዛኛው ያደጋ ሆኖ ራሳቸውን ያለ አግባብ ከሚጠቀሙ ልጆች ጋር ግንኙነት ከመፍጠራቸው የተነሣ ይህን ክፋት ለመለማመድ የተነሳሱ አንዳንድ ልጆች አሉ። እንደ እነዚህ ባሉ ልጆች ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ብዙ ጊዜ ማዘን፣ መናደድና መቅናት ነው፤ የዚህ ዓይነት ልጆች ለኃይማኖታዊ አምልኮ ያላቸውን አክብሮት ስለማያጡ መንፈሳዊ ነገሮችን በተመለከተ ልዩ ክህደትን አያሳዩም። አንዳንድ ጊዜ የፀፀት ስሜት ስለሚያሰቃያቸውና በራሳቸው እይታ እንደ ተዋረዱ ስለሚሰማቸው ለራሳቸው ያላቸውን አክብሮት ያጣሉ።--2T 392 (1870). {1MCP 258.1}1MCPAmh 211.2

  የራስ አክብሮትን አታበላሹ።--አንድ ስህተት የሰራ ሰው ስህተቱን ሲገነዘብ ለራሱ ያለውን አክብሮት እንዳታጠፉበት ተጠንቀቁ። በግድ የለሽነትና በእርሱ ላይ እምነት እንደማትጥሉበት በማሳየት ተስፋ አታስቆርጡት። ‹‹በእርሱ ላይ ያለኝን መተማመን ከመግለጼ በፊት በአቋሙ እንደሚጸና ለማየት እጠብቃለሁ›› አትበሉ። ብዙ ጊዜ ይህ አለመታመን የተፈተነውን ሰው ተደናቅፎ እንዲወድቅ ያደርገዋል። -- MH 167, 168 (1905). {1MCP 258.2}1MCPAmh 211.3

  ራስን መደገፍ የራስ አክብሮትን ይጨምራል።--ለመታደስ ጥረት እያደረጉ ያሉ ሰዎች ሥራ ሊሰጣቸው ይገባል። መሥራት የሚችሉ ሁሉ ምግብን፣ ልብስንና መጠለያን በነጻ ለማግኘት እንዲጠብቁ መማር የለባቸውም። ለራሳቸውና ለሌሎች ሲባል ከሚቀበሉት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ነገርን የሚመልሱበት የሆነ መንገድ መቀየስ አለበት። ራሳቸውን ለመደገፍ የሚያደርጉትን እያንዳንዱን ጥረት አደፋፍሩ። ይህ የራስ አክብሮትንና ክቡር የሆነ ከጥገኝነት ነጻ መሆንን ያጠናክራል። አእምሮንና አካልን ጠቃሚ በሆነ ሥራ እንዲጠመድ ማድረግ ከፈተና ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው።--MH 177 (1905). {1MCP 258.3}1MCPAmh 211.4

  የሆነ ነገር ባለቤት መሆን ድሆች የራስ አክብሮትን እንዲያገኙ ይረዳቸዋል።--እነርሱ [ድሆች] የራሳቸው ቤት እንዳላቸው መሰማት ለመሻሸል ጠንካራ ፍላጎት እንዲኖራቸው ያደርጋል። ለራሳቸው በማቀድና ዘዴዎችን በመቀየስ ወዲያውኑ ክህሎትን ያዳብራሉ፤ ልጆቻቸው የመስራትንና የመቆጠብን ልማዶች ይማራሉ፣ የአእምሮ ችሎታቸውም በከፍተኛ ደረጃ ጥንካሬ ያገኛል። ባሪያዎች ሳይሆኑ ሰዎች መሆናቸው ስለሚሰማቸው ከዚህ በፊት አጥተውት የነበረውን የራስ አክብሮትና የሞራል ነጻነት በከፍተኛ ደረጃ መልሰው ያገኙታል።--HS 165, 166, 1886. (AH 373.) {1MCP 258.4}1MCPAmh 212.1

  ራስን ማሰልጠንና ክብር።--የክርስቶስ አገልጋዮች ሙያቸውን ለማክበርና ተቀባይነት ያለው ክብር እንዲኖራቸው ራስን የማሰልጠንን አስፈላጊነት መመልከት ጠቃሚ ነው። ያለ አእምሮ ስልጠና በሚያደርጉት በእያንዳንዱ ሥራ በእርግጠኝነት ስኬት ማግኘት አይችሉም።--2T 500, 501 (1870). {1MCP 259.1}1MCPAmh 212.2

  ለራስ ሰበብ ከመስጠት ተጠንቀቁ።--ለራሳችን ሰበቦችን ከመደርደር መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ማግኘት የሚገባኝን ክብር አላገኘሁም፣ ጥረቶቼ አልተደነቁልኝም፣ ሥራዬ እጅግ ከባድ ነው የሚሉ ስሜቶችን በፍጹም አትለማመዱአቸው። ክርስቶስ ለእኛ የተሸከመው ነገር ትውስታ እያንዳንዱን የማጉረምረም ሀሳብ ጸጥ ያድርግ። እኛ የደረሰብን ጌታችን ከደረሰበት የተሻለ ነው። ‹‹ለራስህ ታላቅ ነገርን ትፈልጋለህን...አትፈልገው›› (ኤርምያስ 45፡ 5) ።--MH 476 (1905). {1MCP 259.2}1MCPAmh 212.3

  ክርስቶስ የራስ አክብሮትን ይመልሳል።--ጌታ ችግሮችህንና ግራ የሚያጋቡህን ነገሮች በእግሩ ሥር እንድታስቀምጥ እንደሚፈልግ ማስታወስ ሊከብድህ አይገባም። እንዲህ እያልክ ወደ እርሱ ሂድ፡-‹‹ጌታ ሆይ፣ ሸክሞቼ ልሸከማቸው ከምችለው በላይ ናቸው። እነዚህን ሸክሞች ለእኔ ትሸከምልኛለህን?›› እርሱም እንዲህ በማለት ይመልስልሃል፡- ‹‹ሸክሞችህን እወስድልሃለሁ። ‹በዘላለም ደግነት እምርሃለሁ።› ኃጢአቶችህን ወስጄ ሰላም እሰጥሃለሁ። በራሴ ደም ዋጋ ስለገዛሁህ ለራስ ያለህን አክብሮት አታጥፋ። አንተ የእኔ ነህ። ድካምህን ወደ ብርታት እለውጣለሁ። ኃጢአት የሚያስከትልብህን ጸጸት አስወግዳለሁ።›› --Lt 2, 1914 (TM 519, 520.) {1MCP 259.3}1MCPAmh 212.4

  የራስ አክብሮትን ላጣ ሰው የተሰጠ ምክር።--ኢየሱስ ይወድሃል፣ ስለ አንተ መልእክትም ሰጥቶኛል። ሊለካ የማይችል ገርነት ያለው ታላቅ ልቡ ስለ አንተ መዳን ይጓጓል። ራስህን ከጠላት ወጥመድ ነፃ እንድታወጣ መልእክት ይልክልሃል። ለራስህ ያለህን አክብሮት መልሰህ ማግኘት ትችላለህ። በእግዚአብሔር መንፈስ ከፍ በሚያደርገው ተጽእኖ እንደ ተሸናፊ ሳይሆን እንደ አሸናፊ ሆነህ ራስህን ማስቀመጥ በምትፈልግበት ቦታ መቆም ትችላለህ። የክርስቶስን እጅ አጥብቀህ ያዝ፣ አትልቀቀው። --Lt 228, 1903. (MM 43.) {1MCP 259.4}1MCPAmh 213.1

  የራስ አክብሮትን አሳድጉ።--ለራሳችሁ ዋጋ ማሳጣት እግዚአብሔርን አያስደስተውም። በራሳችሁ ሕሊና፣ በሰዎችና በመላእክት ፊት ተቀባይነት እንድታገኙ በኑሮአችሁ ራሳችሁን ማክበርን አሳድጉ…። ወደ ኢየሱስ ሄዳችሁ መንጻትና በሕግ ፊት ያለ እፍረትና ያለ ፀፀት መቆም ልዩ መብታችሁ ነው። ‹‹እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት፣ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ ለማይመላለሱ፣ አሁን ኩነኔ የለባቸውም›› (ሮሜ 8፡1)። ስለ ራሳችን ማሰብ ከሚገባን በላይ ከፍ አድርገን ማሰብ ባይኖርብንም የእግዚአብሔር ቃል ተገቢ የሆነ የራስ አክብሮትን አይኮንንም። እንደ እግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች ኩራትና እኔ ከሌሎች የተሻልኩ ነኝ የሚል አስተሳሰብ ቦታ ሳይሰጠው ለባሕርይ አውቀን ክብር መስጠት አለብን።--RH, Mar 27, 1888. (HC 143.) {1MCP 260.1}1MCPAmh 213.2

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents