Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First

  ምዕራፍ 24—ፍቅር በቤት ውስጥ

  [ምዕራፍ 32 ላይ ‹‹የወረት ፍቅር እና እውር ፍቅር›› የሚለውን ክፍል ይመልከቱ።]

  የእውነተኛ ሰብአዊ ፍቅር ምንጭ።--ለእርስ በርሳችን ያለን ፍቅር የሚመነጨው ለእግዚአብሔር ካለን የተለመደ ግንኙነት ነው። አንድ ቤተሰብ ነን፣ እርሱ እንደ ወደደን እርስ በርሳችን እንዋደዳለን። ዓለም የሚያሳየው ጥልቀት የሌለው ገርነት፣ እጅግ የጋለ ትርጉም የለሽ ጓደኝነት፣ ከዚህ እውነተኛ፣ ቅዱስና ሥነ-ሥርዓት ካለው ፍቅር ጋር ሲነጻጸር ገለባ ከስንዴ ጋር እንዳለው ንጽጽር ነው። --Lt 63, 1896. (SD 101.) {1MCP 211.1}1MCPAmh 172.1

  ክርስቶስ እንደወደደ መውደድ ማለት ትህትና በተላበሱ ቃላትና አስደሳች በሆነ እይታ በሁሉም ጊዜና በሁሉም ቦታ ራስ ወዳድ አለመሆንን ማሳየት ነው።…ማስመሰል የሌለበት ፍቅር ለሌሎች በተሰጠ ልክ መዓዛው እየጨመረ የሚሄድ ሰማያዊ መነሻ ያለው ውድ ስጦታ ነው። --MS 17, 1899. (SD 101.) {1MCP 211.2}1MCPAmh 172.2

  ፍቅር ልብን ከልብ ጋር ያስተሳስራል።--የጋራ ፍቅር፣ የጋራ መቻቻል ይኑር። ያኔ ጋብቻ የፍቅር መጨረሻ መሆኑ ቀርቶ የፍቅር መጀመሪያ ይሆናል። የእውነተኛ ጓደኝነት ግለት፣ ልብን ከልብ ጋር የሚያስተሳስር ፍቅር፣ የሰማይ ደስታ ቅምሻ ነው…። እያንዳንዱ ሰው ፍቅር እንዲሰጠው ከመጠየቅ ይልቅ ፍቅርን ይስጥ።--MH 360, 361 (1905). {1MCP 211.3}1MCPAmh 172.3

  ፍቅር ንጹህ ግን ጥልቀት የሌለው ሊሆን ይችላል።--ፍቅር እንደ መስተዋት የጠራና በንጽህናውም ያማረ፣ ግን ስላልተፈተነና ስላልተሞከረ ጥልቀት የሌለው ሊሆን ይችላል። በሁሉም ነገር ክርስቶስን መጀመሪያ፣ መጨረሻና ከሁሉም በላይ አድርጉት። ሳታቋርጡ እርሱን ተመልከቱት፣ ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር በመከራ እንዲፈተን ሲደረግ በየቀኑ ጥልቀቱ እየጨመረና እየጠነከረ ይሄዳል። ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረ ሲሄድ ለእርስ በርሳችሁ ያላችሁ ፍቅርም እየጠለቀና እየጠነከረ ይሄዳል። ‹‹እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን›› (2ኛ ቆሮንቶስ 3፡ 18)። --7T 46 (1902). {1MCP 212.1}1MCPAmh 172.4

  ፍቅር ሳይገለጽ መኖር አይችልም።--ማህበራዊና የልግስና ስሜቶች ሲታመቁ ይጠወልጉና ልብ ባዶና ቀዝቃዛ ይሆናል…። ፍቅር ሳይገለጽ ለረዥም ጊዜ መኖር አይችልም። ከእናንተ ጋር ግንኙነት ያለው ሰው ልብ ደግነትንና ርኅራኄን በማጣት እንዲራብ አታድርጉ።--MH 360 (1905). {1MCP 212.2}1MCPAmh 172.5

  በጥንቃቄ መያዝ ያለበት የፍቅር ተክል።--ውድ የሆነ የፍቅር ተክል በጥንቃቄ መያዝ አለበት፣ ይህ ሲሆን የሚያፈራው ፍሬ ብርቱ፣ ኃይለኛና ያማረ ስለሚሆን የጠቅላላው ባሕርይ መግለጫ ይሆናል። --Lt 50, 1893. {1MCP 212.3}1MCPAmh 173.1

  የፍቅር ስሜቶች መታፈን የለባቸውም።--ለእግዚአብሔርና ለእርስ በርስ ያለው ፍቅር እንዲገለጽ አደፋፍሩ። በዓለም ላይ እጅግ ብዙ ልባቸው የጠነከረባቸው ወንዶችና ሴቶች ያሉበት ምክንያት እውነተኛ ፍቅርን መግለጽ እንደ ድክመት ተቆጥሮ ሳይገለጽ ታምቆ እንዲቀር ስለተደረገ ነው። የእነዚህ ሰዎች የተሻለው ተፈጥሮ በልጅነታቸው ታፍኖአል፤ የመለኮታዊው ፍቅር ብርሃን የእነርሱን ቀዝቃዛ የሆነ ራስ ወዳድነት ካላቀለጠ በቀር፣ ደስታቸው ለዘላለም ይበላሻል። እኛ ከልጆቻችን ጋር ኢየሱስ ያለው ገር መንፈስና መላእክት ለእኛ የሚያሳዩት ርኅራኄ እንዲኖረን ከፈለግን የልጅነትን ለጋስና አፍቃሪ ስሜቶች ማደፋፈር አለብን።--DA 516 (1898). {1MCP 212.4}1MCPAmh 173.2

  ፍቅር ስሜት አይደለም።--ፍቅር መነሻው ሰማይ የሆነ ተክል ነው። አግባብነት የሌለው አይደለም፤ እውር አይደለም። ንጹህና ቅዱስ ነው። ነገር ግን የተፈጥሮ ልብ ስሜት ሙሉ በሙሉ ሌላ ነገር ነው። ንጹህ ፍቅር በእቅዶቹ ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያስገባና ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ፍጹም መጣጣም ያለው ሲሆን ስሜት ግን ግትር፣ ችኩል፣ አግባብነት የሌለው፣ ገደብን ሁሉ የማይቀበልና የመረጠውን ነገር ጣዖቱ የሚያደርግ ነው። {1MCP 212.5}1MCPAmh 173.3

  እውነተኛ ፍቅር ባለው ሰው ጠባይ የእግዚአብሔር ጸጋ ይታይበታል። የጋብቻ ሕብረት ለመፍጠር የሚደረገውን እያንዳንዱን እርምጃ ጨዋነት፣ ትህትና፣ ቅንነት፣ ሀቀኝነትና ኃይማኖት ይገልጸዋል።--RH, Sept 25, 1888. (MYP 459.) {1MCP 213.1}1MCPAmh 173.4

  የተሳካ ጋብቻ ለመፍጠር እውነተኛ የሆነ የፍቅር ዝግጅት።--እውነተኛ ፍቅር ከፍ ያለና ቅዱስ መርህ ስለሆነ በባህርዩ በስሜት ከተነሳሳና ክፉኛ ሲፈተን በድንገት ከሚሞት ፍቅር ሙሉ በሙሉ የተለየ ነው። ወጣቶች ራሳቸው ለሚመሰርቱት ቤት ዝግጅት የሚያደርጉት በወላጆቻቸው ቤት ለተግባር ታማኝ በመሆን ነው። በዚህ ቦታ ራስን መካድን በመለማመድ ቸርነትን፣ ትህትናን እና ክርስቲያናዊ ርኅራኄን ያሳዩ። በዚህ ሁኔታ ፍቅር በልብ ውስጥ ሞቆ እንዲቆይ ስለሚደረግ ከእንደዚህ ዓይነት ቤተሰብ በመውጣት የራሱ ቤተሰብ ራስ የሚሆን ግለሰብ የሕይወት ጓደኛው እንድትሆን የመረጣትን ሴት ደስታ እንዴት ከፍ እንደሚያደርግ ያውቃል። --PP 176 (1890). {1MCP 213.2}1MCPAmh 173.5

  ፍቅርና ራስን መግራት ቤተሰብን ያስተሳስራል።--ወላጆች በራሳቸው ባህርይና በቤት ሕይወት የሰማያዊ አባትን ፍቅርና ልግስና ምሳሌ በመሆን ለማሳየት ይሹ። ቤት በፀሐይ ብርሃን የተሞላ ይሁን። ይህ ለልጆቻችሁ ከውርስ መሬት ወይም ከገንዘብ እጅግ የበለጠ ዋጋ ያለው ይሆንላቸዋል። የልጅነት ዘመን ቤታቸውን ከሰማይ ቀጥሎ የሰላምና የደስታ ቦታ አድርገው ወደ ኋላ መመልከት እንዲችሉ የቤት ፍቅር በልቦቻቸው ሕያው ሆኖ ይጠበቅ። የቤተሰብ አባላት ሁሉ ተመሳሳይ የሆነ የባሕርይ አሻራ ስለሌላቸው ትዕግስትንና መቻልን መለማመድ የሚያስፈልጉባቸው ተደጋጋሚ አጋጣሚዎች ይኖራሉ፤ ነገር ግን በፍቅርና ራስን በመግራት ሁሉም እጅግ ቅርበት ባለው አንድነት ሊተሳሰሩ ይችላሉ። --PP 176 (1890). {1MCP 213.3}1MCPAmh 173.6

  የእውነተኛ ፍቅር ባሕርያት (እኔ ያልኩት ትክክል ነው ለሚል ወይም ግትር ለሆነ ባል የተሰጠ ምክር)።-- እውነተኛ የሆነና ንጹህ ፍቅር የከበረ ነው። ተጽእኖው ሰማያዊ ነው። ጥልቅና ዘላቂ ነው። አልፍ አልፎ ራሱን የሚገልጥ አይደለም። ራስ ወዳድ የሆነ ስሜት አይደለም። ፍሬ ያፈራል። ሚስትህን ለማስደሰት የማያቋርጥ ጥረት ወደ ማድረግ ይመራል። ይህ ፍቅር ካለህ ይህን ጥረት ለማድረግ ተፈጥሮአዊ በሆነ ሁኔታ ይመጣል። በማስገደድ አይመጣም። የእግር ጉዞ ለማድረግ ወይም በስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ስትወጣ ሚስትህ አብራህ እንድትሄድና አብራህ በመሆኗ ደስተኛ እንድትሆን መሻት እንደ እስትንፋስህ ተፈጥሮአዊ ይሆናል። እርሷ የደረሰችበት መንፈሳዊ ደረጃ አንተ ከደረስክበት ያነሰ እንደሆነ አድርገህ ትመለከታለህ፣ ነገር ግን አንተ ካለህ መንፈስ ይልቅ እሷ ባላት መንፈስ እግዚአብሔር ደስተኛ እንደሆነ አይቻለሁ። {1MCP 214.1}1MCPAmh 174.1

  አንተ ለሚስትህ የምትገባ አይደለህም። እሷ ለአንተ እጅግ መልካም ነች። እሷ አደጋ የማትችል፣ ስሜቷ የሚነካ ተክል ነች፣ በገርነት ጥንቃቄ እንዲደረግላት ትሻለች። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ከልቧ ትሻለች። ነገር ግን ኩሩ መንፈስ ያላት ስትሆን ዘለፋን (ትችትን) የማትወድ ዓይነ አፋር ነች። በጥሞና መታየትን ወይም መተቸትን እንደ ሞት ትፈራለች። የጋብቻ ቃል ኪዳንን በመፈጸም ሚስትህን ከወደድካት፣ ካከበርካትና ከተንከባከብካት ለእርሷ ተፈጥሮአዊ ከሆነው ከዚያ ቁጥብነትና የተለየ አቋም ትወጣለች። --2T 416 (1870). {1MCP 214.2}1MCPAmh 174.2

  ነፍስ ከፍ ያለ ፍቅርን ለማግኘት ይጓጓል።--ሚስትህ በፈቃደኛነት ከጨዋታ ከወጣችበት፣ ከተከበረ ቁጥብነት ለመውጣትና በተግባሮቿ ሁሉ ራስን ዝቅ ማድረግን ለማጎልበት ጠንካራ የሆነ ጥረት ማድረግ አለባት። በውስጥህ ከፍ ያሉ ችሎታዎች ሲቀሰቀሱና በእንቅስቃሴ ሲጠነክሩ የሴቶችን ፍላጎቶች በተሻለ ሁኔታ መረዳት ትችላለህ፤ ነፍስ በዝቅተኛ ደረጃ ባለ እንስሳ ውስጥ ከሚኖር ስሜት ይልቅ ከፍ ያለ፣ ንጹህ ፍቅርን ይጓጓል። እነዚህ ስሜቶች በውስጥህ የጠነከሩት በማደፋፈርና በመለማመድ ነው። አሁን በእግዚአብሔር ፍርሃት አካልህን ከበታች ብታቆይና ሚስትህን ንጹህ በሆነ፣ ከፍ ባለ ፍቅር ለመገናኘት ከፈለግክ የተፈጥሮ ፍላጎቶቿ ይሟላሉ።፡ ወደ ልብህ ውሰዳት፤ ከፍ አድርገህ ተመልከታት። --2T 415 (1870). {1MCP 214.3}1MCPAmh 174.3

  ፍቅር የሚገለጸው በቃላትና በሥራ ነው።--ኤል---ለሚስቱ ያለውን ፍቅር፣ በቃላትና በተግባር መገለጽ ያለበትን ፍቅር፣ ማሳደግ አለበት። ገር የሆነ ፍቅርን ማሳደግ አለበት። ሚስቱ በቀላሉ የሚሰማትና አጥብቆ የመያዝ ተፈጥሮ ስላላት እንክብካቤ ያስፈልጋታል። እያንዳንዱ የገርነት ቃል፣ እያንዳንዱ የአድናቆት ቃልና ከፍቅር የሆነ ማበረታቻ የሚታስታውሰውና በረከትን ይዞ በባለቤቷ ላይ ተመልሶ የሚንጸባረቅ ነው። ያ ግትርነትና ቀዝቃዛ ቁጥብነት እንዲገዛና በመለኮታዊ ፍቅር እንዲለሰልስ የእርሱ ርኅራኄ የሌለው ባህርይ ከክርስቶስ ጋር የቀረበ ግንኙነት መፍጠር አለበት። {1MCP 215.1}1MCPAmh 175.1

  ለሚስቱ በቃላትና በተግባር የገርነትና የርኅራኄ መግለጫዎችን መስጠት ድክመት ወይም ወንድነትንና ክብርን መስዋዕት ማድረግ አይሆንም፤ ይህ በቤተሰብ ክበብ ውስጥ ብቻ እንዲቀር መደረግ የለበትም፣ ነገር ግን ከቤተሰብ ውጭ ወዳሉት አድርስ። ኤል---ማንም ሊሰራለት የማይችለው ሥራ አለው። በጌታ ሥራ ውስጥ ሸክሞችን በመሸከም በእርሱ ሊጠነክር ይችላል። ፍላጎቱና ፍቅሩ በክርስቶስና በሰማያዊ ነገሮች ላይ ማተኮር አለበት፣ ለዘላለም ሕይወት የሚሆን ባሕርይንም መመስረት አለበት።--3T 530, 531 (1875). {1MCP 215.2}1MCPAmh 175.2

  እውነተኛ ፍቅርን የሚያሳዩ ትንንሽ ተግባራት።--እሳት ያለ ነዳጅ መንደድ እንደማይችል ሁሉ ፍቅርም በውጫዊ ተግባራት ራሱን ካልገለፀ በቀር መኖር አይችልም። አንተ፣ ወንድም ሲ፣ በርኅራኄ ተግባሮች ገርነትን ማሳየትና በገርነት ቃላትና በደግነት አክብሮት ለሚስትህ ፍቅርን የመግለጥን መልካም አጋጣሚ መጠበቅ ክብርህን የሚቀንስ እንደሆነ ተሰምቶሃል። ስሜቶችህ የሚለዋወጡና በአከባቢህ ያሉ ነገሮች በጣም ተጽእኖ የሚፈጥሩብህ ሰው ነህ።.... ከሥራ ቦታህ ስትወጣ ሥራው የፈጠረብህን ጭንቀቶች፣ ግራ መጋባቶችና ብስጭቶች ተዋቸው። ወደ ቤተሰብህ ደስታ በተሞላ ፊት፣ በርኅራኄ፣ በገርነትና በፍቅር ና። ይህ ለሚስትህ መድሃኒት ለመግዛት ገንዘብ ከማውጣት ወይም ሀኪም ከማየት የተሻለ ይሆናል። ለአካል ጤና ለነፍስም ብርታት ይሆናል። --1T 695 (1868). {1MCP 215.3}1MCPAmh 175.3

  ቀኑ ሁል ጊዜ ደመናማ እንኳን ቢሆን ትዕግስተኝነት፣ አመስጋኝነትና ፍቅር በልብ ውስጥ ብርሐን እንዲቆይ ያድርጉ። --MH 393 (1905). {1MCP 216.1}1MCPAmh 175.4

  የወላጆች ምሳሌነት ያለው ኃይል።--ልጆች አባታቸውንና እናታቸውን እንዲያከብሩ ለማስተማር ከሁሉ የተሻለው መንገድ አባት ለእናት ርኅራኄ የተሞላበት ትኩረት ሲሰጥና እናትም ለአባት አክብሮት ስትሰጥ እንዲያዩ ዕድል መስጠት ነው። ልጆች አምስተኛውን ትዕዛዝ የሚታዘዙትና ‹‹ልጆች ሆይ፣ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፣ ይህ የተገባ ነውና›› ለሚለው ትዕዛዝ ትኩረት የሚሰጡት በወላጆቻቸው ሕይወት ፍቅርን በመመልከት ነው። --RH, Nov 15, 1892. (AH 198, 199.) {1MCP 216.2}1MCPAmh 176.1

  በወላጆች ውስጥ የሚንጸባረቅ የኢየሱስ ፍቅር።--እናት የልጆቿን አመኔታ ስታተርፍና እንዲወዱአትና እንዲታዘዙአት ስታስተምር በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የመጀመሪያውን ትምህርት ሰጥታቸዋለች። ወላጆቻቸውን እንደሚወዱ፣ እንደሚታመኑባቸውና እንደሚታዘዙአቸው ሁሉ አዳኛቸውን መውደድ፣ በእርሱ መታመንና እርሱን መታዘዝ አለባቸው። ታማኝነት ባለበት እንክብካቤና ትክክለኛ በሆነ ስልጠና ወላጅ ለልጁ የሚያሳየው ፍቅር ኢየሱስ ታማኝ ለሆነ ሕዝቡ ያለውን ፍቅር በደበዘዘ ሁኔታ ያንጸባርቃል። --ST, Apr 4, 1911. (AH 199.) {1MCP 216.3}1MCPAmh 176.2

  የእናት ፍቅር የክርስቶስ ፍቅር መግለጫ ነው።--እናት ስለሚወዱአት እንዲታዘዙአት ልጆቿን ስታስተምር ሳለ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የመጀመሪያዎቹን ትምህርቶች እያስተማረቻቸው ነች። እናት ለልጇ ያላት ፍቅር የክርስቶስን ፍቅር ስለሚወክል በእናታቸው እምነት ያላቸውና የሚታዘዙአት ሕፃናት አዳኙን ለመታመንና ለመታዘዝ እየተማሩ ናቸው። --DA 515 (1898). {1MCP 216.4}1MCPAmh 176.3

  የክርስቲያን ቤት ያለው ተጽእኖ በፍጹም አይረሳም። በፍቅር፣ በርኅራኄና በገርነት የተዋበ ቤት መላእክት ሊጎበኙት የሚወዱትና እግዚአብሔር የሚከበርበት ቦታ ነው። በልጅነትና በወጣትነት ዓመታት ውስጥ በጥንቃቄ የተጠበቀ የክርስቲያን ቤት ተጽእኖ በዓለም ውስጥ ካሉ ክፋቶች ለመጠበቅ እርግጠኛ የሆነ መከላከያ ነው። በእንደዚህ ዓይነት ቤት ከባቢ አየር ውስጥ ልጆች ምድራዊ ወላጆቻቸውንና ሰማያዊ አባታቸውን መውደድን ይማራሉ። --MS 126, 1903. (AH 19.) {1MCP 216.5}1MCPAmh 176.4

  የቤተሰብ ግንኙነት የሚቀድስ ተጽእኖ ሊኖረው ይገባል። እንደ እግዚአብሔር እቅድ የተመሰረቱና የተመሩ የክርስቲያን ቤቶች ክርስቲያናዊ ባሕርይን ለመመስረት አስደናቂ የሆነ እርዳታ ያደርጋሉ።…ወላጆችና ልጆች ሰብአዊ ፍቅርን ንጹህና የከበረ አድርጎ መጠበቅ ለሚችል ለእርሱ ብቻ የፍቅር አገልግሎትን በመስጠት አንድ መሆን አለባቸው። --MS 16, 1899. (AH 19.) {1MCP 217.1}1MCPAmh 176.5