Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 30—ራስ ወዳድነትና ራስን ማዕከል ማድረግ

  በተፈጥሮአችን ሁላችንም ራሳችንን ማዕክል ያደረግን ነን።--በተፈጥሮ ሁላችንም ራሳችንን ማዕክል ያደረግንና የግል አመለካከት ያለን ነን። ነገር ግን ክርስቶስ ሊያስተምረን የሚፈልጋቸውን ትምህርቶች ስንማር የእርሱ ባሕርይ ተካፋዮች እንሆናለን፤ ከእንግዲህ ወዲህ የእርሱን ሕይወት እንኖራለን። አስደናቂው የክርስቶስ ምሳሌ፣ ወደ ሌሎች ሰዎች ስሜቶች የገባበት ወደር የለሽ ገርነት፣ ከሚያለቅሱት ጋር ማልቀሱ፣ ደስ ከሚላቸው ጋር መደሰቱ፣ ከእውነተኛ ልባቸው እርሱን በሚከተሉት ሁሉ ላይ ጥልቅ የሆነ ተጽእኖ ሊያሳድር ይገባል። በደግነት ቃላትና ተግባሮች ለደከሙ እግሮች መንገዱን ቀላል ለማድረግ ይሞክራሉ።-- MH 157, 158 (1905). {1MCP 271.1}1MCPAmh 223.1

  ራስ ወዳድነት አእምሮ እንዲጠብ ያደርጋል።--የራስ ወዳድነት ፍላጎት ሁል ጊዜ መገዛት አለበት፤ እንዲሰራ ቦታ ከተሰጠው አእምሮን የሚያጠብ፣ ልብን የሚያደነድን እና የግብረገብ ኃይልን የሚያዳክም ተቆጣጣሪ ኃይል ይሆናል። ከዚያ በኋላ ተስፋ መቁረጥ ይመጣል። ሰው ራሱን ከእግዚአብሔር በመለየት ለማይጠቅሙ ነገሮች ሽጦአል። ራሱን ማክበር ስለማይችል ደስተኛ መሆን አይችልም። በራሱ ግምት ራሱን ዝቅ አድርጓል። በአስተሳሰቡ ያልተሳካለት ሰው ነው።--MS 21, 1899. {1MCP 271.2}1MCPAmh 223.2

  ራስ ወዳድነት የሰብአዊ ዘር የበደለኝነት ስሜት መንስኤ።--ራስ ወዳድነት ክርስቶስን የሚመስል ትህትና እጦት ነው፣ የዚህ መኖር የሰብአዊ ደስታ እጦትና የበደለኝነት ስሜት መንስኤ ስለሆነ ይህን ባህርይ የሚያፈቅሩ ሰዎችን ወደ እምነት ክስረት ይመራቸዋል።--Lt 28, 1888. {1MCP 271.3}1MCPAmh 223.3

  ስሜቶችን ግራ ያጋባል።--በክርስቶስ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ሰይጣን የብዙዎችን አእምሮ ይገዛል። ይህን አስከፊና አስፈሪ ሥራውን ማወቅና መቋቋም ምነው በተቻለ! ራስ ወዳድነት መርሆዎችን አዛብቷል፣ ራስ ወዳድነት ስሜቶችን ግራ አጋብቷል፣ የአእምሮ ፍርድ አሰጣጥንም አጨልሟል። ከእግዚአብሔር የተባረከ ቃል ብርሃን እየበራ ሳለ እንደዚህ ዓይነት እንግዳ የሆኑ አመለካከቶች መያዛቸውና ከመንፈስና ከእውነት ልምምድ መለየት መኖሩ እጅግ እንግዳ ነገር ይመስላል። {1MCP 272.1}1MCPAmh 223.4

  እግዚአብሔር ለሌሎች የሰጣቸውን መብቶች ከመንፈግ ቁርጠኝነት ጋር ትልቅ ደሞዝ የመጨበጥ ፍላጎት መነሻው በሰይጣን አእምሮ ውስጥ ስለሆነ ሰዎች ለእርሱ ፈቃድና መንገድ በመታዘዝ ራሳቸውን በእርሱ አርማ ሥር ያስቀምጣሉ። በዚህ ወጥመድ ውስጥ የገቡ ሰዎች ጎጂ የሆነ ተጽእኖ እንዳላቸው ማየት በማይችሉባቸው የስህተት መርሆዎች እርሾ ስለኮመጠጡ ሙሉ በሙሉ ካልተለወጡና ካልታደሱ በቀር እምነት ሊጣልባቸው አይቻልም። --SpT Series A, No. 10, p 26, Feb 6, 1896. (TM 392, 393.) {1MCP 272.2}1MCPAmh 223.5

  ስለ ራስህ ብዙ አትናገር (የሌሎችን ሀሳብ በመናቅ ሁል ጊዜ ለማዘዝ ለሚሞክርና አምባገነን ለነበረ ሰው የተሰጠ ምክር)።--ልብህ በእግዚአብሔር መንፈስ መለኮታዊ ተጽእኖ ሥር እንዲለሰልስና እንዲቀልጥ ፍቀድ። ይህ ድርጊትህ ለማንም ብርታት ስለማይሆን ስለ ራስህ ይህን ያህል አብዝተህ መናገር የለብህም። ራስህን ማእከል በማድረግ ሁል ጊዜ ራስህን መንከባከብ እንዳለብህና ሌሎችም እንዲንከባከቡህ መምራት እንዳለብህ ማሰብ የለብህም። አእምሮህን ከራስህ አንሳና ጤናማ ወደ ሆነ መስመር አስገባ። ስለ ኢየሱስ አውራ፣ ራስ ከአንተ ይለይ፤ በክርስቶስ ውስጥ ይስመጥና የልብህ ቋንቋ ይህ ይሁን፡-‹‹እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል›› (ገላትያ 2፡ 20)። በእያንዳንዱ በምትፈልግበት ጊዜ ኢየሱስ ረዳትህ ይሆናል። ከጨለማ ኃይሎች ጋር እንድትዋጋ ብቻህን አይተውህም። እስከ መጨረሻው ሊያድን በሚችል ብርቱ በሆነው ላይ ታምኖአልና በፍጹም አይተወውም። --2T 320, 321 (1869). {1MCP 272.3}1MCPAmh 224.1

  ራስህን ከማጽናናት ተጠንቀቅ።--ራስህን ማጽናናትን አቁምና የዓለምን አዳኝ አስታውስ። በሰው ፈንታ የፈጸመውን ገደብ የለሽ መስዋዕትነት አስታውስና በሰው ፈንታ እንዲህ ያለውን መስዋዕትነት ከከፈለ በኋላ ሰው ክርስቶስንና ጽድቁን ከሚጠሉት ጋር ሕብረት ቢፈጥርና የተዛባ የምግብ ፍላጎትን በማርካት ለነፍሱ ዘላለማዊ ጥፋት ቢያመጣ የሚደርስበትን ተስፋ መቁረጥ አስብ።--5T 508 (1889). {1MCP 273.1}1MCPAmh 224.2

  ለራስ መኖር እግዚአብሔርን ያዋርዳል።--የመጨረሻ ዘመን አደጋዎች በላያችን ናቸው። ራስን ለማስደሰትና የራስን ፍላጎት ለማሟላት የሚኖሩ ሰዎች እግዚአብሔርን ያዋርዳሉ። እነርሱ እውነትን በማያውቁ ሰዎች ፊት እርሱን በተሳሳተ ሁኔታ ስለሚያቀርቡ በእነርሱ አማካይነት መስራት አይችልም…። ትዕቢትን እያበረታታህ እንደሆነ እግዚአብሔር ሊያይ ይችላል። ከመሻሻል ይልቅ ከራስ ወዳድነት የመነጨ ኩራትን ለማርካት የተጠቀምካቸውን በረከቶች ከአንተ ማንሳት አስፈላጊ እንደሆነ ሊያይ ይችላል። --MS 24, 1904. (1SM 87.) {1MCP 273.2}1MCPAmh 224.3

  በራስ መተማመን መንፈሳዊነት እንደሚያስፈልግ ያመለክታል።--አንዳንዶች ራስን የመካድ ሥራ ለመስራት ፈቃደኞች አይደሉም። አንዳንድ ሀላፊነቶችን እንዲቀበሉ ግፊት ሲደረግ ትክክለኛ የሆነ ትዕግስት የለሽነታቸውን ያሳያሉ። ‹‹የእውቀትና የልምድ መጨመር ምን ያስፈልጋል?›› ይላሉ። {1MCP 273.3}1MCPAmh 224.4

  ይህ ሁሉንም ያብራራል። ሰማይ ድሃ፣ ምስኪን፣ እውርና እራቁት እንደሆኑ እየተናገረ እያለ እነርሱ ግን ‹‹ሀብታምና ባለፀጋ እንደሆኑና አንዳችም እንደማያስፈልጋቸው›› ይሰማቸዋል። ለእነዚህ እውነተኛው ምስክር እንዲህ ይላል፣ ‹‹ሀብታም እንድትሆን በእሳት የተፈተነውን ወርቅ፣ ተጎናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፣ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኩል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ›› (ራዕይ 3፡ 17፣ 18)። የራስህ በራስ መተማመን በራሱ ሁሉም ነገር የሚያስፈልግህ እንደሆነ ያሳያል። በመንፈሳዊ ሁኔታ ስለታመምህ ኢየሱስ ሀኪምህ መሆን አለበት።--5T 265 (1882). {1MCP 273.4}1MCPAmh 225.1

  ራስን የማታለል አደጋዎች።--ራሳችንን መረዳትና ስለ ራሳችን ባህርይ ትክክለኛ እውቀት ማግኘት ለእኛ ከባድ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ግልጽ ቢሆንም ለራስ በመተግበር ላይ ብዙ ጊዜ ስህተት አለ። ራስን ለማታለልና ማስጠንቀቂያዎቹና ተግሳጾቹ ለእኔ አይደሉም ብሎ ለማሰብ ተጋላጭነት አለ። ‹‹የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛ እጅግም ከፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?›› (ኤርምያስ 17፡ 9)። ራስን ማታለል እንደ ክርስቲያን ስሜትና ቅናት ሊተረጎም ይችላል። የራስ ፍቅርና መታመን የእግዚአብሔርን ቃል መስፈርቶች ከማሟላት ርቀን ሳለን ትክክል እንደሆንን ማረጋገጫ ሊሰጠን ይችላል።--5T 332 (1885). {1MCP 273.5}1MCPAmh 225.2

  ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ በአእምሮ ላይ ያለው አውዳሚ ተጽእኖ።--ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ በሰብአዊ ልብ ላይ የሚያሳርፈው አሻራ እጅግ ጥልቅ ስለሆነ እና ለሰብአዊ ኃይል ያለው ፍላጎት እጅግ ትልቅ ከመሆኑ የተነሣ የብዙዎች አእምሮ፣ ልብና ነፍስ በመግዛትና በማዘዝ ሀሳብ ይመሰጣል። ይህን በሰብአዊ አእምሮ ውስጥ ያለውን አውዳሚ ተጽእኖ ሰማያዊ እይታ እንዲሰጥ ጌታን ከመፈለግ ውጭ ምንም ነገር ሊያጠፋው አይችልም። ሰው እውነተኛ አቋሙን እንዲያውቅና በልብ ውስጥ ለመጻፍ አስፈላጊ የሆነ ሥራን እንዲሰራ ማድረግ የሚችለው የመለኮታዊ ኃይል ፀጋ ብቻ ነው።--Lt 412, 1907. {1MCP 274.1}1MCPAmh 225.3

  በራስ የመተማመንን ጽንፍ መከላከል (ለሥራ ሀላፊ የተሰጠ ምክር)።--ስለ ራስህ ያለህ አመለካከት እጅግ ከፍ ያለ ከሆነ የሰራሃቸው ሥራዎች ካመጡት ውጤት የበለጠ እርግጠኛ የሆነ ውጤት ይኖራቸዋል ብለህ ስለምታስብ የእብሪተኝነት ድንበርተኛ የሆነውን በራስ መታመን ትማጸናለህ። ወደ ሌላው ጽንፍ በመሄድ ስለ ራስህ እጅግ የወረደ አመለካከለት ከያዝክ የዝቅተኝነት ስሜት ስለሚሰማህ ለመልካም ሊኖርህ የሚችለውን ተጽእኖ በከፍተኛ ደረጃ የሚገድብ የዝቅተኝነት አሻራ ትቶ ያልፋል። ስለዚህ ሁለቱንም ጽንፎች መከላከል አለብህ። ስሜት ሊቆጣጠርህ አይገባም፤ ሁኔታዎች ተጽእኖ ሊያሳድሩብህም አይገባም። ከሁለቱም ጽንፎች የሚጠብቅህን ትክክለኛ የሆነ ግምት ስለ ራስህ መስጠት ትችላለህ። ከንቱ የሆነ በራስ መተማመንን ሳታሳይ ክብር ያለህ ሰው መሆን ትችላለህ፤ የራስን ክብርና የግል ነጻነትህን መስዋዕት ሳታደርግ ትሁት መሆን ትችላለህ። ይህንን ካደረግክ ሕይወትህ በከፍተኛም ሆነ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባሉ ሰዎች ላይ ታላቅ ተጽእኖ የሚፈጥር ይሆናል።--3T 506 (1875). {1MCP 274.2}1MCPAmh 225.4

  ራስን ማዕከል ማድረግ በሽታን ያበረታታል (የግል መልእክት)።--እንዲሳካልህ ከፈለግክ ጥረቶችህ ጽኑ፣ ጥብቅና ትጋት ያለባቸው መሆን አለባቸው። እንደ ክርስቶስ ተከታይ እያንዳንዱን ደስታ የጎደለውና ፍትወተኛ የሆነ መግለጫን መቆጣጠርን መማር አለብህ። አእምሮህ ከመጠን በላይ ራስህን ማዕከል ያደረገ ነው። ስለ ራስህ፣ ስለ አካልህ ድክመቶች ከመጠን በላይ ትናገራለህ። {1MCP 275.1}1MCPAmh 226.1

  ራስህ የመረጥከው መንገድ፣ በተሳሳቱ ልማዶችህ አማካይነት፣ በየዕለቱ በሽታ እያመጣብህ ነው። ሐዋርያው አካላቸውን ለእግዚአብሔር እንዲቀድሱ ወንድሞቹን ይማጸናቸዋል፡-‹‹እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፣ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፣ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ›› (ሮሜ 12፡ 1፣ 2)።--Lt 27, 1872. {1MCP 275.2}1MCPAmh 226.2

  ራስን ማዕከል ማድረግ አመለካከትን ይጎዳል(ሌላ የግል መልእክት)።--ወንድሜ ሆይ፣ በብዙ መንገድ ልትረዳን ትችላለህ። ነገር ግን ራስህን ማዕከል እንዳታደርግ እንድነግርህ ጌታ ልኮኛል። የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት መስማት እንዳለብህ፣ እንዴት መረዳት እንዳለብህ እና እንዴት ማድነቅ እንዳለብህ ልብ በል። ከወንድሞችህ ጋር የተስተካከለ ግንኙነት በመፍጠር እግዚአብሔር ይባርከሃል። የሶስተኛውን መልአክ መልእክት እንዲያውጁ የላካቸው ሰዎች ከሰማይ ኃይሎች ጋር በሕብረት እየሰሩ ነበር። ጌታ በአባሎች መካከል አለመስማማትን የሚያመጣ መልእክት የማወጅ ሸክም በጫንቃህ ላይ አያስቀምጥም። ደግሜ እናገራለሁ፣ እርሱ ማንንም ቢሆን የእርሱ ሕዝብ ለዓለማችን እንዲያስተላልፉ በሰጠው ክቡር መልእክት ላይ ያለውን እምነት የሚንድ ንድፈ ሀሳብ እንዲቀርጽ በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት እየመራ አይደለም። --MS 32, 1896. (2SM 115). {1MCP 275.3}1MCPAmh 226.3

  ለእያንዳንዱ ልጅ ራስን የመርሳት ፀጋ ትምህርት መሰጠት አለበት።--በእያንዳንዱ ልጅ ውስጥ በተለየ ሁኔታ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ማደግ ከሚያስፈልጋቸው ባህርያት መካከል አንዱ ለሕይወት ያልጠበቁትን ፀጋ የሚሰጥ ራስን መርሳት ነው። ይህ ከሁሉም የባሕርይ ብቃቶች እጅግ ውብ ሲሆን ለእያንዳንዱ እውነተኛ የሆነ የሕይወት ሥራ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ብቃቶች አንዱ ነው።--Ed 237 (1903). {1MCP 275.4}1MCPAmh 227.1

  የእውነተኛ ትልቅነት መሰረቱ ራስን መርሳት ነው።--ለኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ስለ መንግስቱ ተፈጥሮ መማር በቂ አልነበረም። እነርሱ ያስፈልጋቸው የነበረው ከመርሆዎቹ ጋር ወደ መጣጣም የሚያመጣ የልብ ለውጥ ነበር። ኢየሱስ ትንሽ ሕጻንን ወደ እርሱ ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ፤ ከዚያም ያንን ትንሽ ልጅ በጥንቃቄ በክንዶቹ ላይ በማቀፍ እንዲህ አለ፣ ‹‹ካልተለወጣችሁና እንደ ትናንሽ ሕጻናት ካልሆናችሁ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት አትገቡም።›› የትንሽ ሕጻን ትህትና፣ ራስን መርሳት እና የመስጠት ፍቅር ሰማይ ዋጋ የሚሰጣቸው ባሕርያት ናቸው። እነዚህ የእውነተኛ ታላቅነት ባህርያት ናቸው።--DA 437 (1898). {1MCP 276.1}1MCPAmh 227.2

  የራስን ኃጢአት የሚያስተስርይ አድርጎ ማሰብ በውሸት ኃይማኖት ውስጥ ያለ የጸሎት መርህ ነው።--አረመኔዎች/ ኃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ጸሎቶቻቸው በራሳቸው ኃጢአትን የሚያስተሰርይ ችሎታ እንዳላቸው አድርገው ይመለከታሉ። ስለዚህ ጸሎቱ ሲረዝም ችሎታውም ትልቅ ይሆናል። በራሳቸው ጥረቶች ቅዱስ መሆን ከቻሉ በውስጣቸው ደስታ የሚያመጣ የሆነ ነገር፣ለመኩራራትም የሆነ ምክንያት ይኖራቸዋል። ይህ የጸሎት ሀሳብ የሀሰት ኃይማኖት ሥርዓቶች ሁሉ መሰረት ላይ ያለ መርህ ውጫዊ መግለጫ ነው። ፈሪሳውያን ይህን የአረመኔዎችን የጸሎት ሀሳብ የወሰዱ ሲሆን በእኛ ዘመን ክርስቲያን ነን በሚሉ ሰዎች መካከልም ቢሆን በምንም መንገድ የጠፋ አይደለም። ልብ እግዚአብሔር እንደሚያስፈልገው ሳይሰማው እንዲኖር የሚያደርጉ ልማዳዊ ሀረጎችን መድገም፣ ከአረማኔዎች ‹‹ከንቱ ድግግሞሽ›› ጋር ተመሳሳይ ባሕርይ አለው። --MB 86 (1896). {1MCP 276.2}1MCPAmh 227.3

  በክርስቶስ ሕይወት ውስጥ ምንም ዓይነት የራስን ሥልጣን (ማንነት) ማሳየት አልነበረም።--በእርሱ ሕይወት ምንም ዓይነት የራስን ሥልጣን የማሳየት ሥራ አልተደባለቀም። ዓለም ለሥልጣን፣ ለሀብት፣ እና ለመክሊት የሚሰጠው አክብሮት ለእግዚአብሔር ልጅ እንግዳ ነበር። ሰዎች ታማኝነትን ወይም አክብሮትን ለማግኘት ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች አንድም ቢሆን መሲሁ የሚጠቀመው አልነበረም። እርሱ ሙሉ በሙሉ ራሱን መካዱ በሚከተሉት ቃላት አስቀድሞ ተገልጾአል፡-‹‹እርሱ አይጮህም፣ ድምጹንም አያነሳም፣ በአውራ ጎዳናም እንዲሰማ አያደርግም። የተቀጠቀጠ ሸምበቆን አይሰብርም፣ የሚጤስ ጧፍንም አያጠፋም።›› --PK 692, 693 (1917). {1MCP 276.3}1MCPAmh 227.4

  ለራስ ወዳድነትና ራስን ከፍ ከፍ ለማድረግ እግዚአብሔር ያዘጋጀው ፈውስ።--በሰው ውስጥ ከወንድሙ ይልቅ ራሱን አስበልጦ የማየት፣ ለራስ የመስራት፣ ከፍ ያለውን ቦታ የመሻት ባሕርይ አለ፤ ብዙ ጊዜ ይህ ክፉ ጥርጣሬንና የመንፈስ መራርነትን ያስከትላል። ከጌታ ራት በፊት የሚፈጸመው ሥርዓት [የእግር እጥበት] የሚካሄደው እነዚህን አለመግባባቶች ለማስወገድ እና ሰውን ከራስ ወዳድነትና ራስን ከፍ ከፍ ከማድረግ ዝቅጠት አወጥቶ ወንድሙን እንዲያገለግል ወደሚመራው የልብ ትህትና ለማድረስ ነው።{1MCP 277.1}1MCPAmh 228.1

  ነፍስን ለመመርመር፣ ኃጢአትን ለማሳመንና ኃጢአት ይቅር የመባሉን የተባረከ ማረጋገጫ ለመስጠት በዚህ ወቅት ከሰማይ የተላከ ቅዱስ ጠባቂ አለ። ክርስቶስ በራስ ወዳድነት ቦይ ላይ እየፈሰሱ ያሉ የሀሳብ ማዕበሎችን ለመለወጥ በፀጋው ሙላት በዚያ ቦታ አለ። መንፈስ ቅዱስ የጌታቸውን ምሳሌ የሚከተሉ ሰዎችን የስሜት ኃይሎች ያነቃቃል። {1MCP 277.2}1MCPAmh 228.2

  አዳኙ ስለ እኛ የተቀበለው ውርደት ሲታሰብ ሀሳብ ከሀሳብ ጋር ይገናኛል፤ የትውስታዎች ሰንሰለት ይመጣል፣ የእግዚአብሔር ታላቅ ደግነትና የምድራዊ ጓደኞች ውለታና ገርነት ትውስታዎች ወደ አእምሮአችን ይመጣሉ። የተረሱ በረከቶች፣ ያለ አግባብ ጥቅም ላይ የዋሉ የምህረት ተግባራት፣ እንደ ቀላል ነገር የታዩ የደግነት ተግባሮች፣ ወደ አእምሮ ይመጣሉ። የከበረውን የፍቅር ተክል ያጨናነቁ የምሬት ስሮች ይገለጣሉ። የባሕርይ ጉድለቶች፣ ችላ የተባሉ ተግባሮች፣ እግዚአብሔርን አለማመስገን፣ ለወንድሞቻችን ያሳየነው ቅዝቃዜ፣ ይታወሳሉ። ኃጢአት እግዚአብሔር በሚያየው ብርሃን ይታያል። ሀሳቦቻችን ራስን የማስደሰት ሀሳቦች ሳይሆኑ ጥብቅ የሆነ ራስን የመቅጣትና የማዋረድ ሀሳቦች ናቸው። ባይተዋርነትን ያስከተለውን እያንዳንዱን የመለያ ግድግዳ ለመስበር አእምሮ ጉልበት ያገኛል። ክፉ ሀሳብና ክፉ ንግግር ይወገዳሉ። ሰዎች ለኃጢአቶቻቸው ንስሃ ይገቡና ይቅርታ ያገኛሉ። በቁጥጥር ሥር የሚያውለው የክርስቶስ ፀጋ በነፍስ ውስጥ ስለሚሆን የክርስቶስ ፍቅር በተባረከ አንድነት ልቦችን ወደ አንድነት ያመጣል። --DA 650, 651 (1898). {1MCP 277.3}1MCPAmh 228.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents